>

....አርቲስት ዳኜ ዋለ ላይ የግድያ ሙከራ ተደረገበት! (ወንድወሰን ተክሉ)

በአማራ ላይ የተከፈተ ታላቅ መንግስታዊ የሽብር ዘመቻ አካል – አርቲስት ዳኜ ዋለ ላይ የግድያ ሙከራ ተደረገበት…!

ወንድወሰን ተክሉ


 ማክሰኞ ማምሻውን አርቲስት ዳኜ ዋለ (የጨነቀለት) ከሟቹ አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ቤት አምሽቶ  ወደ ቤቱ በመሔድ ላይ ሳለ  ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ከባድ ድብደባ ደርሶበት የተጎዳ መሆኑን ማወቅ ተችሏል።

ጥቃቱ የተፈጸመበት ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ላይ ሲሆን ደብዳቢዎቹም የግል ስልኩ ጭምር በመውሰድ  ሳይዘጉ ክፍት አድርገው እየተጠቀሙበት (እየመረጁበት) እንዳለ ለአርቲስቱ ቅርበት ያላቸው ወዳጆቹና መደብደቡን ሰምተው እየደወሉለት ካሉ ወገኖች በኩል ማወቅ ተችሏል።

አርቲስት ዳኜ ዋለ ላይ ጥቃቱን ያደረሱት ሰዎች ማንነት አይታወቅም ቢባልም ከደረሰበት ጥቃት አንጻር ጥቃቱን አድራሾች ማንነት መገመት አያዳግትም።  አርቲስቱ ከሟች ማዲንጎ ቤት ሀዘን ደርሶ ምሽት ላይ ወደ ቤቱ እየተጔዘ ባለበት ሁኔታ ከፊት እና ከኋላ በፓትሮል መኪና መንገድ ዘግተው በማስቆም በመኪናው ውስጥ  በሰደፍ እና በተለያየ ነገር በመደብደብ በእጁ ላይ ያለውን ሁለት ስልክና  ሌሎች ፋይሎቹን ጭምር በመዝረፍ ሳሪስ አካባቢ  ከነመኪናው ጥለውት መሄዳቸውን ነው የአርቲስቱ ወዳጅ የገለጸው።

ይህንን ድብደባና ዘረፋ ከፈጸሙ  በኋላ ወደ አርቲስቱ ስልክ ሲደወል ስልኩ የሚጠራ ሆኖ ሳለ የማይነሳ መሆኑን ለአርቲስቱ የደወሉለት ወዳጆች ገልጸዋል።

ጋሻ መልቲ ሚዲያ በአርቲስት ዳኜ ዋለ ላይ የተፈጸመው ተራ የስርቆት ተግባር ወይም ተራ ድብደባ ነው ብሎ በፍጹም አያምንም።

አርቲስቱ በዘንዶው ጸረ አማራ አቢይ አህመድ ቡድን ከወራቶች በፊት በአማራ ላይ በተከፈተው መጠነ ሰፊ መንግስታዊ የሽብር ዘመቻ ወቅት ታስሮ የተፈታና በስርቱ ጥርስ ውስጥ ከገቡት የአማራ ልጆች ውስጥ አንዱ መሆኑን በመገንዘብ የዛሬውን ጥቃት ተራ የስርቆት ተግባር የማይለውና በአንጻሩም በአማራ ላይ የተከፈተው መጠነ ሰፊ ዘመቻ አካል ብሎ የሚገልጸው መንግስታዊ ጥቃት መሆኑን ነው መረዳት የሚቻለን።

በተለይ ደግሞ ጥቃቱ ከሟቹ አርቲስት ማዲንጎ ቤት ሲወጣ ተጠብቆ የመፈጸሙ ጉዳይ በአርቲስት ማዲንጎ ግድያ ላይ እጁ ያለበት ቡድን የአርቲስት ዳኜ ዋለ በስፍራው ፈጥኖ መድረስ  ያበሳጨውና  መል እክት ለማስተላለፍ የፈለገ ነው ብሎ መገመት ይቻላል።

አርቲስት ዳኜ ዋለ ባለፈው ሳምንት ክህደት ተፈጽሞበት በመታፈን የታሰረውን አርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴን እስር ቤት ድረስ ፈጥኖ በመሄድ ከጠየቁት ውስጥ ግንባር ቀደም የአማራ ልጅ ነው!!!

አቢይ መራሹ የብልጽግና ገዳይ ጨፍጫፊና አስጨፍጫፊ ቡድን በአማራ ሕዝብ ጫንቃ ላይ በተፈናጠጠው  ባንዳው የብአዴን ቡድን በመጠቀም  በአማራ ፋኖ በአማራ ጋዜጠኞችና በአማራ አንቂና አደራጆች ላይ መጠነ ሰፊ ዘመቻ የከፈተ ሲሆን በተለይ በፋኖዎቻችን ላይ በከፈተው ዘመቻ የአማራ ሕዝባዊ ኋይል ፋኖ መስራችና መሪን አርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴን በእንደራደር ሰበብ ጠርቶና ክዶ አፍኖ በማሰር በባህርዳር ሳባታሚ ማረሚያ ቤት ባሰረው ማግስት በመ/አ ማስረሻ ሰጤና ባልደረቦቹ ላይ አፋኝ ቡድን በማሰማራት  – እንዲሁም በምስራቅ አማራ ፋኖ አመራር ፋኖ እስራኤል ላይ ገዳይ የሪፐብሊካን ጋርድ በመላክ እያሳደደ ያለ ቡድን መሆኑ ይታወቃል።

ይህንን በመላው አማራ ፋኖ እና አደረጃጀት ላይ የተከፈተን ጸረ አማራ ዘመቻን መክቶ ለማክሸፍ አማራው ሁሉ የቅድሚያዎች ሁሉ ቅድሚያ ዘመቻን በብአዴን ላይ አድርጎ በመታገል ለነገዳዊ ህልውናው መቀጠል የበኩሉን ድርሻና ሚና እንዲወጣ የሚል ጥሪ መተላለፉና በአንዳንድ የአማራ ከተሞች ሕዝባዊ አመጽ መነሳቱ ይታወቃል።

ብአዴን በአዛዡ አቢይ እየተመራ የአማራ አይን የሆኑትን እየለቀመ ከመጨረሱ በፊት ልናስቆመው ይገባል!!!!

Filed in: Amharic