>
5:18 pm - Monday June 15, 2685

ዛሬ በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ላይ ኦነግ-ሽሜ በዐማሮቹ ላይ የተኩስ እሩምታ ከፍቷል....!(ዘመድኩን በቀለ)

ዛሬ በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ላይ ኦነግ-ሽሜ በዐማሮቹ ላይ የተኩስ እሩምታ ከፍቷል….!

ዘመድኩን በቀለ

* …. ቁጥራቸው ያልተረጋገጠ  አማሮች ሙትና ቁስለኛ ሆነዋል…!!!

“…ሰሞኑን የኦህዴድ ብልጽግና በወለጋ ሆሮ ጉዱሩ ዞን በጀርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ላይ የዐማራም የኦሮሞም ተወላጆችን ይሰበስባል። ይሰበስብና እንዲህ ይላቸዋል። ኦሮሞ የሆናችሁ ለጊዜው ከአካባቢው ዞር በሉ። የሚመጣው ኃይል ማን ኦሮሞ፣ ማን ዐማራ እንደሆነ ለማጣራት መድከም የለበትም። ነገሩ ሲበርድ ሃገር ሲረጋጋ ትመለሳላችሁ። ዐማሮች ግን በጊዜ ከዚህ ብትጠፉ ይሻላችኋል። የሚያድናችሁ፣ የሚታደጋችሁ ማንም ኃይል የለም በማለት ቃል በቃል ለተሰብሳቢው ህዝብ ይነግሯቸዋል።

“…መሸ ነጋ፣ ሁለተኛም ቀን ሆነ። የአካባቢው የኦሮሞ ተወላጆች በተባሉት መሠረት ዕቃቸውን ሸክፈው በተሰጣቸው ኮድ መሠረት አካባቢውን ለቀው ወጡ። ዐማሮቹ ግን መሄጃም የለን፣ የትም አንሄድም ብለው ባሉበት የሚመጣውን ለመቀበል ተዘጋጅተው ይጠባበቁ ጀመር። የዐማሮቹን ጽናት እና ቁርጠኝነት ያየው የኦህዴድ ብልፅግና ሌላ መመሪያ አወጣ። “ማንም የዐማራ ተወላጅ ከወንዝም ቢሆን ከቧንቧ ከቦኖ ውኃ መቅዳት አይችልም” አለ። ፈርተው ሴቶች ከቤት ዋሉ።

“…መሸ፣ ነጋ፣ ሦስተኛም ቀን ሆነ። ወንድ ወንዶቹ ዐማሮች ሁላችንንም ጨፍጭፈው ያለዘር ከሚያስቀሩን እናንተ ሴቶችና ህጻናት አካባቢውን ለቃችሁ ተሰደዱ፣ ብለው ማቲውንና ሴቶችን ከወረዳው አሸሹ። አሸሹናም እነሱ ወንዶቹ ብቻ በመንደሩ ቀሩ። ቆይቶ የህዝቡን መሰደድ የተመለከተው የወረዳው ኦህዴድ መጣ። መጣና የቀሩቱን ወንዶቹን መሣሪያ አምጡ አላቸው። ሕጋዊ ነን። ለምን እንሰጣለን። በአስተዳደሩ ውስጥ በመዋቅር የታቀፍን ሚኒሻዎች እኮ ነን ብለው ይመልሳሉ። ኦህዴዶቹ ኃይል ለመጠቀም ሞከሩ። ዐማሮቹም ለመሞት የቆረጡ ስለነበር በአቋማቸው ፀኑ።

“…መሸ ነጋ አራተኛም ቀን ሆነ። አሁን ፍርዬ ከአዲስ አበባ የኢንተርኔት ኔትወርክ አቋረጠች። የፍርዬ ዋነኛ ሥራም ይሄ ነው። ኔትወርክ ሲቋረጥ ሸኔ የሚባለው የሽሜ ተለዋጭ ኃይል ጭፍጨፋ እንዲጀምር ኮድ መስጠታቸው መሆኑ ነው። ኔትወርኩ ሲጠፋ መሣሪያ የሌላቸው ባገኙት መንገድ መሸሽ ጀመሩ። መሣሪያ ያላቸው ግን የመጣው ይምጣ ብለው የሚሆነውን መጠባበቅ ያዙ። ቀደም ብሎ ኦህዴድ መከላከያውን በትእዛዝ አስወጥቶታል። የኦሮሚያ ልዩ ኃይልም በስፍራው የለም። ቢኖርም ከኦነግ የተለየ የሚያመጣው ነገር የለም። ቆይቶ ባለ ጉድሩዎቹ ሹርቤዎቹ የኦነግሽሜ ጦር ከነዘመናዊ መሣሪያቸው ወደ ጃርዴጋ ጃርቴ ግልብጥ ብለው መጡ። ፈሰሱም።

“…መሸ ነጋ፣ አምስተኛ ቀን። ዛሬ ሐሙስ ከማለዳው  12:00 ጀምሮ የተፈራው ደረሰ። በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ላይ ኦነግሽሜ የተኩስ እሩምታ በዐማሮቹ ላይ ከፈተ። እስከ አሁን እኔ ራሴ ደውዬ ያናገርኳቸው ዐማሮች እንደነገሩኝ ከሆነ ከ5 በላይ ዐማሮች ወድቀዋል። ተረሽነዋል። አንድ የ7 ልጆች አባት፣ አንድ ሌላ የ5 ልጆች አባት እና አንድ ወጣት ተማሪ መገደላቸውን ነግረውኛል። የሁለቱ ሬሳ እስከአሁን አልተገኘም። ግድያውም ተኩሱም ግን እንደቀጠለ ነው።

“…በሰሜን ጦርነቱ እየተካሄደ ያለው በዐማራ ምድር ላይ ነው። ትግሬም ራሱ በድሮንም፣ በጀትም የሚያልቀው በዐማራ ምድር ላይ ነው። ትግሬም የሚታኮሰው የሚጨፋጨፈውም በዐማራው ምድር ላይ ነው። ዐማራው ደግሞ ለጦርነቱ ከወተት አንሥቶ እስከ ሰንጋ ድረስ ለሃገር መከላከያው ሳይሰለች፣ ሳይሰስት፣ ሳያቋርጥ እያቀረበ ነው። ትግሬዎቹ ሲወሩትም የሚዘርፉት፣ ከሊጥ አንሥቶ እስከ ሽሮ በርበሬ የሚያወድሙበት ዐማራውን ነው። እሱ እየተራበ እስኪወረር ጥምር ጦሩን፣ ሲወረር ደግሞ በወያኔ በዐጽሙ እስኪቀር ድረስ እየወደመ ያለው ዐማራው ነው።

“…በወለጋም ይኸው እየታረደ ያለው ያው ዐማራው ነው። ያውም የወሎ እስላም ዐማራ። ዐማራ

Filed in: Amharic