>
4:38 pm - Friday December 1, 0226

እኽኽ....እስከመቼ ? [እንግዳ ታደሰ - ኦስሎ]

ኢትዮጵያን እየገዛት ያለው የሰለጠነ መንግሥት ነው ወይስ በህገ- አራዊት የሚመራ የጫካ መንግሥት ? አንድ ፋኖ ከጫካ ወጥቶ 24 ዓመት ከተማ ገብቶ ለዚያውም ትልቋን አገር ኢትዮጵያ እየገዙ ፥ ከሸበጥ ጫማ ወደ ጣልያን ምርጥ የቆዳ ጫማ በትራንስፎርሜሽን ዑደት ከተለወጡ በኋላ ፥ በትግል ላይ ሳሉ አንገታቸው ላይ ሸብ የሚያደርጉትን « ኩሽክ » የተባለውን ሻርፓቸውን በሲልክ ክራቫት ከለወጡ በኋላ ትንሽ …. ከተሜ… ከተሜ ይሸታሉ ሲባሉ ፣ ጭራሽ « እዚያው ደደቢቴ ከያዘኝ ልክፍቴ » ከሚለው የአማራ ህዝብ ጥላቻቸው ጋር እስከመቼ ድረስ ነው አገራችንን እያመሷት የሚቀጥሉት ?

The TPLF artistsበጨቋኙና ግፈኛው የስታሊን አገዛዝ ዘመን ወደነበረ አንድ ቀልድ አዘል፣ ነገር ግን እውነት ገላጭ ሰፈር ልውሰዳችሁ፡፡ጊዜው የቀልድ ባይሆንም ፣ ፍራሽ አውርደን ሙሾ ደርድረን የምናለቅስበት ወቅት ቢሆንም የመለስ ራዕይ እየተፈጸመ ካለባት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው እውነታ ከስታሊን ዘመን ጋር ስለተመሳሰለብኝ ነው ቀልዱን የሰነቀርኩባችሁ ፡፡ ይቅር በሉኝ ፡፡ አንድ በድሜ የገዘፉ አሮጌት ሴት በስታሊን ዘመን ሁለት ሰዓታት ያህል በአንዘፍዛፊ በረዶ መሃል ቆመው አውቶቡስ ሲጠብቁ ፣ አውቶብሱ ጥቅጥቅ ብሎ ሳያቆምላቸው ያልፋል ፡፡ ጥበቃቸው ሰአታት ጨመረ ፡፡ በስተመጨረሻ አንድ ትንሽ የተረፈ ቦታ ያለው አውቶቡስ ቆመላቸው ፡፡ አሮጊቷ እንደምንም ብለው በአጋዥ ጎታቾች ተረድተው አውቶቡሱ ላይ እንደወጡ « ተመስገን አምላኬ ለዚህ ያበቃኽኝ ብለው ለፈጣሪያቸው ምስጋና ያቀርባሉ » ወዲያው የአውቶቡሱ ሾፌር ፣ እማማ ! እንደርሱ አይባልም ፡፡ ዘላለማዊ ክብር ለጓድ እስታሊን ነው የሚባለው ብሎ ያር ’ቃቸዋል ፡፡

ይቅርታ ጓድ ! እኔ ኋላ ቀር አሮጊት ስለሆንኩ ነው የማይባለውን ያልኩት በማለት ለሾፌሩ ከመለሱ በሗላ ሁለተኛ አይለመደኝም ጓድ በማለት ጥቂት ደቂቃዎች ቆይተው ፣ ጉሮራቸውን እኽኽ በማለት እንዳጠሩ ፣ ለአውቶቡሱ ሾፌር ሌላ ጥያቄ ወረወሩ ፡፡ ይቅርታ ጓድ ! እኔ አሮጊትና ማስታወስም የተሳነኝ ሰው ነኝ ፣ የግዜር ስሙን እንዳልጠራ ተከልክዬ ስታሊንን ማመስገን እንዳለብኝ ተነግሮኛል ፡፡ ስታሊን ሲሞት ደግሞ ምን ልል ነው ? በማለት እንደጠየቁ ? ጓድ ሾፌር ፈጠን ብሎ አዩ እማማ ! ያንግዜ ክብር ምስጋና ለፈጣሪ ብለው ይመልሳሉ አላቸው ብሎ በስታሊን ጊዜ የተቀመጡ የቀልድ መዘክሮች ያስታውሳሉ ፡፡

ዘላለማዊ ክብር ለመለስ ዜናዊ እንዳለው ኃይለማርያም ደሳለኝ መሆኑ ነው ፡፡ስንት ዓመት በአዳር ጸሎት ሲያነበው የነበረውን መጽሃፍ ቅዱሳዊ ቃል ለእምብርቱ ማስፊያና ለሆዱ ሲል እንደካደው ፡፡ በነገራችን ላይ አሁንም ይቅር በሉኝ ደሳለኝ የሚል ስም ያላችሁ ፡፡ ስሙን ያራከሱት ወያኔዎች ናቸው ፡፡ ወያኔዎች አማራን ለማዋረድ ሲሉ ፣ለአህያቸው ሸገር ሲገቡ በፊት አውራሪነት እየነዱ ላስገቡት የቡላ አህያ መጠርያ ያወጡለት ስም ደስ አለኝ ይባላል ፡፡ ዛሬ በዙርያቸው የሰበሰቧቸውን ትግራይ ያልሆኑ ብሄረሰቦች ሁሉ ሲጠሯቸው « ደስአለኞች» እያሏቸው ነው የሚጠሯቸው፡፡

ማን ነው ቀልድ ያለው ከሶቭየት መንደር ብቻ ነው ያለው ? ፡፡ ኢትዮጵያችን እኮ የቅኔ መዝረፊያ አገር ብቻ አይደለችም የቀልድም መፈብረኪያ ጭምር ናት ፡፡ ኃይላማርያም ሳይረሳ ! ወደ ሰማሁት ቀልድ ልውሰዳችሁ ፡፡ ኃይለማርያም ደስ አለኝን የውጭ አገር ጋዜጠኞች ፣ እርሶም ተጋዳላይ ነበሩ እንዴ በማለት ይጠይቁታል ? ኧረ እኔ እቴ ! አባቴ ነበር ተጋዳላይ ! ዝርዝር ውስጥ አልገባም ኢትዮጵያ እውነትም የቅኔ አገር ናት ፡፡

እኽኽ ! እስከመቼ ?

ፈረንጆቹ short memory የሚሉት የመጃጀት በሽታ ካለተጠናወተን በስተቀር ወደ ኋላ 24 ዓመታት የተካሄዱትን ኢትዮጵያን ከአማራ ዘር ጋር በማመሳሰል ጥንታዊ ታሪኳን የማጥፋት ዘመቻ ሳንቆጥር እስቲ የቅርቡን ክስተት እንውሰድ፣ በመንገድ ሥራ ስም ለፋሽስት ጣልያን አትገዙ ብለው የገዘቱትንና መስዋዕት የሆኑትን አቡነ ጴጥሮስ ሃውልት ከስፍራው ሲነሳ ምን አለን ? ነብሱን ይማረውና ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን እዚያች ሃውልት ስር ነበር ፣ አንድ ሰካራም ጀብራሬ ሽንቱን ሲሸና አግኝቶት ከጀብራሬው ጋር ቦክስ ተጋጥሞ በእልህ እመብርሃን ኢትዮጵያን ረሳሻት በሚል ግጥም ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት የሚለውን ድንቅ ተውኔቱን የደረሰው ፡፡

ወመዘክር ውስጥ ከመቶ ዓመታት በላይ የተቀመጡ የታሪክ ድርሳናት ለስኳር መጠቅለያ ሲቸበቸቡና ፣ የአማራ ታሪክ በመጽሃፍ መልክ አይቀመጥም ተብሎ ሲቃጠሉ ምን አልን ? ጉድ አንድ ሰሞን ነው የአንድ ሳምንት ጩኽት ፡፡ ለዚህ ደግሞ የወያኔ ትግሬዎችን የተባበሯቸው ብዙ ደስአለኞች ጭምር ናቸው ፡፡ ለአንዲት ዛኒጋባ ቤት ማቆሚያ ቦታ እስከተሰጣቸው ድረስ እናቴን ያገባ ሁሉ አባቴ ነው የሚሉ ሆድ አደሮች እስካሉ ድረስ ገና ብዙ ጉድ ይታያል ፡፡በወገኖቻቸው እልቂት ላይ ደደቢት ሄደው ፣ ወገን በወገኑ ላይ ላደረሰው እልቂት ካገር ገዳዮች ጋር ብብት ለብብት ተቃቅፈው ዳንስ ከሚያጦፉት ሰዎች በላይ ምን ምስክርነት አለ ? ደሳለኝ መባላቸው ሲያንሳቸው ነው ፡፡ ታንክ ላይ ወጥቶ ሰላምታ ከሚሰጥ አርቲስት ያድናችሁ ፡፡ ከሳሞራ ጉያ ውስጥ ሰምጣ ክምትደንስ መበለት ሴት ያርቃችሁ ፡፡

የጀግናዋ መሪ ጣይቱ ብጡል አሻራ የሆነው ፥ በታሪካዊ ቅርስነት ተመዝግቦ መያዝ የሚገባው ፥ ጥንታዊ ሆቴል ፣ ለባለጊዜዎች በማትረባ ሶልዲ ተሸጦ እኽኽ ብለን አዝነን እንዳልኖርን ፣ በዚህ ሆቴል ውስጥ በቅርቡ ደረታቸውን ለጥይት ያሉ ቆራጥ የኪነጥበብ ሰዎች መንግስት አስነፋጭ የሆኑ ህዝባዊ ሥራዎቻቸውን ስላቀረቡና ፣ ህብረተሰቡን ስላነቁበት የጎረበጠው የትግራይ ወያኔ ቡድን ፣ እዛው ጃዝ አምባ ላውንጅ አዳራሽ ላይ ክብሪቱን እንደጫረ እየተረጋገጠ ነው ፡፡ እግዚአብሄር ያሳያችሁ ! ከጣይቱ ሆቴል እስከ ጊዮርጊስ ድረስ ርቀቱ ምን ያህል ይሆን ? ወይስ እሳት አደጋ ጣቢያ ከዚያ ተነስቶ ይሆን ? አላውቅም ድሮ በማውቀው ከሆነ የማወራው ይቅር በሉኝ ፡፡

ሴራው እንዲህ ነው !! ፡፡ ከጠዋቱ አንድ ሰአት በፊት አንድ የጃዝ አምባ ሠራተኛ ያለወትሮው በጠዋት ገብቶ ወጥቷል ፡፡እርሱ ከወጣ በኋላ ከጃዝ አምባው አዳራሽ ላይ እሳቱ ተነስቷል ፡፡ ያ ሰው ማነው ? ገብራይ ? ለታይ ?ወይስ ካላዩ አይታወቅም ፡፡ እንዲታወቅም አያስፈልግም ፡፡ ምክንያቱም ሴራው በአማራ ቅርስነት ተብሎ በሚገመተው ላይ መዝመት ነዋ !! እጅግ የሚገርመው ! ይህ በወያኔ ትግሬዎች የተለኮሰ እሳት ጣራውን ይዞት እስኪወርድ ድረስ ጊዮርጊስ አጠገብ ያለው የእሳት አደጋ ፣ የአደጋ መጥሪያ ስልኩን አጥፍቶ እሳቱ ስራውን እስኪጨርስ ድረስ ቁጭ ብሎ ነበር ፡፡እግዜር ያሳያችሁ ! ሰው በመኪና ሄዶ ነው ኧረ ! አገር ነደደ ያላቸው ፡፡መጥተውስ ምን ሠሩ ? ይዘውት የመጡት የእሳት አደጋ ማጥፊያ መኪና አይሰራም ፡፡ ይህ የኔ ፈጠራ አይደለም እዚህ ጋዜጣ ላይ የሴራውን ደባ ታነቡታላችሁ ፡፡http://www.ethiopianreporter.com/…/8520-%E1%8B%A8%E1%8A%A5%…

አገራችንን እየገዛ ያለው ማነው ? እንደድሮው የሰፈር ጋንጊስተሮች ቡድን የቻይና ግሩፕ ? ኧረ እነርሱ በስንት ጣማቸው መንግሥት ባይሆኑም በሰፈር አዛውንቶች ተግሳጽ ጸጥ እኮ ይሉ ነበር ፡፡ እነኚህ እኮ ከመንደር ዱርየ በታች የወረዱ የደደቢት ደደቦች ናቸው ፡፡ የአንድ ጋዜጠኛ ሚስት ነሽ ብለው ፣ ከነህጻናቶቿ በምግብና በመኝታ ቀጥተው ወደመጣችበት አገር ዲፖርት የሚያደርጉ መንግሥት ናቸው ወይስ ዱርየዎች ? ያሳፍራል ! የደደቢቶቹ እነ ካህሳይና ወይም ግርማይ ኤርፖርት ላይ ስልጣን በችሎታ ሳይሆን በዘር ተሰጥቷቸው እስከዛሬ ስንቱን አስምጠው ? ስንቱን አሳልጠው ይሆን ? እኽኽ እስከመቼ !!

Filed in: Amharic