>

የፈለገ ዮርዳኖስ ት/ቤት ረብሻ ምክንያቱ…! (ከዘመድኩን በቀለ)

የፈለገ ዮርዳኖስ ት/ቤት ረብሻ ምክንያቱ…!

ከዘመድኩን በቀለ

“…ትናንት ከሰዓት በሰንደቅ ዓላማው ብረት አጠገብ ጉድጓድ ሲቆፈር ተማሪዎች ያያሉ። እናም እንደከዚህ ቀደሙ የኦሮሚያን ሰንደቅ ዓላማና የኦሮሚያን መዝሙር በግድ ሊያዘምሯቸው እንደሆነም ይረዳሉ ተማሪዎቹ። ምንም አላሉም። ጮጋ ብለው ወደቤታቸው ይሄዳሉ።

“…መሸ… ነጋም ሁለተኛ ቀን ሆነ። ዛሬ ጥቅምት 2/2015 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቅዱስ ቂርቆስ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ በሚገኘው የፈለገ ዮርዳኖስ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓለማ በኢትዮጵያ መዝሙር አጅበው ዘምረው ከሰቀሉ በኋላ “ሌላ አንድ አዲስ ባንዲራና አዲስ መዝሙር ይቀራችኋል” ተብሎ በአስተማሪዎቻቸው ተነግሮ የኦሮሚያ ክልል ባንዲራ በኦሮምኛ መዝሙር ታጅቦ በአዲስ አበባ ልጆች እንዲሰቀል ይታዘዛል። ተማሪዎቹ ድርጊቱን ቢቃወሙም የህወሓት የማደጎ ልጅ የሕገ መንግሥቷም አስከባሪ ኦህዴድኦነግ መስሚያው ጥጥ ነውና በድፍረት ሰቀለው።

“…ተማሪዎቹ መልሰው ተቃወሙ። ትምህርት ሲጀመር የክፍለ ከተማው አመራሮች መጥተው የሰቀሉት የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ነው። እኛ ኦሮሞ አይደለንም። ብዙ ብሔር ብሔረሰቦች ነን። እንዴት ከዚህ ሁሉ ብሔር የአንድ የኦሮሞ ብቻ ባንዲራ እና መዝሙር ተልይቶ ይሰቀል፣ ይዘመርም ይባላል? እንዴትስ “እኛ የኦሮሞ ልጆች በደማችን ያገኘነውን ሥልጣን ምናምን የሚል የፓርቲ መዝሙር ሌሎቻችን በግድ ዘምሩ እንባላለን ይላሉ ህፃናቱ። አንድ ብሔራዊ መዝሙር፣ አንድ ሰንደቅ ለእኛ በቂያችን ነው ብለው ተቃወሙ። ህፃናቱ…!!

“…የህወሓት ጥጋብን ያስተነፈሰው ጊዜ ነው። ቡን አድርጎ ያጠፋትም ጊዜ ነው። እንደ ጊዜ እኮ ከምር ጀግና የለም። የነገ ባይታወቅም ለዛሬ ጉዳት የደረሰበት ንብረትም፣ ተማሪም፣ ፎሊስም የለም።

Filed in: Amharic