>

የብልፅግና ኢትዮጰያ አሸነፈች ዲስኩርና የአማራ ፖለቲካ...! (ሞሀመድ ሀሰን)

የብልፅግና ኢትዮጰያ አሸነፈች ዲስኩርና የአማራ ፖለቲካ…!

ሞሀመድ ሀሰን


በትናንትናው እለት የብልፅግና ደጋፊዎች፣ ተደማሪ ፀሀፊዎችና አክቲቪስቶች መንግስታቸውን ምን ያክል የማያቁት እንደሆነና ላለፉት ሁለት አመታት ስለ ብልፅግና ስንነግራቸው የነበረውን ነገሮች ሁሉ ችላ በማለት ያለ ሂሳብና ሀሳብ የደረሰባቸውን ኪሳራ ሲያወራርዱ በአሽሙር ጭምር የታዘብንበት ወቅት ነበር። በአንዴ በጦርነት ነጋሪ፣ ከክተት፣መክትና አንክት ወደ ሰላም ሰባኪነት የተገለበጡበትን የብርሀን ፍጥነትም ያየንበት ቀን ነበር። የማንደግፈው የብልፅግና መንግስት ቀላል ተገማች መሆኑና እኛ ያወቅነውን ያህል እንኳ የብልፅግና መንግስት ደጋፊዎችና ተደማሪዎች የሚደግፉትን መንግስት ምንም ያለማወቃቸው ነገርም የትናንቱ አስቂኝ ነገር ሆኖ አልፏል። ብልፅግና ደጋፊዎቹን #Nomore ብሎ አስጀምሮ #Gameover ንም እንዲያክሉ አድርጎ በስተመጨረሻ ራሱ ብልፅግና #Havemore & #Hugmore my darling ተባብለው ከወያኔ ጋ ተቃቅፈው ተጨባብጠዋል። ደጋፊዉም ሀፍረቱን ውጦና ተከናንቦ የሰላም ዘማሪና የኢትዮጵያ አሸነፈች theatrical orchestra vocal band ሆኖ ብቅ ብሏል። ከነ “በሞኝ ቁመት፣ውሀ ይለኩበት” ሰፈር የተቀየረ ነገር የለም። የጥገኝነት መጨረሻው ይሄው ነው። ዛሬ ኢትዮጵያ አሸነፈችም ሆነ የሰላም ዋጋው ከፍ ያለ ነው አልክም፣ አላልክም ውሳኔው ያንተ አይደለም።

ወደ ቁም ነገሩ ስንመለስ:–

===============

The politics of the people of Amhara still continued to be unaccounted for anything except used as a ploy only to materialize the interest of the elite who always swear in the name of Ethiopia. ያም ሆኖ በዚህ ሁለት አመት ውስጥ የአማራ ፖለቶካ  ከ Ethiopia tradational political establishment የተለመደ ውዥንብር ራሱን ነፃ በማድረግ እንቅስቃሴ የገባበትንም ግብር አይተናል። አማራው ለፕሪቶሪያው ድርድር በብልፅግና በፍፁም ሊወከል እንደማይችል ግልፅ ተደርጎ የአማራ ልጆች በድርድሩ መወከል እንዳለባቸው ራሳቸውን በማዘጋጀት ወደፊት የመጡበት ሂደት ምን ያክል ህዝባችን ወድቆ ከነበረበት ሰመመን መንቃቱን ማሳያ ጅምር ነው። ለአሁን በድርድሩ ባለመካተታቸው የሚቀርቡ ብዙ ምክኒያቶች ሊኖሩ ቢችሉም የትግል መጀመሪያ ድምፅን ማሰማት ፍላጎትን ማሳወቅ ነው። የበለጠ ተደራጅቶ፣ተሰባስቦና መክሮ formidable force ለመሆን በቀጣይነት መሰራት ያለበት አጀንዳ ነው። ይህ ለወደፊት የአማራ ልጆች ከሚሰሩት ከብዙ ነገሮች አንዱና ጅማሮው ነው። ከዚያ ባለፈ ወጣቱ ፋኖ ለመሆን ያሳየው ተነሳሽነት ሌላኛው የወደፊት ተስፋችን ነው። ይሄን ከ trdatiinal politics የተደረገውን shift  ያስተዋለው ያለ አይመስልም በተለይ በገዢው ፓርቲ በኩል። ዛሬም አሻንጉሊቶችን በአማራ ህዝብ ራስ ላይ በመሾም በቀጣይነት አንገት አስደፍቶ ለመግዛት በተለመደው ስሌት ውስጥ መሆናቸውን የሚያሳብቁ ምልክቶች አሉ።

ሁሌም እንደምንለው የደርግ መውደቅ የአንድ ስርአትን መጠናቀቅና አዲስ ተስፋ ለሀገር ያበሰረውን ያክል ለአማራ ህዝብ ደሞ የመከራ ዘመን አጥቢያ ነበር። ዛሬም ከዚህ የተለየ ነገር አልተፈጠረም።

አማራ አሁንም: –

===========

> ለኢትዮጵያ ፖለቲካ የእንጀራ ልጅ መሆኑ እንደቀጠለ ለመሆኑ ኦቦ ሽመልስና ወ/ሮ አዳነች አበቤ ተደራድረው ኦሮሚያና አዲስ አበባ ወሰን እንደተጋፈፉ ባየንበት ሀገር አማራው በፖለቲካ ውሳኔ የተወሰደበትን መሬት በህይወት መስዋእትነት ማስመለስ ቢችልም ያን የሚያፀና መልስ እንኳ በግልፅ አልተሰጠውም!

> ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ለማሟያነት ብቻ (bench squad) የሚፈለግ እንጂ የፖለቲካው ዋና ተዋናይ (elite squad) ውስጥ እንደሌለ ግልፅ ሆኗል!

> አማራን በኢትዮጵያዊነቱ የሚፈልጉት ስልጣናች  አደጋ ላይ የወደቀ ሲመስላቸውና ከላያቸው ላይ የወደቀውን የፖለቲካ አደጋ እንደራ የእሳት እራት ነፍስ ራሱን በእሳቱ አስበልቶና ማገዶ ሆኖ ፖለቲካቸው  እስከሚስተካከል ብቻ ነው!

> ኢትዮጵያ ብታሸነፍ ከሌላው የበለጠ የሚጠቀመው ነገር ያለ ይመስል ባታሸንፍ ከሌላው የበለጠ የሚጎዳው ነገር ያለ ይመስለ ኢትዮጵያን የፍርሀቱ መነሻ አድርጎ የማቅረብ ፖለቲካው እንደቀጠለ ነው!

> በአማራነት ከመቆም ውጭ ያለው ነገር በሙሉ ሀሳብ የሌለው ባዶ መሆኑን መረዳት እንዳለበት ትምህርት መውሰድ ያለበት ክስተት ሆኖ አልፏል!

> እከሌ ነኝ ብሎ በኢትዮጵያ ውስጥ የእከሌነቱን ጥቅምና ትሩፋት ሁሉም ሲያረጋግጥ አማራው ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ በኢትዮጵያ ውስጥ መዋለሉ ያተረፈለት ነገር የጦስ ዶሮ ከመሆን ያለፈ ፋይዳ የሌለው ነገር መሆኑን ነው!

=================

መፍትሄው: —

አማራ ሆነን ቆመን ትግላችንን ዳር እናደርሳለን!

Filed in: Amharic