>

የአባ ገዳ ባንዲራ በወላጆችም ተቃውሞ ገጠመው...! (ፅናት ሚዲያ )

የአባ ገዳ ባንዲራ በወላጆችም ተቃውሞ ገጠመው…!

ፅናት ሚዲያ 


*…  በአዲስ አበባ ጉለሌ ክ/ከተማ ታስቦ የነበረው የወላጆች ስብሰባ አለመሳካቱ ተሰማ።

እሁድ በ25/3/15 ዓም እለት እንጦጦ አምባ የቀድሞ አምሃ ደስታ የተማሪ ወላጅ ስብሰባ ነበር።

በርካታ ወላጆችም በመገኘት ህዝቡ የወረደው የኢትዮጵያ ባንዲራ መጀመሪያ ይሰቀል በማለት ጥያቄ አቀረበ።

በመጨረሻም ለሰብሳቢዎቹ  ማነው የኦሮሚያ ባንዲራ ይሰቀል ብሎ ያዘዛቹ በማለት ባለመግባባት ህዝቡ እንዲህ ድምፁን ከፍ በማድረግ አሰምቷል። ወላጆቹም የልጆቻቸውን ፍሬ እየተካፈሉ ነው አዲስ አበባ ወደ ትግል ገብቷል።

==

በአዲስ አበባ ኩለሌ ክ/ከተማ በቀድሞው አምሀ ደስታ በአሁኑ እንጦጦ አምባ ትምህርት ቤት ተማሪዎች  የኦሮሚያ ክልል ባንዲራ እና መዝሙር በግዳጅ እንዲዘምሩ በተነሳው ተቃውሞ በተያያዘ ከወላጆች ጋር ለማካሄድ የታሰበው ውይይት ባለመሥማማት መበተኑ ተሰምቷል።

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ሽሮ ሜዳ አካባቢ በሚገኘው አምሀ ደስታ ወይም እንጦጦ አምባ ትምህርት ቤት የኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ ዓላማ አይሰቀልም በሚል የተፈጠረውን አለመግባባት በተመለከተ ከወላጆችና መምህራን ጋር ለማካሄድ የታሰበው ስብሰባ ባለመግባባት መበተኑን ነው በስፍራው የነበሩ ምንጮቻችን የገለፁት፡፡

እንደ ምንጮቻችን ገለፃ ትናንት ህዳር 25 ተጠርቶ በነበረው ስብሰባ በርካታ ወላጆች ተገኝተው የነበረ ቢሆንም ገና ውይይቱ ሳይጀመር ወላጆች ባሰሙት ጉርምርምታ ሳይካሔድ ቀርቷል።

ድጋሚ እዚህ ትምህርት ቤት ልጆቻችንን ለማስተማር አንልክም ከፈለጋችሁ  አድርጉት በማለት የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማን እያውለበለቡ እና የኢትዮጵያን መዝሙር እየዘመሩ ወላጆች ከግቢ መውጣታቸው ነው የተነገረው።

አክለውም በገዥው ፓርቲ የታሰበውን የወላጆች ስብሰባ ተከትሎ ሽሮ ሜዳና አካባቢው በከፍተኛ ሁኔታ በፖሊስ ጥበቃ ስር መዋሉንም ምንጮች ለፅናት ሚዲያ ገልፀዋል።

https://fb.watch/hdRaaRf-_0/

አዲስ አበባ ወደ ትግል ገብቷል። 

Filed in: Amharic