>

ግዕዝ እንደ ቁቤ አይደለም!  (አቻምየለህ ታምሩ)

ግዕዝ እንደ ቁቤ አይደለም!

አቻምየለህ ታምሩ

ኦነጋውያን ሰው ሁሉ እንደሚያንጋጉት መንጋ የሚሉትን ሁሉ ያላ አንዳች ጥርጣሬ የሚቀበልና የሚሰለቅጥ እንዲሁም ለማሰብ ፍቃደኛ ያልሆነ ይመስላቸዋል። ከሰሞኑ እንደተከታተልነው ያሉትን ሁሉ ለሚቀበላቸው መንጋ የጥቁር ሕዝብ ፊደል የሆነው የኢትዮጵያ ፊደል የአርመንን ፊደል ተውሶ እንደሚጽፍ ደርተው የተማሪዎች መማሪያ መጽሐፍ አዘጋጅተዋል። እውነቱ ግን በተቃራኒው ነው።

ከታች ከታተመው የአርመን ተወላጅ የታሪክ ተመራማሪ ከሆኑት ከRubina Sevadjian ጥናት እንደምናዳምጠው የኢትዮጵያ ፊደል ወይንም የግዕዝ አጻጻፍ የአርመን አጻጻፍ ከመፈጠሩ መቶ አመታት በፊት የነበረ እንጂ ኦነጋውያን ለኦሮሞ እንደሚዋሹት ግዕዝ ከአርመን ፊደል ወርሶ መጻፍ አልጀመረም። እንዴውም እኒህ የአርመን ተወላጅ የታሪክ ተመራማሪ እንደሚነግሩን የአርመን አጻጻፍ ከኢትዮጵያ ፊደል የተወረሰ ሊሆን እንደሚችል ነው።

 

ኦነጋውያን ግዕዝን ከአርመን ፊደል ተውሶ እንደምፈጽ ተረት መፍጠር የፈለጉት አፍሪካ በሙሉ ከቅኝ ግዛት በተላቀቀበት ዘመን እነሱ ወደ ቅኝ ግዛት ተመልሰው የቅኝ ገዢ ፊደል በመውረስ ቁቤ የሚሉትን የቅኝ ግዛት አጻጻፍ በኦሮሞ ትውልድ ላይ መጫናቸው ተቃውሞ እየተነሳበት ስለሆነ ለዚህ ማጣፊያ ፍለጋ ነው። ሆኖም ግን ግዕዝ ቁቤ አይደለም፤ ወደ ቅኝ ግዛት ተመልሶ በቅኝ ግዛት ፊደል በላቲን አይጽፍም!

https://www.facebook.com/100000358765743/posts/pfbid02BqCFgprZfDwrJPZco6bV4wGk3oj8CPGW2ZwwnM9k4i7uCw5327kGaP9MqDUpiuEKl/

Here is the transcription of what she said;

“… we can safely say that Geez precedes the Armenian by hundreds of years… Mesrop Mashtots, the man who invented the Armenian alphabet in 405, is likely to have seen Geez and been influenced by it.”

Filed in: Amharic