ጋዜጠኛ ታዲዮስ ታንቱ በአራት ክሶች እንዲከላከሉ በሙሉ ድምጽ ብይን ተሰጠባቸው…!
ናትናኤል ያለምዘውድ
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የፀረሽብርና ህገመንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው ዛሬ ከሰዓት የቀረብት ጋዜጠኛ ታዲዮስ ታንቱ!!
የጥላቻ ንግግር በማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀል በቀረበባቸው በአራት ክሶች እንዲከላከሉ በሙሉ ድምጽ ብይን ተሰጥቶባቸዋል
በ5ኛው ክስ በሚመለከት ግን መከላከል ሳያስፈልጋቸው ነጻ ናቸው ተብለዋል።
ይህ በእንደዚሁ እንዳለ የጋሽ ታዲዮስ ጠበቆች የሆኑት ጠበቃ አዲሱ ጌታነህና እታለማው የዋስትና ጥያቄ በድጋሚ ጠይቀው ውሳኔው ለማክሰኞ 20/3/2015ዓ.ም ተቀጥሯል !!