>

የትኛው ሰልፍ ላይ ነን...?  (ክርስቲያን ታደለ)

የትኛው ሰልፍ ላይ ነን…?

ክርስቲያን ታደለ


*… የጋራ ግብ የሌለው እንዴት በጋራ ሊቆም ይችላል? ይኼ ከባድ ነው። ለምንድን ነው የምታገለው? ምን ለማሳካት ነው የምታገለው? የምታገልለት ሕልም የማን ሕልም ነው? ሕልሙ እንዲሳካስ የኔ ድርሻ ምንድን ነው?  የሚሉ ቀላል የሚመስሉ ግን ደግሞ የግድ ራሳችንን ጠይቀን የግድ ምላሽ ልናገኝባቸው የሚገቡ መሰረታዊ ጥያቄዎች ናቸው።

ውስጣዊ አንድነትን ማጠናከር ማለት በውሸት መስማማት ማለት አይደለም። ይልቁንም አንድ በሚያደርጉን የጋራ ጉዳዮች ላይ የበለጠ ትኩረት አድርጎ፤ ጊዜ የሚሰጡ ጉዳዮችን በይደር እያቆዩ ለጋራ ግብ በአንድነት መቆም ማለት ነው። ለምሳሌ የቱንም ያህል የአቀራረብና ታክቲክ ልዩነት ቢኖር በሕዝብ ደኅንነትና የአገር አንድነት ላይ የግድ አንድ ልንሆን ይገባል። ፉክክራችን፣ መተጋገላችን፣…ሁሉ፥ አገርና ሕዝብን የበለጠ እጠቅማለሁ በሚል እንጂ በሌላ ሊሆን አይገባም።

የጋራ ግብ የሌለው እንዴት በጋራ ሊቆም ይችላል? ይኼ ከባድ ነው። ለምንድን ነው የምታገለው? ምን ለማሳካት ነው የምታገለው? የምታገልለት ሕልም የማን ሕልም ነው? ሕልሙ እንዲሳካስ የኔ ድርሻ ምንድን ነው?  የሚሉ ቀላል የሚመስሉ ግን ደግሞ የግድ ራሳችንን ጠይቀን የግድ ምላሽ ልናገኝባቸው የሚገቡ መሰረታዊ ጥያቄዎች ናቸው። ተመሳሳይ ምላሾች ሳይኖሩን በተመሳሳይ ሰልፍ ውስጥ ከተገኘን ትርፉ መጓተት ነው። ድካም ነው። መቋጫውም ሽንፈትና ውድቀት ነው። አብሮ ለመውደቅ አብሮ አይቆምም። በመሰል ሰልፍ ውስጥ የጋራ ቅዠት እንጂ የጋራ ሕልም ብሎ ነገር አይኖርም። የትኛው ሰልፍ ላይ ነን?

Filed in: Amharic