>

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ በመቶ ሺህ ብር ዋስትና ከእስር ተፈታ ...! (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ በመቶ ሺህ ብር ዋስትና ከእስር ተፈታ …!

 

ኢትዮጵያ ኢንሳይደ


ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ከሁለት ወራት እስር በኋላ ዛሬ አርብ ህዳር 2፤ 2015 በመቶ ሺህ ብር ዋስትና ከእስር ተፈታ። ጋዜጠኛው ከእስር የተፈታው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በስር ፍርድ ቤት ተፈቀደለትን ዋስትና ካጸና በኋላ ነው።

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በትላንትናው ዕለት በነበረው የችሎት ውሎ፤ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን ቢያጸናም ከዚህ በፊት ለጋዜጠኛው የተፈቀደለትን የ20 ሺህ ብር ዋስትና ወደ መቶ ሺህ ብር ከፍ አድርጎታል። ይግባኝ ሰሚ ችሎቱ በስር ፍርድ ቤት ተወስኖ ነበረውን የዋስትና ገንዘብ ወደ መቶ ሺህ ብር ያሳደገው የጋዜጠኛውን ገቢ ከጠየቀ በኋላ ነው።

ከትላንት በስቲያ ረቡዕ በጽህፈት ቤት በኩል በተካሄደው ችሎት፤ ጋዜጠኛ ጎበዜ በባለቤትነት ለሚያስተዳድረው “የአማራ ድምጽ” ለተሰኘው የዩቲዩብ መገናኛ ብዙሃን ንግድ ፈቃድ ሲያወጣ 500 ሺህ ብር ማስመዝገቡን ለችሎቱ ገልጾ ነበር። ጋዜጠኛ ጎበዜ፤ በአዲስ አበባ ገነት ሆቴል አቅራቢያ ከሚገኘው የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የተፈታው ዛሬ አስራ አንድ ሰዓት ከሩብ ገደማ መሆኑን ጠበቃው አዲሱ አልጋው ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

Filed in: Amharic