>

ይብቃን! ለትግራይ ህዝብ የጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት (DW)

ይብቃን! ለትግራይ ህዝብ የጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት

DW


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ፤ በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል ትላንት በደቡብ አፍሪቃ የተደረሰዉን የሰላም ስምምነት አስመልክቶ ዛሬ ሐሙስ ጥቅምት 24 ቀን በአርባ ምንጭ ስቴድየም ባደረጉት ንግግር ለትግራይ ህዝብ ተከታዩን መልዕክት አስተላልፈዋል።

„የትግራይ ህዝብ በተደጋጋሚ ህዝባችን፤ ምድሩ ምድራችን እንደሆነ ስንገልፅ ቆይተናል። ተጠቃ ብለን በትልቅ ድል የልጅነት ወራራችንን ያጠፋን እና ትግራይን የተከለከልን መኖንችንን ታሪክ ይመሰክራል። ዛሬም ያ ልባችን በቦታዉ ነዉ ያለዉ። ለመላዉ ትግራይ ህዝብ ማስተላለፍ የምፈልገዉመልዕክት፤  አላስፈላጊ ጦርነት፤ አላስፈላጊ ጉዳት፤ አላስፈላጊ ኢትዮጵያን አጋልጦ የመስጠት ሂደት በዚህ ይብቃ። ብዙ መከፈል ያማይገባዉ ዋጋ ተከፍሏል። ብዙ ደም ፈሷል። ንብረት ወድሟል። ኢትዮጵያን የዓለም ሚዲያዎች፤ የሚያቁም የማያዉቁም፤ ትልቁም ትንሹም፤ በከፍተኛ ደረጃ አንጓጧታል። አስነስተዋታል። ይብቃን! ብዙ ጊዜ ከሰላም ድርድር በኃላ፤ ሸፍጦች፤ ተንኮሎች ፤ደባዎች ይታያሉ። የተከበርከዉ የትግራይ ህዝብ፤ እኛ ልባችንን ከፍተን፤ ሰላም ለማምጣት ዝግጁ ስለሆንን፤ ይሄንን የገባነዉን ቃል ለመጠበቅ፤ ከሌሎች ወንድም ህዝቦች ጋር፤ በጋራበመሆን፤  የበኩልህን ሚና እንድትወጣ። ተንኮል ክፋት ሸር፤ እዚህ ጋር እንዲበቃ። ጥቂቶች እየሸረቡ ኢትዮጵያዉያን ዳግም አደጋ ዉስጥ። ጦርነት ዉስጥ እያዳይገቡ ህዝባዊ ኢትዮጵያዊ፤ ዜግነታዊ ሚናችሁን እንድትወጡ፤ ለትግራይ ወንድሞች እና እህቶች በታላቅ ትህትና፤ አደራ ማለት እፈልጋለሁ“

አስተያየቶትን ይፃፉልን!

Filed in: Amharic