>

ዲሽቃን ጨምሮ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ከፍተኛ የሆነ አዲስ የዘር ፍጂት በወለጋ ተፈፀመ ...! (ጌትነት አሻግሬ)

ዲሽቃን ጨምሮ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ከፍተኛ የሆነ አዲስ የዘር ፍጂት በወለጋ ተፈፀመ …!

ጌትነት አሻግሬ


የኦሮሚያ ልዩ ሃይል ዛሬ ከለሊቱ 11ሰዓት ጀምሮ በአንገር ጉትን እና የተለያዩ የወለጋ አካባቢዎች የአማራ ተወላጆችን መሰረት ያደረገ ጪፍጨፋ እያካሄደ መሆኑን ምንጮቻችን ከቦታው አድርሰውናል።

ዛሬ ህዳር 24 /2015 ዓ/ም ከለሊቱ 11ሰዓት ጀምሮ በተካሄደው ጪፍጨፋ ባብዛኛው እቤት ውስጥ ያሉ ሴቶች፣ህፃናትእና አዛውንቶች ያለርህራሄ ተገድለዋል ተብሏል።

በዚህም በርካታ ቁጥር ያላቸው የአማራ ተወላጆች ሲገደሉ በርካቶች ደግሞ መቁሰላቸውን የአይን እማኞች ለአማራ ድምፅ ተናግረዋል።

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ ውስጥ ልዩ ስማቸው አንዶዴ ዲቾ ቀበሌ እና  አንገር ጉቴ ከተማ ላይ የክልሉ ፀጥታ ኃይሎች ዛሬ ህዳር 24/2015 ዓ/ም ከማለዳው ጀምሮ በከፈቱት ተኩስ በርካታ የአማራ ተወላጆች መገደላቸውን የአይን እማኞች ለአማራ ድምፅ ተናግረዋል።

በፀጥታ ኃይሎቹ ዛሬ ህዳር 24/2015 ዓ/ም  ከንጋቱ 12 ሰአት ጀምሮ የተከፈተው ተኩስ ከአንገር ጉቴ ከተማ እና ከአንዶዴ ዲቾ ቀበሌ በተጨማሪ ወደ ሌሎች አከባቢዎችም እየተዛመተ መሆኑን የአይን እማኞቹ አመላክተዋል።

ከሰሞኑ በአከባቢው የሰፈሩት የክልሉ ፀጥታ ኃይሎች የአማራ ተወላጆችን ያነቃሉ፣ያደራጃሉ በሚል የጠረጠሯቸውን ግለሰቦችን ማሰር እና መደብደብ መጀመራቸውን ተከትሎ ጉዳዩን በሽምግልና ለመፍታት ነዋሪዎቹ ቡዙ ጥረት ሲያደርጉ መሰንበታቸውን ለአማራ ድምፅ ተናግረዋል።

የክልሉ ፀጥታ ኃይሎች ሽምግልናውን ገፍተው ነው ዛሬ ማለዳ ተኩስ የከፈቱት የሚሉት የአይን እማኞቹ፡በዚህም በርካታ ቁጥር ያላቸው የአማራ ተወላጆች ሲገደሉ በርካቶች ደግሞ መቁሰላቸው ተናግረዋል።

አሁን ላይ የአንገር ጉትን ከተማ ነዋሪዎች ከተማዋን ለቀው ህይወታቸውን ለማትረፍ እግር ወዳመራቸው እየሸሹ ሲሆን የሚመለከተው የመንግስት አካል በአስቸኳይ እንዲደርስላቸው ጥሪ አቅርበዋል።

የክልሉ ፀጥታ ኃይሎች የአማራ ተወላጆችን ያደራጃሉ ያሏቸውን ግለሰቦችን በህግ ጥላ ስር እናውላለን በሚል ከሰሞኑ በምስራቅ ወለጋ ጊዳ ኪረሙ ወረዳ ስር በምትገኘው ኪረሙ ከተማ እና በሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን ሆሮቡሉቅ ወረዳ እና ጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳ ባደረጉት እንቅስቃሴ ከ150 በላይ የአማራ ተወላጆችን መግደላቸውን የአማራ ድምፅ መዘገቡ አይዘነጋም።

Filed in: Amharic