>

ከአርጆ ጉደቱ እና ከነቀምት ከሞት ተርፈው ሲመጡ የነበሩ አማሮች ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ በኦህዴድ/ኦነግ ተከለከሉ...! ( አሚማ)

ከአርጆ ጉደቱ እና ከነቀምት ከሞት ተርፈው ሲመጡ የነበሩ አማሮች ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ በኦህዴድ/ኦነግ ተከለከሉ…!

አሚማ


ከአርጆ ጉደቱ እና ከነቀምት ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ የነበሩ አንድ ተሽከርካሪ ሙሉ አማራዎች ምዕራብ ሸዋ ዞን ባኮቲቤ ሲደርሱ እንዳያልፉ ክልከላ የተደረገባቸው መሆኑን አስታውቀዋል።

ህዳር 12/2015 ከነቀምት ተነስተው ወደ አዲስ አበባ ብሎም ወደ ወሎ ኮምቦልቻ ለማቅናት በአንድ ቅጥቅጥ አይሱዙ እየተጓዙ የነበሩ ከእነ ህጻናቱ ከ70 በላይ አማራዎች ምዕራብ ሸዋ ዞን ባኮቲቤ ላይ ሲደርሱ ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ ወደነቀምት እንዲመለሱ መደረጉ ተገልጧል።

እንዲመለሱ የተደረገውም በባኮ ቲቤ ፖሊሶች ሲሆን መኪናውን አስቁመው ፍተሻ ካደረጉ በኋላ ከምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በማንነታቸው ብቻ ተፈናቅለው በከፍተኛ ችግር የከረሙ መሆናቸውን የገለጹላቸው ቢሆንም ሾፌሩን አስገድደው እንዲመልስ አድርገውታል።

ተፈናቃይ ወገኖችም ለመመለስ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን፣ ለደህንነታቸው እንደሚሰጉ እና በርሃብ እየተቆሉ መሆናቸውን ቢገልጹም ፖሊሶች ከተደዋወሉ በኋላ ለመደብደብ በመዘጋጀታቸው ተገደው ወደ ነቀምት እንዲመለሱ መደረጉ ታውቋል።

እነዚህ እየተንገላቱ ያሉ ተፈናቃዮች ሰኔ 11/2014፣ ነሃሴ 23/2014 እና ጥቅምት 23ለ24/2015 ከጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ለሶስተኛ ጊዜ ተፈናቅለው ከአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና ከተባባሪ የመንግስት አካላት ማንነት ተኮር ጥቃት የተረፉ እና የሚደርስላቸው ያጡ አማራዎች ናቸው።

ከሞት ለምን አመለጣችሁ መሆኑ ነው

Filed in: Amharic