>

የይልማ መርዳሳ የጭስ ቦምብ (መስፍን አረጋ)

የይልማ መርዳሳ የጭስ ቦምብ

መስፍን አረጋ

ፍራብ (ፍሬ ሐሳብ፣ abstract)


የኦነጉ አየር ኃይል አዛዥ ይልማ መርዳሳ ጭስ ለማስነሳት ሲል ብቻ መቀሌ ላይ እንደዋዛ ጣል የሚያደርጋት የጭስ ቦምብ፣ በጭሱ አፍና የምታስለቅሰው የአማራን ሕዝብ ሲሆን፣ በጭሱ ሸፍና የምታስቀው ደግሞ የወያኔንና የኦነግን አመራሮች በተለይም ደግሞ ደብረጽዮንን እና ጭራቅ አሕመድን ነው፡፡  ይልማ መርዳሳ መቀሌ ላይ የጭስ ቦምብ በመጣሉ ተቃውሞ መውጣት ያለበት ያማራ ሕዝብ እንጅ የትግሬ ሕዝብ አይደለም፡፡    

—————————————————-

ወያኔና ኦነግ የአማራን ሕዝብ በየዕለቱ ከሚጨፈጭፉትና ከሚያርዱት በተጨማሪ በገፍ ለመጨፍጨፍና ለማረድ ሲፈልጉ፣ ጭራቅ አሕመድና ደብረጽዮን የተጣሉ ይመስሉና የቁጩ ግርግር ፈጥረው “ጦርነት ጀመሩ” ያስብላሉ፡፡   ወያኔ ወደፊት ገፍቶ ያማራን ክልል ወርሮ ወሳኝ ቦታወችን ይዞ ይጠባበቃል፡፡  

ጭራቅ አሕመድ ደግሞ “ወያኔን ለመከላከል” በሚል ሰበብ በሎሌው በብአዴን አማካኝነት ክተት አውጆ የአማራን አርሷደሮች ስብስቦ ይጭንና ወሳኝ ቦታ ይዞ ከሚጠባበቃቸው ከወያኔ ፊት ዘርግፎ ይሸሻል፡፡ ወያኔ ደግሞ ያለ ስንቅ፣ ትጥቅና መሪ ከፊቱ የተዘረገፉለትን የአማራ አርሷደሮች በመትረየስና በድሽቃ በመረፍረፍ እንደቅጠል አርግፎ “ባስር ሺ የሚቆጠሩ የዐብይ አሕመድ ወታደሮችን ደምስሸ ባስር ሺ የሚቆጠሩትን ማረኩ” በማለት አዶ ከበሬ እየደለቀ፣ የውስጥና የውጭ ደጋፊወቹን ያስፈነድቃል፡፡  

ወያኔ የአማራ ክልልን ወርሮ አማሮችን በመረፍረፉ ፖለቲካዊ ኪሰራ እንዳይደርስበትና ዓለም ዐቀፍ ተቃውሞ እንዳይገጥመው ደግሞ፣ የይልማ መርዳሳ ጠያራ መቀሌ ላይ አንድ ቦምብ ትጥልና ትልቅ ጭስ ታስነሳለች፡፡  ቦምቧ ትልቅ ጭስ የምታስነሰው ደግሞ የምትጣለው ጭራቅ አሕመድና ደብረጽዮን ከምዕራባውያን አጋሮቻቸው ጋር በመመካከር አስቀድመው ባዘጋጇቸው ትምህርትቤት ወይም ሆስፒታል ቅጽር ውስጥ ሥራየ ብለው በተቀመጡ የነዳጅ በርሜሎች ላይ በመሆኑ ነው፡፡  ከነዳጅ በርሜሎቹ ጋር እንዲቀጣሉና አስከሬናቸው ለዕይታ እንዲቀርብ የሚፈረድባቸው መከረኞች ደግሞ ወያኔ “የማረከቻቸው” ያማራ አርሷደሮች ባይሆኑ እንጅ ቢሆኑ አያስገርምም፡፡

የአማራ ሕዝብ ሆይ፣ ቆም ብለህ አስብ እስኪ፡፡  የትኛው የጦቢያ ትምህርት ቤት ወይም ሆስፒታል ነው፣ በነዳጅ ጢም ብሎ እንደተሞላ ቦቴ የሚንበለበለውየመጻፊያ እርሳስና የራስ ምታት መድሐኒት ችግር በሆነበት አገር፣ የትኛው ትምህርት ቤት ወይም ሆስፒታል ነው በተቀጣጣይ የተሞላው?  ለማንኛውም መቀሌ በሚገኝ ትምህርት ቤት ወይም ሆስፒታል ቅጥር ውስጥ ሥራየ ብለው የተቀመጡ በነዳጅ የተሞሉ በርሚሎች ሥራየ ብለው ተቃጥለው ተንበልብለዋል፡፡  በርሚሎቹ የተቃጠሉት ደግሞ በይልማ መርዳሳ ቦንብ ሳይሆን በራሱ በወያኔ ክብሪት ሊሆን ይችላል፡፡  ወያኔ ግን ያቃጠለብኝ ይልማ መርዳሳ ነው ብሎ ከሷል፡፡  ይልማ መርዳሳ ደግሞ የወያኔን ክስ አላስተባበለም፡፡  ስለዚህም መቀሌ ላይ ጭስ ያስነሳቸው የይልማ መርዳሳ ቦንብ መሆኗን መቀበል የግድ ነው፡፡      

የይልማ መርዳሳ የጭስ ቦንብ መቀሌ ላይ ትልቅ ጭስ እንዳስነሳች ደግሞ አፍቃሪ ወያኔ የሆኑት የምዕራባውያን ሚዲያወች (BBC, CNN, New York Times ወዘተ.) መቀሌ በቦንብ ተደበደበች፣ ሆስፒታሎች ተቃጠሉ፣ ሕሙማን አለቁ፣ ትምህርት ቤቶች ወደሙ፣ ሕጻነት ተፈጁ የሚለውን (አስቀድመው ያዘጋጁትን) ዜናቸውን አለቅጥ እያጮኹ በማጧጧፍ በመላው ዓለም ያሰራጩታል፡፡  ወሬው ሁሉ ስለ መቀሌ መደብደብና ስለ ትግሬ ሕዝብ ሰቆቃ ብቻ ይሆናል፡፡  

በግንባር በደብረጽዮን በጀርባ በጭራቅ አሕመድ የሚጨፈጨፈው የአማራ ሕዝብ፣ ጨፍጫፊ ተብሎ ይጠቀሳል፣ ይወቀሳል፣ ይከሰሳል፡፡  ተወራሪው አማራ ወራሪ ተብሎ ይወገዛል፡፡  ወያኔ ወልደያን ዙርያዋን ከቦ እየደበደበ ሳለ፣ ለወያኔ ያላት ፍቅር ወደር የሌለው ሱዛን ራይስ (Susan Rice) በማርያም ጣቷ የምታሸከረክረው ያሜሪቃ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የትግራይ ሕዝብ ሰቆቃ ባስቸኳይ እንዲያቆም፣ የአማራ ኃይል ከወልቃይት ባስቸኳይ ለቆ ይውጣ የሚል መግለጫ ያወጣል፡፡  

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጭራቅ አሕመድ፣ ይልማ መርዳሳን ጨምሮ መከላከያን ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠሩት ደግሞ ኦነጋውያንና የኦነጋውያን ቅጠረኞች የሆኑት አበባው ታደሰን የመሳሰሉ ፀራማሮች በመሆናቸው ምክኒያት መከላከያ ከደሙ ንጹሕ ይደረግና፣ ያልሞት ባይ ተጋዳይ ትግል የሚያደርገው የአማራ ሕዝባዊ ኃይል ግን የጦር ወንጀለኛ ይደረጋል፡፡  በትግሬወች ላይ ተፈጸመ የሚባለው የፈጠራ ወንጀል ሁሉ ባማሮችና ባማሮች ላይ ብቻ ይላከካል፡፡  የኦሮሞና የትግሬ ሕዝብ ሰላም ናፋቂ፣ የአማራ ሕዝብ ግን ጥብ ያለሽ በዳቦ ባይ ሞገደኛ፣ ጦረነት ናፋቂ ነፍጠኛ ተደርጎ ይፈረጃል፡፡    

ይልማ መርዳሳ መቀሌ ላይ እንደ ዋዛ ጣል የሚያደርጋት የጭስ ቦንብ ዋና ተግባሯ ይሄውና ይሄው ብቻ ነው፡፡  ትግራይ በቦንብ ተደበደበች፣ ያስደበደቧት ደግሞ ዐብይ አሕመድን የከበቡት አማሮች ናቸው በሚል ሰበብ ወያኔ የትግሬን ሕዝብ ባማራ ጥላቻ ይበልጥ አነሳስቶ ወረራውን ይበልጥ እንዲገፋበትና፣ በወረራው ዓለማቀፍ ተቃውሞ እንዳይደርስበት ማድረግ፡፡ 

ይልማ መርዳሳ መቀሌ ላይ እንደ ዋዛ ጣል የሚያደርጋት የጭስ ቦንብ ሌላው ተግባሯ ደግሞ፣ ጭራቅ አሕመድ ወያኔን ደበደበ ተብሎ በውነትም ከወያኔ ጋር የምሩን የተጣላ እንዲያስመስልና የአማራን ሕዝብ ማታለሉንና ማጃጃሉን እንዲቀጥል ማስቻል ነው፡፡  የጭራቅ አሕመድን ማታለልና ማጃጃል ይበልጥ አሳማኝ ለማድረግ የሚጣጣሩት ደግሞ የጭራቅ አሕመድ አፍቃሪ ወይም ተቀጣሪ የሆኑት፣ ዜና ቲዩብ፣ የኔታ ቲዩብ፣ ኢሳትና መሰሎቻቸው ናቸው፡፡  

ይልማ መርዳሳ መቀሌ ላይ እንደ ዋዛ ጣል የሚያደርጋት የጭስ ቦንብ ከነዚህ ከሁለቱ ውጭ ሌላ ምንም ተግባር የላትም፡፡  በተለይም ደግሞ ምንም ወታደራዊ ጠቀሜታ የላትም፡፡  ወያኔ በመቶወች የሚቆጠሩ የጭነት መኪኖችን እያግተለተለ፣ ወታደሮቹንና ስንቁን በጠራራ ፀሐይ ወደ አማራ ክልል ሲያመላለስ፣ ካማራ ክልል የዘረፈውን ደግሞ ወደ ትግሬ ክልል ሲያጓጉዝ፣ ዓይታ እንዳላየች የምታልፈው የይልማ መርዳሳ ጠያራ፣ መቀሌ ላይ ቦንብ ጥላ በነዳጅ የተሞሉ በርሜሎች የምታቃጥለው፣ ትልቅ ጭስ አስነስታ ለወያኔ ወረራ ትልቅ ሽፋን ለመስጠት ስትል ብቻ ነው፡፡  

ይልማ መርዳሳ መቀሌ ላይ እንደዋዛ የሚጥላት የጭስ ቦንብ የምታስለቅሰው የአማራን ሕዝብ ሲሆን፣ የምታስደስተው ደግሞ የወያኔንና ኦነግን አመራሮች በተለይም ደግሞ ደብረጽዮንንና ጭራቅ አሕመድን ነው፡፡   በመሆኗም፣ ይልማ መርዳሳ መቀሌ ላይ ቦምብ በመጣሉ ተቃውሞ መውጣት ያለበት ያማራ ሕዝብ እንጅ የትግሬ ሕዝብ አይደለም፡፡    

መስፍን አረጋ mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic