>

ለቤተመንግስት መስሪያ ሲባል በርካታ  ዜጎች ተፈናቅለው ወደ ጎዳና ሊጣሉ ነው...! (ባልደራስ)

ለቤተመንግስት መስሪያ ሲባል በርካታ  ዜጎች ተፈናቅለው ወደ ጎዳና ሊጣሉ ነው…!

ባልደራስ


*…የወረዳው የመሬት አስተዳደር ሀለፊዋ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በመምጣት፤ “በሶስት ቀን እቃችሁን አውጡ ቤታችሁ ይፋርሳል” እንዳሏቸው ነዋሪዎቹ ተናግረዋል..!

ከወር በፊት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 10 እየተሠራ ነው በሚባለው ቤተ-መንግሥት ሳቢያ የአካባቢው ነዋሪዎች ቅያሪ ቦታ ቤት መቀለሻ ገንዘብ ሳይሰጣቸው በላያቸው ላይ ሊፈርስ እንደሆነ ከነዋሪዎቹ በደረሰን ጥቆማ መሠረት አቤቱታቸው ሰሚ ያገኛል በሚል ተስፋ ፓርቲያችን ባልደራስ መግለጫ አውጥቶ ነበር፡፡ በወቅቱ ቤቶቹን በነዋሪዎቹ ላይ የማፍረስ ሂደቱ ለጊዜውም ቢሆን ተገትቶ ነበር፡፡ ይሁንና አሁንም የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ነዋሪዎች ምንም ምትክ ቦታ እና የመሥሪያ ገንዘብ ሳይሰጣቸው ቤታቸው ላያቸው ላይ ሊፈርስ እንደሆነ  በድጋሚ በመግለፅ ላይ ናቸው፡፡

በ13/03/2015 ዓ.ም የወረዳው የመሬት አስተዳደር ሀለፊዋ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በመምጣት፤ በሶስት ቀን እቃችሁን አውጡ ቤታችሁ ይፋርሳል እንዳሏቸው ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። ይህም የአካባቢውን ህብረተሰብ ድንጋጤ ውስጥ መክተቱን ተናግረዋል። ትዐዛዙ የደረሳቸውም በፅሁፍ ሳይሆን በቃል ብቻ መሆኑን ነዋሪዎቹ በመግለፅ ላይ ናቸው፡፡ በፅሁፍ እንዲሰጧቸው ቢጠይቁም እንደተከለከሉ ተናግረዋል። ይኽ አሠራር ተጠያቂነትን የመሸሽ የተለመደ አካሄድ ነው፡፡ አቤቱታ ሰሜ ባይኖርም ውሳኔው በፅሁፍ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡

Filed in: Amharic