>

አቶ ስንታየሁ ወደ ኦሮሚያ ክልል ተወሰዱ...! ባልደራስ

አቶ ስንታየሁ ወደ ኦሮሚያ ክልል ተወሰዱ…!

ባልደራስ

*…. ጋዜጠኛ ዓባይ ዘዉዱ የሽብር ክስ ቀረበበት!

የባልደራስ የድርጅት ጉዳይ ሀላፊው እና የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባሉ አቶ ስንታየሁ ቸኮል ቤተሰቦቻቸው ዛሬ የግፍ እስረኛውን ለመጠየቅ ሲሄዱ ከነበሩበት ወረዳ ዘጠኝ ፖሊስ ጣቢያ ሊገኙ አልተቻለም። ወዴት እንደተወሰደ ሲጠይቁ አዲስ አበባ ወንጀል ምርመራ(ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ) እንደተወሰደ የተነገራቸው ቢሆንም አዲስአበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሲሄዱ ግን ሊያገኙት አልቻሉም።

ለቤተሰቦቻቸው እንደደረሰው መረጃ ከሆነ የግፍ እስረኛው አቶ ስንታየሁ ወደ ኦሮሚያ ክልል ተወስደዋል።

የብልፅግና መንግስት ቂም በቀል መወጫ የሆኑት አቶ ስንታየሁ ከዚህ በፊት ለአራት ግዜ በፍርድ ቤት ዋስ ተፈቅዶላቸው የተከፈለ ቢሆንም እስካሁን ሊፈቱ አልቻሉም። ይህ ነውረኛ ድርጊት ኢትዮጵያን እያስተዳደረ ያለውን የብልፅግና ፓርቲ ፍፁም ህገወጥነትና አንባገነንነት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው።

ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የግፍ እስረኛው አቶ ስንታየሁ የተፈቀደላቸው ዋስ ተከብሮ በአስቸኳይ ከህገወጡ ከእስር እንዲፈቱ ያሳስባል።

በተያያዘ መረጃ

ጋዜጠኛ ዓባይ ዘዉዱ በኦሮሚያ እና በቤንሻንጉል ክልል በአማራ ላይ የሚፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በመዘገቡ የሽብር ክስ ቀረበበት!

Filed in: Amharic