>

ከዘር ፖለቲካው ያተረፍነው  ግድያ፣ መፈናቀል፣ ጦርነት፣ ስደት፣ ለትውልድ የሚተርፍ ቂም ብቻ ነው ...! (ግርማ ካሳ)

ከዘር ፖለቲካው ያተረፍነው  ግድያ፣ መፈናቀል፣ ጦርነት፣ ስደት፣ ለትውልድ የሚተርፍ ቂም ብቻ ነው …!

ግርማ ካሳ


ትግራይ፣ ጎንደር፣ ወሎና አፋር  የሆነውን ሁላችንም የምናውቀው ነው፡፡ ጦርነት፣  የመቶ ሺሆች ህይወት መቀጠፍ፣ ውደመት፣ መከራ፣ ሰቆቃና የሚሊዮኖች መፈናቀል:፡፡በኦሮሞ ክልል፣  በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል የዘር ማጥፋት፣ የዘር ማፅዳት ተፈፅመዋል፡፡እየተፈፀሙም ነው፡፡የጎሳ የዘር ጦርነቶች ብዙ ህዝብ እየቀጠፉ ነው፡፡  ከምእራብ ኦሮሞ ክልል ብቻ ከ750 ሺህ በላይ ዜጎችተፈናቅለዋል፡፡ወላይታና  ጉራጌ ዞኖች ክልል ካልሆንን የሚል ውዝግብ ውስጥ ናቸው፡፡ በእፋርና በሶማሌ ክልል ሚሊሺያዎች መካከል ደም እየፈሰስ ነው፡፡ከተሞች እየወደሙ ነው:: በአዲስ አበባችን የኦሮሞ ክልል መዝሙር ካልተዘመረ፣ ዩእአባ ገዳ አርማ ካልተሰቀለ በሚል ትምህርት ቤቶች የመማሪያ ቦታዎች ሳይሆን የቀስ ቦታዎች እየሆኑ ነው፤፡

ምን አለፋችሁ ከጎሳና ከዘር ፖለቲካው የተነሳ ኢትዮጵያውን እርስ በርስ እየተገዳደልን ነው:: ኢትዮጵያ እጅግ በጣም እየተማሰች ነው፡፡

አሁንም እላለሁ ከዘር ፖለቲካ እንውጣ፡፡ የዘር ሕገ መግስቱ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ውስጥ ይጣል፡፡  የጎሳ አወቃቀር ይፍረስ፡፡  የአማራ ክልል ይፍረስ:: የኦሮሞ ክልል ይፍረስ:: ለእስተዳደር አመች የሆኑ፣ በዘር ላይ ያልተመሰረቱ፣ ማንም ዜጋ ከየትኛው አካባቢ መጥቶ መስራት፣ ሃብት ማፍራት፣ መኖር፣ መነገ፣  ኢንቨስት ማድርግ፣ መመረጥና መምርጥ የሚችልባቸው አነስ ያሉ መስተታደሮች ይመስረቱ፡፡

Filed in: Amharic