>

አስመሳይነትና አድርባይነት:- እንደ ኢዜማ እና እንደ ብአዴን  ማህበረሰባዊ ነቀርሳ እሴት...! (ሸንቁጥ አየለ)

አስመሳይነትና አድርባይነት:- እንደ ኢዜማ እና እንደ ብአዴን  ማህበረሰባዊ ነቀርሳ እሴት…!

 

ሸንቁጥ አየለ


የኦህዴድ/ኦነግ ብሄረተኝነት መሰረት አንባሪ፥ ሞሻሪ፥ አጠናካሪ እና አወዳሽ ብርሃኑ ነጋ/ኢዜማዊ እንዲሁም በአዴን ገልበጥ ብለዉ  የኦህዴድ/ኦነግን ብሄረተኝነትን ሲያወግዙ እንደማዬት አጸያፊ ነገር የለም፥፥

ኢትዮጵያዊ መቼም ከማስመሰል በሽታ ሳይድን እንደ አንድ እንደተከበረ ሀገር የሚቆም ህዝብ አይሆንም፥፥

ብርሃኑ ነጋ የኦህዴድ/ኦነግ የጎሳ ፖለቲካ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እና ኢትዮጵያ ላይ የበላይነቱን እንዲጨብጥ ቁልፍ ሚና የጨበጠ ሰዉ ነዉ፥፥ ከብአዴናዉያን ጋር በመተባበርም  የኦሮሞ ብሄረተኝነት ወደ ኢትዮጵያዊ ብሄረተኝነት እንዳያድግ ትልቅ እንቅፋት ፈጥሯል፥፥

ምክንያቱም ኦህዴድ/ኦነግ ሀገር እያወደመ ሳለ ብርሃኑ ነጋ/ኢዜማዉያን እና ብአዴናዉያን የኢትዮጵያን ሀገራዊ ዉድመት እንደ ሀገራዊ ብልጽግና  በመዉሰድ በአድርባይነትና በእስመሳይነት ኦነግ/ኦህዴድን አባልገዉታል፥፥

ከሁሉም በላይ አለ አገባብ በሚዳ ያበጠዉን የኦህዴድ/ኦነግ ብሄረተኝነት መለስ ብሎ ወደ ኢትዮጵያዊ ብሄረተኝነት እንዳያድግና ሀገር አቀፋዊ ሚና እንዳይኖረዉ በሽንገላ እና በማስመሰል አቀጭጨዉ በቂጡ አስቀምጠዉታል፥፥

ብርሃኑ ነጋ/ኢዜማዉያን እና ብአዴናዉያን በያንዳንዱ የኦህዴድ/ኦነግ ጥፋት ነገ ተጥያቂ ናቸዉ፥፥ ተከታዮቻቸዉ እና ደጋፊዎቻቸዉ ደግሞ ከብዙ ሃገራዊ ዉድመት ብሁዋላ የህሊና  እዳ  እና ቁስል ተሸክመዉ እራሳቸዉን ይወቅሳሉ ተብሎ ይጠበቃል፥፥

ሃሃሃሃ እዉነታዉ ግን መጨረሻ ላይ የሚሆነዉ ሌላ ነዉ፥፥ ብርሃኑ/ኢዜማዉያንም ሆኑ ብአዴናዉያን እና ደጋፊዎቻቸዉ  ልክ እንደትናንቱ ተከረባብተዉ ወንጀሉን የሰራዉ ኦነግ/ኦህዴድ ብቻ ነዉ ባይ ነዉ የሚሆኑት፥፥ ልክ ትናንት 27 አመታት ከወያኔ ጋር ተባብሮ ብዙ ወንጀል ሲሰራ የነበረዉ ብ አዴን ለአዲሱ ጌታዉ ለኦህዴድ/ኦነግ እየሰገደ ወያኔን መዉቀስ እንደያዘዉ፥፥ እንዲሁም የወያኔን ዲሞክራሲያዊነት ጅምር ሲያወድስ የነበረዉ እና 42 ፕሮፌሰሮች ሲባረሩ የህዉሃት ልዩ እና እንቁ ፕሮፌሰር ተደርጎ የተመረጠዉ ብርሃኑ ነጋ  ስልጣን ሲያንሰዉ ወያኔ ላይ ጣቱን መቀሰር  እንደ እንደጀመረዉ፥፥

እዉነትን እየደፈጠጡ አስመሳይነት እና አድር ባይነት  ተሸክሞ መሮጥ ማለት  አንድ ሀገር ፈጽሞ በግሩ እንዳይቆሞ  የሚያደርግ ታላቅ  ማህበረሰባዊ ነቀርሳ እሴት ነዉ፥፥

Filed in: Amharic