>

በአቶ ዮሃንስ ቧያለው ላይ አፈና ተፈፀመባቸው፣ ከኤርፖርት ታፍነው ተመልሰዋል (ፈለገ ግዮን)

በአቶ ዮሃንስ ቧያለው ላይ አፈና ተፈፀመባቸው፣ ከኤርፖርት ታፍነው ተመልሰዋል…!!!

ፈለገ ግዮን

*…. የበረራ የአውሮፕላኑ እንዲያልፈው እና እንዲመለስ ከተነገረው በኋላ በተመሣሣይ ስአት  የፌደራል ፖሊስ ቤተሠቦቹን እየደበደበ ከግቢ በማስወጣት ቤቱን አሽጎ ሄዷል!

አቶ ዮሃንስ ተረኛውን የኦህዴድ /ብልፅግናን ያለማቋረጥ እየታገለ ያለ እና የአብይ አህመድ የስልጣን መደለያ ሣያጓጓው፣ ከስልጣን የሚገኘው ጥቅም ሣያሣሣው ለአማራ ህዝብ ጥቅምና ክብር ሣይታክት እየታገለ ያለ እውነተኛው የህዝብ ልጅ ነው።

አቶ ዮሃንስ የሚያደርገው ትግል ዛሬ ላይ እንደማንኛውም ዜጋ በገዛ ሃገሩ መኖርና መንቀሣቀስ እንዳይችል ተረኛው መንግስት አፈና ፈፅሞበታል።

ዛሬ ነሃሴ 25/12/2014 አቶ ዮሃንስ ለግል ስራ ወደ ዱባይ ለመሄድ እንደማንኛውም ዜጋ የሚጠበቅባቸውን ጉዳይ አሟልተው ቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት ከደረሱ በኋላ የመጀመሪያውን ፍተሻ አልፈው የሁለተኛው የፍተሻ ደረጃ ላይ ሲደርሱ የተረኛው ደህንነት ነኝ ባይ መውጣት እንደማይችል እና እንደተከለከለ ከአለቆቹ ትዛዝ እንደደረሠው በመንገር የበረራ የአውሮፕላኑ እንዲያልፈው እና እንዲመለስ ከተነገረው በኋላ በተመሣሣይ ስአት በመኖሪያ ቤቱን የፌደራል ፖሊስ ቤተሠቦቹን እየደበደበ ከግቢ በማስወጣት ቤቱን አሽጎ የሄደ ሲሆን አቶ ዮሃንስ ከነ ቤተሠቡ ሜዳ ላይ ወድቋል ።

 

Filed in: Amharic