>

የፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴን መታሰር አስመልክቶ ከሸዋ ፋኖ የተሰጠ የአጋርነት መግለጫ!!

የፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴን መታሰር አስመልክቶ ከሸዋ ፋኖ የተሰጠ የአጋርነት መግለጫ!!

(መስከረም 11/2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ)

የአማራ ህዝብ  በአራቱም አቅጣጫ ተከ*ቦ ከምን ጊዜውም በላይ የጀግኖች ልጆቹን እና ፋኖዎች አንድነት በሚያስፈልግበት በዚህ ወሰኝ ሰዓት ስርዓት በተቀያየረ ቁጥር ስሙን እየቀየረ የአማራን ህዝብ ጥያቄ ሲ*ያ*ፍን እና ጥያቄውን ያነሱትን አማሮች በስርዓቱ ሲያ*ሳድ*ድ አለፍ ሲልም ሲያ*ስገ*ድል የነበረው ቀንደኛ የአማራ ጠ*ላት ብዓዴን ዛሬም እንደትላንቱ የአማራን ህዝብ ጀግና የፋኖ መሪ አርበኛ ዘመነ ካሴን ገዢው ስርዓት ባቀነባበረው እርቅ በሚል ሴ*ራ እና  ለህዝባችን እንታመናለን በአማራ ህዝብ ጥቅም አንደራደርም በሚሉ ተቆርቋሪ መሳይ ፖለቲከኞች በኩል እርቅ በሚል ሰበብ ዘመነን በማባበል በዛሬው እለት እን*ዲ*ታፈን አርገውታል ስለሆነም ይህን አስመልክቶ የሸዋ ፋኖ የሚከተለውን መግለጫ አውጥቷል።

1) ባሁኑ ሰዓት ህዝባዊ ቅቡልነት ያላቸውን የህዝብ ልጆች በማ*ሳደ*ድ ላይ የሚገኘው አማራ ጠ*ሉ ስርዓት ከዚህ ድርጊቱ እንዲታቀብ።

2) አርበኛ ዘመነ ካሴ  ጥያቄው የአማራ ህዝብ የነፃነት ጥያቄ ሆኖ ሳለ ይህን እየተረዱ አማራ ነን የሚሉ አካላት የዘመነ ካሴን መታሰር እንደ ትልቅ ድል የሚቆጥሩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ እናሳስባለን። ያ ሳይሆን ቢቀር ፍፁም ወንድማማችነታችን የተቋረጠ መሆኑን እናሳውቃለን።

3) እናስታርቃለን እናደራድራለን ብላችሁ ዘመነን ያሳሰራችሁ አካላት እውነታውን ለህዝቡ እንድታሳውቁ እናሳስባለን።

4) የአማራ ህዝብ እስካሁን ከምንም በላይ ዋ*ጋ እንዲከፍል እና አሁንም ላለው ምስ*ቅል*ቅል ተጠያቂው አካል ውክልና ሳይሰጠው ራሱን የአማራ ተወካይ ነኝ የሚለው ብዓዴን መራሹ አካል መሆኑ ታውቆ ይህን አካል ታግሎ ለመ*ጣ*ል ራሱን እንዲያዘጋጅ እናሳስባለን።

የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን አደጋ  በተባበረ  ክንድ ይቀለብሳል

ሸዋ ፋኖ

መስከረም 11-01 -2015 ዓ.ም

Filed in: Amharic