የዘመነ ካሴ መታሰር፤ የጭራቅ አሕመድ ዐዲስ ዘዴ
መስፍን አረጋ
ጭራቅ አሕመድ ይሄን ሁሉ የመከራ ዶፍ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚያወርደው በኦነግ ጥንካሬ ሳይሆን ራሱን የአማራን ሕዝብ በማዳከም ነው፡፡ የአማራን ሕዝብ ማዳከም የቻለው ደግሞ የአማራን ሕዝብ በባዶ ንግግር አፍዝዞ በማደንገዝ የአማራ ሕዝብ ዋና ጠላት እሱና እሱ ብቻ ሆኖ ሳለ፣ የአማራ ሕዝብ ዋና ወዳጅ እሱና እሱ ብቻ መስሎ በመቅረብ ነው፡፡ አሁን ላይ ግን ይህ ዘዴው ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ከሽፎበታል፡፡ የአማራን ሕዝብ በባዶ ንግግር የማታለል ቁማር ተበልቷል፡፡ በዚህም ምክኒያት የአማራን ሕዝብ መብላቱን ለመቀጠል፣ ጭራቅ አሕመድ ሌላ ዓይነት ዐዲስ ቁማር መቆመር የግድ ሁኖበታል፡፡ የዘመነ ካሴ መታሰርም የዚሁ የዐዲሱ ቁማር አካል ነው፡፡
ዘመኔ ካሴን አታልሎና አባብሎ እጁ በማስገባት ያሰረው ጭራቅ አሕመድ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም (ምንም እንኳን ጭራቅን ማመኑ የራሱ የዘመነ ጥፋት ቢሆንም)፡፡ ጭራቅ አሕመድ ዘመነን በማዋረድና በዘመነ መዋረድ ተከፋይ ብአዴኖቹን በማስጨፈር የአማራን ሕዝብ ለማዋረድና በጎጥ ለመከፋፈል ማድረግ የሚፈልገውንና የሚችለውን ስላደረገ፣ ከዚህ በኋላ የዘመነ ታስሮ መቆየት ለጭራቅ አሕመድ ምንም ፋይዳ የለውም፡፡
ስለዚህም ቀጣዩ የጭራቅ አሕመድ ርምጃ ዘመነን ከእስር ፈትቶ፣ የአማራ ሕዝብ ወዳጅ እሱና እሱ ብቻ መስሎ በመቅረብ፣ በአማራ ሕዝብ ያጣውን ተቀባይነት መልሶ ማግኘትና የአማራን ሕዝብ እንደ ቀድሞ እያታለለ መብላቱን መቀጠል ነው፡፡ ባጭሩ ለመናገር፣ ጭራቅ አሕመድ ዘመነን ያሰረው አማራን ለማዋረድ ሲሆን፣ የሚፈታው ደግሞ አማራን ለማረድ ነው፡፡
ስለዚህም ሰፊው የአማራ ሕዝብ ወይ፡፡ ዋና ትግልህ መሆን ያለበት ዘመንን ለማስፈታት ሳይሆን፣ ዘመንን ያሰረውን ጭራቅ አሕመድን ለማሰር ነው፡፡ ጭራቅ አሕመድን ስታስር ዘመነ ካሴ ብቻ ሳይሆን ጭራቅ አሕመድ ያሰራቸው ሁሉም ጀግኖችህ ባንድ ጀምበር ይፈታሉ፡፡ ስለዚህም ቁልፉ ጥያቄ የአማራ ሕዝብ ጭራቅ አሕመድን የሚያስረው እንዴት ነው የሚለው ነው፡፡
ጭራቅ አሕመድ የአማራን ሕዝብ በልቶ የማይጠረቃ አረመኔ ኦነጋዊ አውሬ ቢሆንም፣ የአማራን ሥጋ የሚዘነጣጥልባቸው ጥርሶቹ ግን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ብአዴኖች ናቸው፡፡ በተለይም ደግሞ የጭራቅ አሕመድ ክራንቻወች (ማለትም ረዝመው ያገጠጡት ሁለቱ የፊት ጥርሶቹ፣ canines ) ደመቀ መኮንን እና ተመስገን ጡሩነህ ናቸው፡፡ በመሆናቸውም፣ ጭራቅ አሕመድ የአማራን ሕዝብ መብላት አቅቶት፣ ርቦት እጁን እንዲሰጥ ብአዴናዊ ጥርሶቹን ማርገፍ ብቻ በቂ ነው፡፡ በተለይም ደግሞ መንጋጋወቹን እነ ግርማ የሽጥላን እና ሰማ ጡሩነህን መንቀል፣ ክራንቻወቹን ደመቀ መኮንን እና ተመስገን ጡሩነህን ደግሞ መመንገል የግድ ነው፡፡
የቀበሌው የደመላሽ ፋኖ ዋና ሚና መሆን ያለበትም በየራሱ ቀበሌ ላይ የተተከሉትን የጭራቅ አሕመድን ብአዴናዊ ጥርሶች ማወላለቅ ነው፡፡ የአማራ ሕዝብ የጭራቅ አሕመድን ጥርሶች በማወላለቅ ጭራቅ አሕመድን ጨርቅ ካደረገ፣ ወያኔና ኦነግ እዳቸው ገብስ ነው፡፡
መስፍን አረጋ
mesfin.arega@gmail.com