“… እኔም ሆንኩ ጠበቆቼ በቀጣዩ ችሎት አንቀርብም ይበቃል…!”
አርበኛ ዘመነ ካሴ
ጥላሁን አበጀ
በአርበኛ ዘመነ ካሴ ላይ ተመስርቶ የነበረው ክስ ዛሬ ህዳር 16 በዋለው ችሎት የአርበኛ ዘመነ ካሴ ጠበቆች ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ በመቀበል ክሱን ውድቅ አድርጎታል።አቃቢ ህግ ክሰ አሻሸሎ የሚመጣ ከሆነ በሚል ለህዳር 26 ተቀጥሯል።
ከህግ ባለሙያዎች እንደገለፁልኝ ከሆነ በአሁኑ ሰዓት አርበኛ ዘመነ ካሴ ምንም አይነት ክስ የለበትም ።ምናልባትም በሚቀጥለው ቀጠሮ አቃቢ ህግ ተለዋጭ ክስ እስካላመጣ ከክስ ነፃ ነውም ብለውኛል።
በሌላ በኩል አርበኛ ዘመነ ካሴ ከችሎቱ ሲወጣ በፍ/ቤቱ ጊቢ ውስጥ ለነበረው በርካታ ደጋፊዎቹ ጠንከር ያለ መልዕክት አስተላልፏል።በመልዕክቱም :-በውሸት ክስ ቤተሰቦቼም ደጋፊዎቼም ችሎት እንዲመላለሱ አልፈልግም ,ሽምግልናም ይበቃል, ወደ ፍ/ቤትም አልመጣም በማለት ገልጿል።
በሚቀጥለው ቀጠሮ አርበኛውም ጠበቆቸም አይገኙም!