ህወሃት ወልቃይትን ከያዘ፣ የአማራ ህዝብ ዝንተ አለሙን ባሪያ ሆኖ ይኖራል
ብ/ር ጀኔራል ተፈራ ማሞ
~ የአማራ ልዩ ሀይል፣ በኮማንዶ፣ ፓራ ኮማንዶ ይሰልጥን ስንል የነበረው ህወሃት በዚህ ልክ እንደሚመጣ ስለምናውቅ ነበር ፤ የአማራ ክልል ተላላኪ አመራሮች ግን አልፈቀዱም::
~ ::
~ የአማራ ህዝብ የራሱ መሪ ሊያገኝ አልቻለም:: ህዝቡ የሰጠኸውን መሸከም የሚችል ህዝብ ነው:: የአማራ ህዝብ ታግሎ መጣል፣ ታግሎ መቀየር ፣ ታግሎ ማሻሻል የሚችል ህዝብ አይደለም::
~ የአማራ አመራሮች 30 እና 40 አመት ተላላኪ ሆነው እየቀጠሉ ሳለ የአማራ ህዝብ ግን መታገል አልፈለገም:: ህዝቡ ዋጋ ከፍሎ፣ መስዕዋትነት ከፍሎ አመራሮችን ከትክሻው ላይ አሽቀንጥሮ መጣል ነበረበት:: የአማራ ህዝብ ባ*ሪያ ሆኖ መኖር የሚችል ህዝብ ነው:: ህወሃት ራያ ቆቦን ሲቆጣጠር ደሴ የሚገኝ አመራር ወደ ደብረብርሀን የሚፈረጥጥ ነው:: ደሴ በጠላት ስትያዝ የባህርዳር አመራሮች ወደ አዲስ አበባ የፈረጠጡ ናቸው::
~ የአማራ አመራሮች ሚሊሻውን፣ ልዩ ሀይሉን፣ ፋኖን አደራጅተው አሰልጥነው አስታጥቀው መጠበቅ ሲገባቸው ፋኖን ሲያሳድዱት፣ ሲገድ*ሉት፣ ሲያስሩት ከረሙ:: ይህ ሁሉ ዘመቻ በፋኖ ላይ ሲካሄድ ህዝቡም ባላየ ባልሰማ ተኝቶ ነበር::
~ የአማራ ህዝብ በእራሱ ህልውና እና መሬት የመጣበትን ጠላት በራሱ ሀይል መመከት ካልቻለ እና ሌላ ሀይል ነጻ ያወጣኛል ብሎ ካሰበ አበቃለት:: ህዝቡ በራሱ አደረጃጀት እና ትጥቅ ጠላት ወያኔን አፈር ካላስበላ ዘላለሙን ሲደማ ይኖራል:: የትግራይ ታጣቅ ኤርትራን የምትፈራ ኤርትራ ብዙ ህዝብ ስላላት አይደለም:: ጠንካራ አደረጃጀት እና ስነልቦና ስላላቸው ነው:: የአማራ ህዝብ 30 እና 40 ሚሊየን ህዝብ ይዞ ግን ጠላት ወያኔ ሲፈነጭበይ ይታያል:: ይህም ደካማ አመራሮች ስለፈጠረ እና አብይ አህመድ ነጻ ያወጣኛል ብሎ ማሰቡ ነው (አብይን እኔ የጠቀስኩት)::
~ ህወሃት ህጻናትን እና ሽማግሌዎችን አሰልፎ የአማራን ህዝብ እየቀ*ጠቀጠ ያለው ቁርጠኛ ስለሆኑ እና ቁርጠኛ አመራር ስለፈጠረ ነው:: የአማራ ህዝብ ግን ከዚህ በተቃራኒው ነው:: አማራ :- ከ*ሀዲ ፣ ባ*ንዳ፣ ተላላኪ፣ ስል*ብ እና ሆዳ*ም አመራር ይዞ እንዴት ሊያሸነፍ ይችላል?
~ ዘመነ ካሴ እና ማስረሻ ሰጤ ለአማራ ህዝብ ጥቅም ቁርጠኛ አቋም ያላቸው ልጆች ነበሩ፣ ነገር ግን አመራሩ እኒህን እንቁ ልጆች መጠቀም አልቻለም: በዚህም ምክንያት የአማራ ህዝብ ያለ መሪ፣ ያለ አደራጅ ተበትቦ እንዲበላ ሆኗል::
~ ልጆቹን እንደ አውሬ አድኖ የሚያጠፋ አመራር ተሸክሞ፣ ያስወረረውን አመራር መልሶ አመራር አድርጎ የሚሾም ህዝብ፣ ተላላኪን ሆ*ዳም አመራር መሪዬ ነው ብሎ የተቀበለ ህዝብ በአለም ላይ ያማራ ህዝብ ነው:: ለዚህ ህዝብ እንዴት ብለህ ዋጋ ትለፍላለህ? ይህ ህዝብ የሚቀ*ጠቀጠው: የሚጨ*ፈጨፈው በራሱ ችግር ነው::
ህወሃት ወልቃይትን ከያዘ፣ የአማራ ህዝብ ዝንተ አለሙን ባሪያ ሆኖ ይኖራል