>

ጉዳዩ ሄዶ ሄዶ "ድርድር እፈልጋለሁ ግን አልፈልግም !" እንዳይሆን...!?! (ያሬድ ሀይለማርያም)

ጉዳዩ ሄዶ ሄዶ “ድርድር እፈልጋለሁ ግን አልፈልግም !” እንዳይሆን…!?!

ያሬድ ሀይለማርያም

ህውሃት በስተመጨረሻ በጫናም ይሁን በሌሎች ምክንያቶች ተኩስ ማቆምና ድርድር እፈልጋለሁ ማለቱ እጅግ በጎ ነገር ነው። ይህን አቋሙን ቀደም አርጎት ቢሆን ኖሮ ተጨማሪ ደም መፋሰስን ያስቀር ነበር። በመንግስት በኩል ተኩስ ለማቆምና ለሰላም ቀድሞ የታየውን በጎ ፍላጎት አሁንም ይኖረዋል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። የተኩስ ማቆሙም ሆነ የሰላም ፍላጎቱ የሁለት እዬሽ ከሆነ ድርድሩ የመሳካት እድሉ ሰፊ ነው።

ወደ ሰላም ድርድሩ ለመግባት ግን የሚቀርቡ ቅድመ ሁኔታዎች ላይ እጅግ መጠንቀቅ የግድ ይላል። በድርድር ወቅት መነሳት ያለባቸውን እና የመደራደሪያ ነጥብ መሆን የሚገባቸውን ነገሮች ከወዲሁ እያመጡ ወደ ድርድር ለመግቢያ እንደ ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጥ ግን በሌላ ቋንቋ ድርድር እፈልጋለሁ ግን አልፈልግም እንደማለት ሊቆጠር ይችላል።

– የድንበር ይዞታ ጥያቄ፣

– የትጥቅ መፍታት፣

– የቀጣይ ግንኙነቶችና፣

ወዘተ … እልባት የሚሹ እና ወደ ውይይት ከተገባ በኋላ የመደራደሪያ ነጥቦች የሚሆኑ እንጂ ወደ ውይይት ለመግባት ቅድመ ሁኔታ መሆን አይገባቸውም ብዬ አምናለሁ።

አሁንም ሰላም እንዲወርድ፣ እርቅ እንዲሰፍን እና ተጠያቂነት እንዲኖር ከምኞት ባለፈ እንጣር።

Filed in: Amharic