>

የወንበዴዎች አለቃ በርባንን ፈትታ ንጹሐ ባሕርይ ክርስቶስን የምትሰቅል ዓለም ታሳዝናለች... ! (በመጋቤ ሐዲስ ነቅዐ ጥበብ) 

የወንበዴዎች አለቃ በርባንን ፈትታ ንጹሐ ባሕርይ ክርስቶስን የምትሰቅል ዓለም ታሳዝናለች… !

 

በመጋቤ ሐዲስ ነቅዐ ጥበብ 


እኚህ በሥነ ምግባር የተከበሩ በአረጋዊነታቸው የሚፈሩ እና የሚታፈሩ አዛውንት ያለ በደላቸው እና ያለ ኃጢኣታቸው ስለእውነት የሚከፍሉትን የሕይወት ዋጋ እና የደም ተጋድሎ ሳስብ የዓለም ከንቱነት ይገርመኛል ። ዓለም ለንጹሐን እና ለእግዚአብሔር ሰዎችም ምንም ዓይነት ቦታ እንደሌላት የክርስቶስ ሕይወት መስታወት ሆኖ ያሳየኛል ።

ግዴላችሁም ባለ ጊዜዎች በዚህ ምድር ላይ የምንፈራው አካል እንኳን ባይኖር የሰማዩን ዳኛ እንፍራ ምክንያቱም በሰፈሩት ቁና መሰፈሩ አይቀርምና የጊዜ ጉዳይ እንጂ ዓለም እንደሆነች ወላዋይ ናት ዛሬም የሾመችውን ነገ መሻር ዛሬ ያከበረችውን ነገ ማዋረድ ዛሬ የሰቀለችውን ነገ መፈጥፈጥ አሳምራ ታውቅበታለች ።

👉ፍትሕ ለግፉዓን ድምፅ ለሆኑት አዛውንት !!!

            ጥቅምት ፳፱ ፪ ፪፻ ፲፭ ዓም

Filed in: Amharic