>

የከንቲባው ፍጻሜ…!!   (ዘመድከን በቀለ)

የከንቲባው ፍጻሜ…!!

 ዘመድከን በቀለ


“…በሰሜን ሸዋ በሸዋሮቢት ከተማ በትናንትናው ምሽት የከተማዋ ከንቲባ አቶ ውብሸት አያሌው ባልታወቁ ሰዎች ተመተው መገደላቸው ይታወሳል። ከአቶ ውብሸት በተጨማሪ የአቶ ውብሸት ባለቤትም የተመቱ ሲሆን ነገር ግን ለከፍተኛ ህክምና ወደ ደብረብርሃን ይሁን ወደ አዲስ አበባ ለጊዜው ወዳልታወቀ ሥፍራ ለህክምና መላካቸው እንጂ እስከአሁን የሞታቸው ዜና አልተሰማም።

“…የሸዋሮቢት ከተማ የተለየያዩ ከንቲባዎችን አስተናግዳ ታውቃለች። ከአቶ ውብሸት በፊት አቶ ቴዎድሮስ እና ወሮ ሉባባ የሚባሉ ሁለት ከንቲባዎችም ተሾመው ነበሩ። አቶ ቴዎድሮስ በፋኖዎች የፌስቡክ ገፅ ውስጥ ገብተው በኮመንት መስጫ ሳጥኑ ላይ ” አንድ ሞርታር ይዞ መጎረር አይከብድም?” ብለው አስተያየት ከሰጡ በኋላ በደረሰባቸው ውግዘት ተደናግጠው ሥልጣን ለቀው አሁን ሰላማዊ ሰው ሆነው ብስክሌት እየነዱ በሰላም መኖር ከጀመሩ ሰነባብተዋል ነው የሚባለው። ወሮ ሉባባም በሁሉ ዘንድ ተወዳጅ የነበሩና በእድገት ወደ ዞን ያደጉ ሴት ከንቲባ ነበሩም ይላሉ አስተያየት ሰጪዎች። ቀጥሎ የመጡት አቶ ውብሸት ነበሩ።

“…አቶ ውብሸት የተረከቡት የሸዋሮቢት ከተማ ህዝብ በጁንታው የደቀቀ፣ በኦነግ ሴቶቹ የተደፈሩባት፣ ንብረት የተዘረፈባት፣ ዕልፍ ጀግኖች የወደቁባት፣ በአጠቃላይ የኢኮኖሚዋም፣ የሥነ ልቦናም ድቀት የገጠማት፣ ሆደባሻ ከተማን ነበር። ለዚህ በዘርፈ ብዙ ሀዘን ለተመታ ከተማ ህዝብ ደግሞ የሚያስፈልገው የሚያጽናና፣ የሚያበረታታ፣ ለሥራ የሚያፋጥን፣ የሥነ ልቦና ህክምና የሚሰጥ ሰው ነበር መመደብ የነበረበት።

“…መንዝን በቤተሰብ የሚያስተዳድረው አቶ ግርማ የጅብጥላ ግን ይሄን ትእቢተኛ ሰው መደበ። ህዝቡን ሰብስቦ የሚደነፋበት፣ አሳይሃለሁ፣ እቆርጥሃለሁ፣ እፈልጥሃለሁ እያለ እንደ ከንቲባ ሳይሆን እንደ ጀነራል የሚያደርገው፣ ከወፈሩ አይፈሩ ሆኖ ጮማው አዕምሮውን ደፍኖበት በጦርነቱ የሞቱ የፋኖና የሚሊሻ ቤተሰቦች ላይ ሳይቀር እንደግርማ የጅብጥላ ሲያቅራራ ከረመ ይላሉ አስተያየት ሰጪዎች።

“…ከዚህም አልፎ ዐቢይን ተሳደባችሁ ብሎ የሸዋ ሮቢትን ወጣቶች በጅምላ ፈጃቸው። በቅርቡም ሁለት ወጣቶችን አስገደለ። ግርማ የሺጥላ ለዚህ ጀብዱ ቪ8 መደበለት። በዐማራ ልዩ ኃይልም እንዲጠበቅ ተደረገ። በቃ ሚጢጢዬ አምባገነን ሆነ። ትናንት ምሽት ግን ውብሸት ባልታወቁ ሰዎች ተገደለ። አብረውት የነበሩትና ግርማ የሺጥላ የመደበለት የዐማራ ልዩ ኃይል አባላት ፖሊሶችም ጥለውት ሸሹ። አላዳኑትምም። አልተከላከሉለትምም። ሚስቱም ተመታች። ቨ8ቱም ቀረ። የግርማ የጂብጥላም ሞራል አብሮ ደቀቀ። ዐማራን ለማዋረድ ይደክም የነበረው አንደበትም ተዘጋ።

“…ከንቲባው ባለፈው የሸዋሮቢት ወጣቶችን ከረሸነ፣ ካስረሸነ በኋላ የሟች ቤተሰቦች ሀዘን እንዳይቀመጡ አስደረገ። ከለከለ። ሁሉም አዘኑበት። ለዚህ ተግባሩም የመንዙ ግርማ የጅብጥላ ጀግና ብሎ ጠራው። አሞካሸውም። ዛሬ በከንቲባ ውብሸት መኖሪያ ቤት ለቅሶ የሚደርሰው አንድም ሰው ጠፋ። ወዳጄ የሸዋ ህዝብ አይጥላህ። እንዲያውም በከንቲባው ሞት የተነሣ ግርማ የጂብጥላ ጦር ይልካል ተብሎ ተጠብቆ የነበረ ቢሆንም ከተማዋ የተለመደ ሰላማዊ እንቅስቃሴዋን ቀጥላለች። ቀጣዩ ከንቲባም ከውብሸት ትምህርት የወሰደ እንደሚሆን ይታመናል ይላሉ ሸዋሮቢቶች።

“…አሁን ከዘመነ ህወሓት ጀምሮ 30 ዓመት ሙሉ ብአዴን ሆነው ዐማራ ህዝብ ላይ ያላገጡ ነውረኞች ደንግጠዋል ይላሉ። አያ ግርማ የጂብጥላም ጠባቂ ቁጥር ይጨመርልኝ ብሏልም ተብሏል። በጠባቂ ብዛት ግን አይዳንም። ቤተሰቡ ያለቀበት፣ የታሠረበት ዐማራ፣ የዐማራ ፋኖ ከሸዋሮቢት ትምህርት የወሰደም ይመስላል። ሃዘን ከገባ አይቀር ብአዴኖች ቤትም ይግባ እንጂ ያሉም ይመስላሉ። አባቱ የተገደለበት፣ ወንድሙ የተገደለበት፣ የታሰረበት ሁላ በቀጣይ ወደ ምሥራቅ ወደ ሸዋሮቢት መመልከቱም አይቀርም። ጎን ለጎን ኦነግም አስወግዶት ቢሆንስ የሚሉም አሉ።

“…የሆነው ይሄ ነው…!! የሞቱትን የዐማራ ወጣቶች ግን ነፍሳቸውን ይማር። በቀጣይ እንዲሁ ዘገባ ሲኖር አቀርብላችኋለሁ።

Filed in: Amharic