>

ከ ኦሮሞ Oligarchy ጋር ላስተዋውቃችሁ...!!! (ዮሴፍ የየሱስወርቅ)

ከ ኦሮሞ Oligarchy ጋር ላስተዋውቃችሁ…!!!

ዮሴፍ የየሱስወርቅ

መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት የ “ዳላር”  ምንዛሬ በአንድ ጊዜ

በስምንት ብር እንዲጨምር ብሄራዊ ባንክን አዘዘ::

በጎን  ለሚስቱ  ና  ለቅርብ ሰዎቹ  ትእዛዙ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት የቻሉትን ያህል “ዳላር” ከባንክ እንዲያወጡ መንገዱን አመቻቸላቸው::

አዜብ መስፍንና ወዳጆቹ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር የውጭ ምንዛሬ ማውጣታቸው ከተረጋገጠ በኃላ ብሄራዊ ባንክ የታዘዘውን የምንዛሬ ማስተካከያ አወጀ!!

እነ አዜብ መስፍንና ወዳጆቹ በርካሽ ከመንግስት ያወጡትን “ዳላር” ምንም አይነት ግብይት ሳይፈፅሙ ለባንኩ በመመለስ በአንድ ጨረቃ ቢጠሯቸው የማይሰሙ ዲታ ከበርቴዎች ሆኑ!!!

****

ኢህአዴግ ቁጥር 2 ይሄንን ጨዋታ ሊደግመው እየተሯሯጠ ነው:

“ዳላር” እጅግ  በሚያስደነግጥ ፍጥነት ሶስት ወር ባልሞላ ጊዜ መቶ ብር ደርሷል ምንዛሬው!!!

አብይ አህመድና  ተረኞቹ ኦህዴዶች እነ አባ ዱላ ገመዳ ታከለ ኡማ አዳነች አቤቤና ወዳጆቻቸው በአገር ቤት ያለውንም በውጭ የሚገኘውንም hard currency  በራሳቸውና በወኪሎቻቸው አማካኝነት ተቆጣጥረውታል::

የጋንዲ የብሄራዊ ቲያትር የውጭ ምንዛሬ ስራ ሳይቀር በተረኞቹ ተወሯል::በውጭ ሃገር ገንዘብ ላኪነቱን ስራ “ኬኛ” ሆኗል::

አሁን የቀረው አንድ ቀጭን ትእዛዝ ብቻ ነው!!

ብሄራዊ ባንክ ሰሞኑን “የውጭ ምንዛሬ ማስተካከያ” ያውጃል:

በብርሃን ፍጥነት እነ ታከለ ኡማን  አባዱላ ገመዳን ቢሊየነር የሚያደርገው ፕሮጄክት በስኬት ይጠናቀቃል::

ለጨዋታው ድምቀት ኢትዮጵያ ስንዴ ወደ ውጭ ላከች የሚል ዜና ይመረቅልህና  የራስህን ስንዴ ጆንያ ቀይረው

ከዩክሬን የተገዛ ብለው ያቀርቡልሃል!!

አቅሙ ካለህ ትገዛና ዳቦ ትበላ ይሆናል:: አለዚያ ብዙም አትቸገር በቴሌቪዥን የብልፅግና ስኬትና ኢትዮጵያ ስንዴን ለውጭ ገበያ ማቅረቧ  ይተረክልሃል::

ብልፅግና ይፋፋምባችሁ!

Filed in: Amharic