>

ስርአት አልበኛው የብልጽግና መንግስት....! (መርእድ እስጢፋኖስ)

ስርአት አልበኛው የብልጽግና መንግስት….!

መርእድ እስጢፋኖስ


Talk the talk ,walk the walk ይሉታል ፈረንጆቹ።ጠ/ሚ አብይ እያደረጉ ያሉት ህንን ነው።ሰውየው ወደ ከፍተኛ ስልጣን ከመምጣታቸው በፊት የገባቸው ነገር ቢኖር ለኢትዮጵያ ህዝብ “የሚፈልገውን መንገር እንጂ የሚፈልገውን ማድረግ “አስፈላጊ እንዳልሆነ ወስነዋል። በመሆኑም የምንፈልገውን እነገሩን የሚፈልጉትን እያደረጉ ቀጥለዋል።

በቅርቡ  የፓርላማ ውሎአቸው ሰውየው ምን ያህል ስርአት አልበኛ እና የወጣላቸው አምባገነን ብቻ ሳይሆኑ ደፋር ሙሰኛ መሆናቸውንም፡ ልብ ይሏል።

ያው ውሽታቸውን ለምደነዋል።በቴሊቪዥን መስኮት ብቅ ባሉ ቁጥር አንድ ጆንያ ውሽት ይዘውልን ይመጣሉ።አሁን ደግሞ ይባስ ብሎ ንቀታቸውና ስድባቸው ከአንድ መሪ የሚጠበቅ አልሆነም።

ዋልጌ መሪ በአፉ የሚጸዳዳ መሪ ኢትዮጵያ መንግስታዊ ስርአት ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ እንደ ጠ/ሚ አብይ አህመድ ገጥሟት የሚያውቅ አይመስለኝም።

የጫካ ሀውስ ነው የማሰራው 500ቢሊዮን ነው የሚፈጀው 49ብሊዮን ብለው ለምን ቀነሱብኝ ሲሉ ንዴታቸውን ሚስጥር አወጡብኝ ብለው በጠረጠሯቸው ዲፕሎማቶች ላይ ነስንሰዋል።መቼም political correctness የሚባል ነገር አልፈጠረባቸውም ።ምክንያቱም በአጋጣሚ እና በእድል መሪ የሆኑ ናቸው።ምናልባትም የናታቸው ከራማ ገና በሰባት አመታቸው የነግሯቸው ይዞላቸው ይሆናል። ነገር ግን አንድ መሪ አምስት አመት ሙሉ አገርን በሁለንተናዊ መልኩ እያወደመ እንዲቀጥል የተፈቀደለት መሆኑ ሳይበቃ እንዴት ሰዋዊ ስርአት simple decency ያጣል።

አስተዳደጋቸው በጣም መከራ የበዛበት ነው።ከዚያ የተነሳ ነው እንዳንል ቀደም ያሉ መሪዎቻችን ብዙም ከጠ/ሚ አብይ የተለየ አስተዳደግ ያደጉ አልነበሩም ።ግን ንግግራቸው ግብረገባዊ ነበረ ማለት ይቻላል።ቆጣ ብለው ከተናገሩም ከአውዱ አይወጡም የአብይ አህመድ ግን “ሁዱ ሲራይና !”ስድብ እስከመቼ።

በአሁኑ ፓርላማ ፦ሶስት ነገር ታዝቢያለሁ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዙሪያ ስልጣን ከያዙበት ጊዜ ጀምሮ የውሽት ድርቶ ነው የሚያቀርቡት አንድም ቀን ትክክል ሆነው አያውቁም ።በምስራቅ አፍሪካ ግዙፉ ኢኮኖሚ ኬንያ ነች ባአሁኑ ሰአት በሁለተኛ ደርጃም የምትቀመጠው ሩዋንዳ ናት።ቀደም ባሉ ትንበያዎች መስረት ግን ሶዎስተኛውን ቦታ ትይዛለች ይህም በ2021 ተተደረገው የኢኮኖሚ 6.7%ፕሮጄክሽን ነው።ስለዚህ  አሁን ያለውን አያሳይም።

ስለጫካ ሀውስ፦ዲፕሎማቶችን ከላይ ሆኜ ስለማያቸው ፈርተው ነው።ይሄ የማይሆን ጀግንነት ከርካሽ አባባል ጋር ተሳፍቶ የተነገረ ነው።”የዛሬ ወር አካባቢ ንዮርከር መጽሄት ጋር ጠ/ሚ ባደረጉት ኢንተርቪው “ለአሜሪካ ደሜን አፈሳለሁ “ማለታቸውን ማስታወሱ ቀላል ነው።ዲፕሎማቶችን ማስፈራት ቀርቶ ተገዥነታቸውን ያሳያል።29 ሚሊዮን ረሀብተኛ ባለበት ሀገር ይህን ያህል ግንዘብ ለጫካ ሀውስ ማውጣት ወቅትን ቦታን ሁኔታዎችን ያላገናዘበ ነው።

ሌላው ይሄ ብር ከየት ነው ምንጩ?

ምክንይቱ የተሰጠበት ምንድነው?

የገንዘብ ሚኒስቴር የማታውቀው ለምንድነው?

ይህንን ገንዘብ ታኮ የሚመጣ የፖለቲካ ኪሳራ ወይም ሂሳብ ማወራረድ ተጠያቂው ማነው።? ምክንያቱም “There is no free lunch in politics” ነጻ ምሳ ብሎ ነገር በፖለቲካ ውስጥ ስለሌለ።በነገርችን ላይ ይህ አይነት የመሪዎች ሙስና በእንግሊዘኛው embezzlement ይባላል። የቀድሞ የፈረንሳይ ፕሬዝዳን ኒኮላ ሳርኮዚ በዚህ ህግ መተላለፍ ዘብጥያች ወርደዋል።የቀድሞ የusa ፕሬዝዳንት ዶናልድ ጄ ትራም ቱባ ክስ ተመስርቶባቸዋል።የእስራኤሉ ጠ/ሚ ናትንያሁ በዚህ ክስ ከሚፈርድባቸው አንዱ እንደሆኑ ይጠበቃል።

ስለዚህ አብይ አህመድ በሙስናም አገሪቱን እየመሩ ነው።ግን talk the talk ,walk the walk ሆነ እና ነገሩ ራሳቸው ሌባ ራሳቸው ዘራፊ ራሳቸው ከህግ በላይ ሆነው “ጸረ ሙስና ኮምሽን ” እና “ጸረ ሌብነት ኮምሽን” በሳቸው በላይ ጠባቂነት አቋቋሙልን።ይህ ኮምሽን የሀገርቱ የበላይ ህግ ጠባቂ የሆነው የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት እንኳ አያወቀውም።

Filed in: Amharic