የማዲንጎ አፈወርቅ እረፍት…
ዘመድኩን በቀለ
“…ትናንት ምሽት ሲዘፍን እንዳመሸ እና በሰላምም ወደ ቤቱ እንደሄደ ነው የተነገረው። መሸ ነገ ዛሬ ጠዋት ላይ የህመም ስሜት ተሰምቶት ራሱ መኪናውን እያሽከረከረ ወደ በአዲሱ ክፍለ ከተማ ለሚ ኩራ ጤና ጣቢያ ለምርመራ ሄደ። ቆይቶ አስከሬኑን ውሰዱት ተባለ። በቃ የሆነው ይሄ ነው።
“…ማዲንጎ በሰውነቱ ላይ ምንም ዓይነት አካላዊ ጉዳት እንዳልነበረበት ጓደኞቹ በተገኙበት ቢረጋገጥም የአዲስ አበባ ፖሊስ ግን አስክሬኑን ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ሆስፒታል መላኩን ተሰምቷል።
“…የዐማራ የሆኑቱ አርቲስቶች በሙሉ ኢትዮጵያ ውስጥ በተመሳሳይ መልኩ ሲሞቱ የኖሩት። ኢዮብ መኮንን ልቤን አለ ሞተ። ታምራት ደስታ ልክ እንደ ማዲንጎ መኪናውን እያሽከረከረ ክሊኒክ ሄደ እዚያው ሞተ። ሌሎቹንም አርቲስቶች አሟሟታቸውን ተመሳሳይ ነው። ባለፈው ዓመት የሞተው የሰው ለሰው ድራማ አዘጋጅ የነበረው አርቲስት መስፍን ጌታቸው የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የልብ ጓደኛ ነበር። ዐማሮች መታረዳቸውን በይፋ መቃወም ጀምሮም ነበር። ከዚያ ኮረና መጣ ተባለ። አጣድፈው ካምፕ አስገቡት። ሞተ። አበቃ።
“…ጥላሁን ገሰሰ፣ ፍቃዱ ተክለማርያም፣ ታምራት ሞላ፣ ኃብተ ሚካኤል ደምሴ፣ ማናለሞሽ ዲቦ፣ አለባቸው ተካ፣ ሱራፌል ደምሴ፣ ወዘተ ጨምሩበት። አብዛኞቹ ቆረጠኝ፣ ሆዴ ተቃጠለ እንዳሉ ነው የሞቱት። ከዘመነ ህወሓት ጀምሮ የዐማራ ልሂቃን የሚባሉቱ አካላት በሙሉ የሚያጸዳ ገዳይ ቡድን በኢትዮጵያ እንዳለ ግራ ትከሻዬን ይሸክከኛል። ሃጫሉም ቢሆን መኪና ውስጥ ከሴቷ ጋር እንዳለ በጥይት ተገደለ ነው የተባልነው። አስከሬኑ ላይ ግን ደምም ውግም አልታየም ተብሏል። ፖለቲካውን ግን ሠሩበት። በሃጩሉ ሞት ምክንያት በኦሮሚያ ይኖሩ የነበሩ ዐማሮችና ኦርቶዶክሳውያን እንዲጸዱ ተደረገ። ከፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ ጀምረህ ቁጠር፣ ዶር አምባቸው፣ ጀነራል አሳምነው፣ አስቻለው ደሴ ልቅም ተደርገው ነው የጸዱት። የእግዜር ሞት የሞቱ የሉም እያልኩ ግን አይደለም። ሞልተዋል። በተለይ የአደባባይ ሰዎች በሙሉ ግን በአብዛኛው የጸዱ ይመስለኛል። አረጋውያኑ እነ ኦቦይ ስብሃት ነጋ፣ እነ ቅዱሳን ነጋ፣ ተቀምጠው እኮ ነው ሌላው ጡሩጉ የሚደረገው። ለመግደል የራሩላቸውን ጥቂቶችን በልጅነታቸው ጡረታ አውጥተዋቸዋል። ገሚሱን በመኪና አደጋ ሽባ አድርገው ዊልቸር ላይ አውለዋቸዋል።
“…ከኢንጂነር ቅጣው እጅጉ ጀምሮ በውጭ ሃገር የተከበሩ ሆነው ኖረው የተቀጠፉ አሉ። ወጋኝ ብለው በዚያው የተሸኙ። ልንዘረዝራቸው እንችላለን። በየ ዩኒቨርስቲው ስንትና ስንት ምጡቅ አዕምሮ ያላቸው የዐማራ ልጆች ናቸው የተገደሉት። ከፎቅ ወርውረው፣ በጩቤ፣ በጥይት ያጸዱአቸውን ቤት ይቁጠረው። የማያልቅ ጉደኛ ሆኖ ነው እንጂ ስንቱ ዐማራ ነው የጸዳው። አይደለም በህወሓት በኦህዴድ በኦነግና በብአዴን በግንቦት 7 ኤርትራ በረሃ የተረሸነው ዐማራን ቤት ይቁጠረው። ግንቦት 7 ኢዜማ ሆኖ ከመጣ በኋላ እንኳ ብርሃኑ ነጋ ሚንስትር፣ አንዳርጋቸው ጽጌ የሸአቢያ ደላላ ሆነው ሲከብሩ ስንቱ የዋሕ ዐማራና ኦርቶዶክስ ነው በኢዜማ ስም የጸዳው። የደብረ ዘይቱ ልጅማ ያንገበግበኛል። ለልቅሶ፣ ለሽርሽር፣ ዘመድ ጥየቃ ኢትዮጵያ መጥተው የተወገዱትን ቤት ይቁጠረው። መኪና ገጭቷቸው፣ ወዘተረፈ እየተባሉ ማለት ነው። ጋዜጠኛ ደምስ መኮንን በብዕር ስሙ (ቬሮኒካ) ከ30 ዓመት በኋላ ለውጥ መጣ ብሎ ገባ። በብዕር ስሙ ሲያቆስላቸው የኖሩት አሰፍስፈው ጠበቁት። ከሆነ ሰው ጋር ሻይ ጠጥቶ ወደ ቤቱ ገባ። ደምሲተፋ አመሸ። ሆስፒታል ገባ። አጣድፈው አፀዱት። ሳይመረመር አካልበው ቀበሩት። የዐማራ ድምጽ ሬድዮም ተዘጋ። የቬሮኒካም ብዕር አብሮ ተቀበረ።
“…ተጠንቀቁ ማለት አይቻልም። ከምንስ ትጠነቀቃላችሁ። ነገር ግን አጥብቃችሁ ጸልዩ። ሃይማኖተኛም ሁኑ። እነ ጌታቸው ረዳ፣ እነ ጀነራል ጻድቃን የዐማራን ኤሊት እንበቀለዋለን የሚሉት የዐማራ ኤሊት ማለት ዘፋኙንም፣ ዶክተሩንም፣ ኢንጂነሩንም፣ ቄሱንም፣ ሼኩንም፣ አትሌቱንም፣ ወዘተርፈውን ሁሉ መሆኑን ማወቅ አለብህ። ከህወሓት ጋር ሠርተህ ብታመልጥ፣ ኦህዴድኦነግ ሲመጣ ያርድሃል። ኢንጂነር ስመኘው በቀለን ተመልከት። አርቲስት ሆነው ዐማራና ኦርቶዶክስ በመሆናቸው ማስታወቂያ መሥራት፣ ፊልም መሥራት፣ ቲያትር መሥራት እየቻሉ የተገፉትን፣ ለማኝ የኔቢጤ የተደረጉትን አስታውሱ። ነገር ግን በእምነታቸው ጸንተው ያሸነፉ፣ የተጠበቁ፣ የተከለሉትንም አስታውሱ። ሃሺሻም፣ ጠጪ፣ ሰካራም የተደረጉትንም አስታውሱ። ሴት ባየህ ቁጥር ለሃጭህን አታዝረብርብ፣ ቀሚስ ስተከተል አትኑር። ተረጋጋ፣ ሰብሰብ በል። ደግሞ ልጋብዝህ ካለ ጋር ሁሉ ለሆድህ ብለህ ዊኒጥ ዊኒጥ ብለህ አትጣድ። ያገኛችሁትን ሁሉ አግበስብሳችሁም አትብሉ። አትጠጡም። ቆጠብ በሉ። በአንድ ሴት ፅኑ። እንደፌንጣ ከዚህ እዚያ አትዝለሉ። የሞት መድኃኒቱ ልጅ ነውና በጊዜ ተሰብስበህ ዘርህን ተካ። ለዚህ ደግሞ ሃይማኖት ከሌለህ ከባድ ነው። ከራበህ ቲማቲም ከትፈህ ብላ። ብቻህን ሆስፒታል አትሂድ። ያውም ዐማራ ሆነህ ለሚኩራ… !! ኧረ በፈጠረህ።
“…ለምንድነው ግን የባጥ የቆጡን የምቀባጥረው? ሃኣ? ምንነክቶኝ ነው በማርያም። ምንአለ እንደሌላው ሁሉ እንደ ዐቢይ አህመድ ሁላ “አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ በማረፉ የተሰማኝ ኀዘን ከባድ ነው። ለሀገሩ በአጭር እድሜው ብዙ የሠራ ከያኒ ነው። ሀገር በተደፈረች ጊዜ ሕመሙን እየቻለ ግንባር ተገኝቶ ሠራዊቱን አጀግኗል። ሠልጣኞችን አበርትቷል። ነፍሱ በሰላም ትረፍ።” ብዬ የረጅም ጊዜ ህመም እንደነበረበት ገልጬ ነፍስ ይማር ብዬ የማላልፈው? ምንአይነት ጉድ ነው።