አሳይ መሲሁ የብልጽግና መንግስት የፖለቲካ ፍልስፍና፥- የነገደ ጉራጌ መከራ እንደማሳያ…!
ሸንቁጥ አየለ
— ከወያኔ የወረሰዉን የጎሳ ፖለቲካና የጎሳ ክልል ይዞ የቀጠለዉ ብልጽግና ከፖለቲካ ፍልስፍናዉ እስከ ታክቲካል የፖለቲካ እርምጃዉ ሀሳዊ መሲህ ሆኖ ቀጥሏል፥፥
— በአንድ በኩል ክልል ለጠየቁ ልዩ ልዩ ነገዶች እና ዞኖች አዳዲስ ክልሎችን እየፈጠረ ያድላል፥፥ አዳዲስ የጎሳ ክልሎችን ያቋቁማል፥፥
–ብልጽግና አዳዲስ ክልሎችን ሲፈጥርም ሆድ አዳሮቹ የብልጽግና ካድሬዎች በልልታ እየዘለሉ የብልጽግናን መንግስት ዲሞክራሲያዊነትን ያዉጃሉ፥፥ ይጮሃሉ፥፥
— በሌላ መልኩ ደግሞ ሌሎች ነገዶች እኛም ተገፍተናል፥ የራሳችን ክልል ሊኖረን ይገባል ብለዉ በሚጠይቁ ጊዜ ህዝቡን ይደበድባል ፥ ይሥራል ያፍናል፥ በሆድ አደር ካድሬዎቹም ክልል መጠየቅ ዘረኝነትና መከፋፈልን የሚጋብዝ ነዉ የሚል ፕሮፖጋንዳ ይዘዉ ህዝብን ይሳደባሉ፥፥
— ነገደ ጉራጌ በኢትዮጵያ እንደ ልቡ ነግዶ እና ሰርቶ እንዳይኖር በልዩ ልዩ የሀገሪቱ ክፍል ንግዱ ይወረሳል፥ ከሚኖርበት ይፈናቀላል፥ ይገደላል ይጨፈጨፋል፥፥ ሊላዉ ቀርቶ በሀረር፥ በአዋሳ እና በናዝሬት ቢዝነሱ ይወርሳል፥ በብዙ የኦሮሚያ አካባቢዎችም ይፈናቀላል፥፥ ይሄ የነገድ ጉራጌ መከራ ከወያኔ እስከ ብልጽግና የቀጠል ነዉ፥፥ በተለይም ግን በሃሳይ መስሂዉ ብልጽግና በባሰ መልክ ተጠናክሮ ቀጥሏል፥፥
–ኢትዮጵያ የሁሉም ኢትዮጵያዉያን ሀገር እንዳትሆን ብልጽግና በጎሳ ፖለቲካ ሀገራዊ መሰረቱን በመናድ እንዲሁም ለአንዳንድ ነገዶች አዳዲስ ክልሎችን በመፍጠር የጎሳ ፖለቲካን ህጋዊ አድርጎ ቀጥሏል፥፥ ነገደ ጉራጌ ከጉራጌ ክልልነት ይልቅ ኢትዮጵያ ሀገር ሆና ብትቀጥል አትራፊ መሆኑን ጠንቅቆ የሚያቅ ህዝብ ነዉ፥፥ ሆኖም በሀገር ደረጃ ማረፊያ ያጣዉ ነገደ ጉራጌ ክልል ይኑረኝ የሚል ጥያቄን ማንሳቱ ከዘረኝነት ወይም ኢትዮጵያን ለመጉዳት የታሰበ ሳይሆን ከሚደርስበት መከራ መሸሸጊያ ፍለጋ ነዉ፥፥
— ሆኖም ሀሳይ መሲሁ የብልጽግና መንግስት ሰላማዊ ጥያቄ ያነሳዉን የጉራጌን ህዝብ መደብደብ፥ መቀጥቀጥ፥ ማሰር፥ ሀብታቸዉን ማቃጥልልን የፖለቲካ ግብ አድርጎ ይዞታል፥፥ የብልጽግና ካድሬዎችም የጉራጌን ህዝብ መደብደብ እና መከራ ለኢትዮጵያ አንድነት ሲባል ነዉ በማለት ጸረ ህዝብ ፕሮፖጋንዳቸዉን እየረጩ ነዉ፥፥