>

የኦሮሞ ነፃነት ግንባርን ያስቆጣው የትግራይ መንግስት የድርድር ፍላጎት መግለጫ...(ኦነግ/OLF)

“የኦሮሞ ህዝብ የራሱን እጣፈንታ በራሱ ጥረት ይወስናል፤ የማንንም እርዳታም ሆነ እገዛ አይፈልግም….!!!” ኦነግ/OLF

የኦሮሞ ነፃነት ግንባርን ያስቆጣው የትግራይ መንግስት የድርድር ፍላጎት መግለጫ…

ኦነግ/OLF በተለየ ሁኔታ ከትግራይ ህዝብ ተወካይ ህወሓት ጋር አብሮ የመስራት እንቅስቃሴውን ሙሉ በሙሉ የካደ ተግባር ስለመፈፀሙ ለመላው አለም አቀፍ ማህበረሰብ ለማሳወቅ ወስኗል።

የህወሓት ሃይል አሁንም የኦሮሞ ህዝብን ጥያቄ የረሳ፣ ለበደል ጊዜ እና ለጋራ ነፃነት አብሮ የመቆም ቁርጠኝነቱን ያዋረደ ተግባር መፈፀሙን ገለጿል። የትግራይ ህዝብም ይህ ድርጊት ትልቅ ስህተት መሆኑን ተረድቶ መሪ ድርጅታቸውን ህወሓትን ወደመስመሩ እንዲመለስ እንዲያደርጉት በመግለጫው አሳስቧል።

ለዘመናት በክህደት ዑደት ውስጥ የሚዋጀው ይህ የህወሓት ሃይል ራሱን ተንበርካኪ ባደረገ መልኩ በብልፅግና መንግስት እግር ስር መውደቁ በእጅጉ እንዳሳሰበው ኦነግ አሳውቋል። ከዚህ በፊትም በ1991 የመንግስት ለውጥ ሰዓት ላይ ይህንን መሰል ክህደት በኦሮሞ ህዝብ ትግል ላይ ጥቁር ጠባሳ እንደነበረው የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው ።

የትኛውንም ቁልፍ ውሳኔ ሲወስን ከኦሮሞ ህዝብ አታጋይ ሃይላት ጋር ሲያደርግ የነበረውን ውይይት በመተው አሁንም በቀጥታ የአካባቢውን ሙሉ የሃይል አሰላለፍ በሚረብሽ መልኩ TPLF ይህንን ውሳኔ ወስኖ በሚዲያ አሳውቆናል።

በተደጋጋሚ የተፈፀሙ ክህደቶች ለኦሮሞ ህዝብ አታጋይ ድርጅት ኦነግ/OLF ትልቁን ውሳኔ እንዲወስን አስገድዶታል። ከዚህ በኋላ ከህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ህወሓት ከተባለ ድርጅት ጋርም ሆነ ሌሎች ተመሳሳይ ክህደት ውስጥ ከሚገቡ የአካባቢው አደረጃጀቶች ጋር አብሮ ላለመስራት ወስኗል።

Filed in: Amharic