>

ትኩረት የተነፈገው ወደ ዘር ጦርነት እየሄደ ያለው የነወለጋ ችግር  (ግርማ  ካሳ)

ትኩረት የተነፈገው ወደ ዘር ጦርነት እየሄደ ያለው የነወለጋ ችግር

ግርማ  ካሳ


*…. ልዩ ሀይሉ ከኦነግ በላይ ጨፈጨፈን

ወገኖች በወለጋ፣ ምእራብ ሸዋ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ጉጂ፣ ቦረና፣ በቅርቡ ደግሞ በአርሲ እልቂቶችና ደም መፋሰሶች እየተበራከቱ መጥተዋል፡፡ በምእራብ ኦሮሞ ክልል ያሰባሰብኩት አንዳንድ መረጃዎች ላጋራችሁ፡፡

ቢያንስ አምስት የታጠቁ ኃይላት አሉ፡፡ 1ኛ በነ ጃል መሮ የሚመሩት  ኦነጎች፣ 2ኛ ኦህዴድ ብልጽግና ያደራጃቸው በመንግስት መዋቅር ውስጥ ባሉ አካላት የሚደገፉ ኦነጎች፣ 3ኛ የኦሮሞ ልዩ ኃይሎች፣ 4ኛ የአገር መከላከያ ሰራዊትና አምስተኛ የአማራ ሚሊሺያዎች ናቸው፡፡

የአማራ ሚሊሺያዎች የሚንቀሳቀሱት በዋናነት በምስራቅ ወለጋ ዞን ሰሜናዊ ወረዳዎች፣  በጊዳና በኪረሙ፣ በሆሮጉድሩ ዞን ባሉ የኡሙሩ፣ ጃርቴና አቤ ደንጎሮ ወረዳዎች  እና በሰሚነሸእዋ ደራ ወረዳ ነው፡፡ በወለጋ ባሉ አምስት ወረዳዎች አማራዎች ብዛታቸው ከአንድ ሶስተኛ እስከ ግማሽ እንደሆነ ነው የሚነገረው፡፡በደራ ደግሞ ከ75% በላይ ናቸው ነው የሚባለው፡፡

በምእራብና ቂለም ወለጋ፣ በመራብ ሸዋ ወረዳ፣ ከደራ ውጭ ባሉ የሰሚነ ሸዋ ወረዳዎች የአማራ ሚሊሺያዎች የሉም፡፡ በነዚህ ቦታዎችን የሚንቀሳቀሱ ኃይላት አራት ብቻ ናቸው ማለት ነው፡፡

እስከ አሁን በተደረጉ ጦርነቶች፣  ከ7 ሺህ በላይ ኦሮሞዎች፣ ለ4 ሺህ በላይ አማራዎች እንደተገደሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከ750  ሺህ በላይ ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል፡፡

የፌዴራል መከላከያ ባለባቸው አካባቢዎች ሰላምና መረጋጋቶች አሉ፡፡ ሆኖ ልክ የፌዴራል መከላከያ ሲነሳ ወይንም ወደ ሌላ ቦታ ሲዘዋወር እልቂቶች ይፈጠራሉ፡፡ የኦሮሞ ልዩ ኃይሎች አንዳንድ ቦታ በሃቀኝነት ህዝብን በመጠበቅ መስዋትነት እየከፈሉ ያሉ ብዙ አሉ፡፡ በሌላ በኩል ከኦነግ አንጃዎች ጋር ሆነው የሚሰሩ፣ ለኦነግ መረጃዎች የሚያቀብሉም አሉ፡፡ ብዙ የልዩ ኃይል አባላትም ኦነጎችን የተቀላቀሉም አሉ፡፡

ኦነጎች በቅርቡ ነጆ፣ ደምቢ፣ ነቀምቴ ከተሞች ዘልቀው በመግባት ብዙ ወድመት እንደፈጸሙ የሚታወስ ነው፡፡ ሆኖ ልክ የመከላከያ ሰራዊት ሲመጣ ሸሽተው ይሄዳሉ፡፡ በቅርቡም ደግሞ በምስራቅና በሆሮ ጉድሩ  በአማራ ሚሊሺያዎችና በኦነጎች መካከል ውጊያዎች ተደርገዋል፡፡ የኦሮሞ ልዩ ኃይሎችም አሰላለፋቸውን ከኦሮሞ ልዩ ኃይሎች ጋር ያደረጉበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ በዚያ አካባቢ ሁኔታው ወደ ዘር ጦርነት እያመራ ነው፡፡ መልኩን እየቀየረ ነው የመጣው፡፡

በኔ እምነት በአስቸኳይ ከፍተኛ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደዚያ እንዲሰማሩ ተደርጎ፣ በቋሚነት የሆሮ ጉድሩ ዞንን ሙሉ ለሙሉ፣ እንዲሁም ከነቀምቴ በስተሰሜን ያለውን የምስራቅ ወለጋ ዞን አካባቢዎች እንዲቆጣጠር መደረግ አለበት፡፡ የኦሮሞ ልዩ ኃይል ከነዚህ አካባቢዎች ለቆ መውጣት አለበት፡፡ ኦነጎችን ሙሉ ለሙሉ በየጫካዉና በጢሻው በመግባት ማጽዳትም ያስፈልጋል፡፡ የአማራ ሚሊሺያዎችም ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ይደረግ፡፡  ከዚያ በአማራና በኦሮሞ ሽምጋሌዎች መካከል ውይይቶች ተደርገው ፣ አብረው የሚሰሩበት ሁኔታ ይፈለግ፡፡ ይህ ካልሆነ ግን በአማራና በኦሮሞ መካከል እጅግ በጣም አደገኛ የሆነ የዘር፣ የመበቃቀል ክፉ ጦርነት ነው እየሆነ የሚመጣው፡፡

በምእራብና በቄሌም ወለጋ፣ በኦህዴድ ብልጽግናዎችና በኦነጎች መካከል ባለው ጦርነት ነው ሰው እያለቀ ያለው፡፡ በዚህ መሃል፣ ኦነግ ሲመቱ፣ በበቀል አህያዊን ፈርቶ ዳዉላውን እንደሚባለው፣ በዚያ  የሚኖሩ፣ ራሳቸውን መመከት የማይችሉ  ሰላማዊ አማራዎችን ይጨፈጭፋሉ፡፡ ኦሮሞውም ፍዳዉን እየበላ ነው፡፡ ጥቃት ብልጽግናዎች ኦነግ ደገፋችሁ ብለው መከራቸው ያበሏቸዋል፡፡ ማታ ኦነጎች ይመጡና ብልጽግናን ደገፋችሁ ብለው ፍዳቸውን ያሳዩአቸዋል፡፡

እዚህ ግር እንደው ጊዚያዊ መፍትሄ የምለው፣ የብልጽግና መንግስት ሰላምና መረጋጋትን ማምጣት ካልቻለ፣ በሰላምም ይሁን በጦርነት፣እንዳለ ቄሌምና ምእራብ ወለጋ ታጣቂዎቹን እንዲወጣ ማድረጉ ሊሻል ይችላል፡፡ ህዝቡ ሰላም እንዲያገኝ ብለው አልነበረም ከትግራይ ወጥተው የነበሩት፡፡ አሁን ህዝቡ ሰላም እንዲያገኝ የመንግስት ታጣቂዎች ከቄሌምና ከ መራብ ወለጋ ይውጡ፡፡

(ከዚህ በታች ያለችው፣ የጦርነት ሰለባ የሆነች የኦሮሞ እናት ናት፡፡ እንግዲህ ያለፈው አራት አመት ለዚች እናት ብ ልጽግና ነን የሚለው ቡድን ያመጣላት ውድመትን ነው፡፡ ላንቺ ለኦሮሞዋ ቋሚያ፣ም ከኦሮሞ ነጻነት፣ ፍትህ እቆማለሁ፣ የሚለው፣ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ግ ን ባር በሉት ሰራዊት ፣ ለዚህ እናት ያተረፈላት ነገር ሰቆቃን ነው፡፡

https://youtu.be/nbtR3w-NMwA

Filed in: Amharic