>

ፋኖና ሻቢያ፣ ወያኔና ኦነግ  (መስፍን አረጋ )

ፋኖና ሻቢያ፣ ወያኔና ኦነግ

መስፍን አረጋ 


ጠላቶች ማንነታዊ ጠላቶች እና ምንነታዊ ጠላቶች ተብለው በሁለት ዐብይ ክፍሎች ሊከፈሉ ይችላሉ፡፡  ማንነታዊ ጠላት ማለት በማንነት (ማን በመሆን) የሚጠላ ጠላት ማለት ሲሆን፣ ምንነታዊ ጠላት ማለት ደግሞ በምንነት (ምን በመሆን) የሚጠላ ጠላት ማለት ነው፡፡

በማንነት የሚጠላ ማንነታዊ ጠላት ዘላለማዊ የሕልውና ጠላት ነው፣ ማንነትን መቀየር አይቻልምና፣ ጦቢያዊ መልኩን፣ ነብር ዝንጉርጉርነቱን ሊለወጥ አይችልም እንዲሉ (ኤርምያስ 13፡23)፡፡  ለምሳሌ ያህል ነጭ ላዕልተኞች (white supremacists) የጥቁር ማንነታዊ ስለሆነም ዘላለማዊ የሕልውና ጠላቶች ናቸው፣ ጥቁርን የሚጠሉት በጥቁርነቱ ነውና፣ ዓላማቸውም ጥቁርን ከምድረገጽ ማጥፋት ነውና፡፡  ባጭሩ ለመናገር ማንነታዊ ጠላት ማለት ሕልውናየ የሚጠበቀው የጠላቴን ሕልውና በማጥፋትና በማጥፋት ብቻ ነው በሚል ዳዶ ድምር (zero sum) መርሕ የሚመራ ሕልውና አጥፊ ጠላት ማለት ነው፡፡  

በሌላ በኩል ግን በምንነት (በድርጊት፣ በሁነት) የሚጠላ ምንነታዊ ጠላት፣ የሚጠላበት ድርጊት ወይም ሁነት ሲወገድ ጠላትነቱም አብሮ የሚወገድ ጊዜያዊ ጠላት ነው፡፡  ለምሳሌ ያህል ወያኔና ኦነግ ምንነታዊ ጠላቶች ናቸው፣ ጠላትነታቸው የስልጣንና የጥቅም ብቻ ነውና፡፡  የስልጣንና የጥቅም ቅሬታወቻቸውን ካስወገዱ ደግሞ ጠላትነታቸውም አብሮ ይወገዳልና፣ እየተወገደም ነውና፡፡ 

የአማራን ሕዝብ በተመለከተ ግን፣ ወያኔና ኦነግ የአማራን ሕዝብ የሚጠሉት በማንነቱ (አማራ በመሆኑ) ብቻ ነው፡፡  ስለዚህም ወያኔና ኦነግ የአማራን ሕልውና ለማጥፋት ቆርጠው የተነሱ፣ የአማራ ሕዝብ የሕልውና ጠላቶች ናቸው፡፡  በመሆናቸውም ወያኔንና ኦነግን በተመለከተ የአማራ ሕዝብ ያለው ምርጫ አንድና አንድ ብቻ ሲሆን፣ እሱም ወይ እነሱን ማጥፋት ወይም በነሱ መጥፋት ነው፡፡  ጅብ ከሚበላህ በልተኸው ተቀደስ፡፡       

በማንነት (ማን በመሆን) ከሚጠላ ከሕልውና ጠላት ጋር ማድረግ የሚቻለው ገድሎ የመዳን የሞት ሽረት ትግል ብቻ ነው፡፡  ከሕልውና ጠላት ጋር መከራከርም መደራደርም አይቻልም፣ ዓላማው ጠላቱን ከምድረገጽ ማጥፋትና ማጥፋት ብቻ ነውና፡፡  የሕልውና ጠላት እደራደራለሁ ካለ ደግሞ በድርድሩ አምኖበት ሳይሆን ጊዜ ለመግዛትና ለማዘናጋት ሲል ብቻ ነው፡፡  ስለዚህም፣ የአማራ ሕዝብ ከሕልውና ጠላቶቹ ከወያኔና ከኦነግ ጋር መቸም ቢሆን መደራደር የለበትም፣ ትርፉ ወያኔና ኦነግ ይበልጥ ተጠናክረው የሕልውናውን ክስመት ይበልጥ እንዲያፋጥኑት ጊዜ መስጠት ብቻ ነውና፡፡

በሌላ በኩል ግን፣ በምንነት (በድርጊት ወይም በሁኔታ) ከሚጠላ ጠላት ጋር ከመዋጋት ይልቅ መደራደር ይመረጣል፡፡  ሁለት ባላንጋሮች በሕልውና የሚፈላለጉ የሕልውና ጠላቶች እስካልሆኑ ድረስ፣ በእከክልኝ ልከክልህ ወይም በሰጥቶ መቀበል መርሕ መሠረት በመደራደር ለሁለቱም ባላንጋሮች ከሚበጅ ስምምነት ላይ መድረስ ይችላሉ፡፡  ለምሳሌ ያህል ወያኔና ኦነግ ጠላትነታቸው በስልጣንና በጥቅም ላይ ብቻ ስለሆነ፣ ለሁለቱም የሚበጃቸው ከመዋጋት ይልቅ መደራደር ነው፣ እያደረጉት ያሉትም ይህንኑ ነው፡፡  መደራደራቸውን ይበልጥ ጠቃሚ የሚያደርግላቸው ደግሞ ዓላማቸው የአማራን ሕልውና ለማጥፋት በመሆኑ፣ መተባበራቸው ዓላማቸውን የማሳካት ዕድላቸውን ከፍ ስለሚያደርግላቸው ነው፡፡

የማንነት (ማን የመሆን) ጠላት፣ ማንነቱን በራሱ ላይ ከመመሥረት ይልቅ የሌላውን ማንነት በማጥፋት ላይ የመሠረተ፣ በሥርሰደድ (chronic) የማንነት ቀውስ የሚሰቃይ፣ የዝቅተኝነት መንፈስ ክፉኛ የሚጫወትበት በሽተኛ ጠላት ነው፡፡  ለምሳሌ ያህል ወያኔ የአማራ ሕልውና ጠላት የሆነው ትግሬነቱን መሠረት ያደረገው የሐበሻ የሚባሉት ትውፊቶች (ታሪክ፣ ሐይማኖት፣ ባሕል፣ ስነጽሑፍ ወዘተ. ) ሁሉም የትግሬና የትግሬ ብቻ ናቸው በሚለው ድቡሽት ላይ ስለሆነና፣ ይህን ድቡሽታዊ ማንነቱን እውን ማድረግ  የሚችለው ደግሞ አማራን ከምድረገጽ በማጥፋት ብቻ ስለሆነ ነው፡፡  ለዚህ ደግሞ የአማራን ሕዝብ ቀን ከሌት ስለሚዘልፍ ብቻ፣ ወያኔወች በታላቅ አክብሮት “መምህር” ይሉት የነበረው፣ ነውር ጌጡ የሆነው ወያኔው አቶ ገብረኪዳን ደስታ “ትግሬ የራሱ ታሪክ አለው፣ አሮሞም የራሱ ታሪክ አለው፣ አማራ ደግሞ የራሱን ታሪክ ይፈልግ” ሲል የተናገረውን መጥቀስ ብቻ ይበቃል፡፡

ኦነግ ደግሞ የአማራ ሕዝብ የሕልውና ጠላት የሆነው በጭፍጨፋ የተስፋፋ መጤ የመሆን ታሪኩን ማጥፋት የሚችለው የአማራን ሕልውና በማጥፋት ብቻ ስለሆነ ነው፡፡  የኦነግ ትርክት አሌፍና ፓሌፍ (አልፋና ኦሜጋ) አማራ መጤ ነው የሚለው የሆነበትም ምክኒያት ይሄው ነው፣ ኋላ የመጣ ዓይን አወጣ እንዲሉ፡፡  የሉባ ዘላን ሠራዊት በሐበሻ ምድር ላይ ተስፋፍቶ የተንሰራፋው ሱማሌ በጅራፍ ሲገርፈው እየፈረጠጠ፣ ግራኝ አሕመድ አጼ ልብነ ድንግልን አሸንፎ ክፉኛ ያዳካመውን የአማራን ሕዝብ ያለርህራሄ እየጨፈጨፈ ነበር፡፡  ይህ እውነታ ደግሞ አነግን ስለሚያሸማቅቀው፣ እውነታውን ለማድበስበስ ከተቻለም ለማጥፋት የማይፈነቅለው ዲንጋ የለም፡፡  

ኦነግ ኦሮሞ ነው ከሚለው ሕዝብ ውስጥ ከዘጠና በመቶው በላይ ኦሮሞ ያይደለ፣ ማንነቱን በሞጋሳና በጉዲፈቻ አማካኝነት የተነጠቀ፣ ባብዛኛው አማራ የሆነ ሕዝብ ነው፡፡  

በጦቢያ ምድር ላይ ከጣና እስከ ጫሞ

በኦሮምኛ ቃል ያለ ተሰይሞ፣ 

ከመስፋፋት በፊት ሁሉም አስቀድሞ

አይደለም ኦሮሞ ወይም የኦሮሞ፡፡

ኦነግ ኦሮሞ ነው የሚለው ሕዝብ፣ አሮሞ የሚል ስያሜ በኦነግ ሳይሰጠው በፊት ራሱን ወረ ምንትስ፣ ወረ ቅብጥርስ እንጅ ኦሮሞ ብሎ አያውቅም፡፡  ሌላው ቀርቶ አሮሞ የሚለውን የኦነግን ተወዳጅ ቃል ለሕዝብ መጠሪያ እንዲሆን ለኦነግ የመረጠለት ባዕድ ጀርመናዊ ነው፡፡  በንደዚህ ዓይነት እንቶ ፈንቶ ላይ ማንነቱን መሥርቶ በማንነት ቀውስ የሚሰቃይ ድርጅት፣ የአማራ ሕዝብ የሕልውና ጠላት ባይሆን እንጅ ቢሆን አያስገርምም፡፡   

በሌላ በኩል ግን የባሕርጌ (ባሕር ነጋሽ፣ ኤርትራ) ሰወች ባጠቃላይ ሲታዩ አማራን የሚጠሉት አማራ ቅኝ ገዛን ከሚል በተሳሳተ አመለካከት ላይ ከተመሠረተ የቁጭት ስሜት ብቻ ነው፡፡  ባሕርጋዮች (ማለትም የባሕርጌ ሰወች ወይም ኤርትሬወች) የሚጠሉት አማረኛ ስለሚናገር ብቻ የአማራ ነው የሚሉትን የጦቢያን መንግስትና አስተዳደር እንጅ የአማራን ሕዝብ አይደለም፡፡  ባሕርጋዮች ባጠቃላይ ሲታዩ ማንነታቸውን የአማራን ሕልውና በማጥፋት ላይ ያልመሠረቱ፣ በራሳቸው ማንነት የሚኮሩ ኩሩወች ናቸው፡፡  እርግጥ ነው፣ ባሕርጋዮች የአማራን ሕዝብ እንደ ሕዝብ ዐድጊ ወይም ፀዐዳ አፍንጫ በማለት ሊያንኳስሱ ይሞክራሉ፡፡  ይሄን የሚሉት ግን የቅኝ ተገዛን ቁጭታቸውን ለመወጣት ሲሉ ብቻ ነው፡፡  በተጨማሪ ደግሞ ባሕርጋዮች ቅኝ ገዛን የሚሉትን የአማራን ሕዝብ ዐድጊ ሲሉ፣ ራሳቸውን የዐድጊ ዐድጊ እያሉ መሳደባቸው እንደሆነ ከነሱ የተሰወረ ቢሆንም፣ ከአማራ ሕዝብ የተሰወረ ስላልሆነ፣ በነሱ ዐድጊ መባሉን የአማራ ሕዝብ ከቁብ አይቆጥረውም፣ የአማራ ሕዝብ ማንም ምን ቢለው ንቆ የሚተው በራሱ የሚተማመን ኩሩ ሕዝብ ነውና፡፡

ሻቢያ የሚጠላው የአማራ ነው ብሎ የሚያስበውን የጦቢያን መንግስትና አስተዳደር እንጅ፣ የአማራን ሕዝብ እንደ ሕዝብ አይጠላም፡፡  ስለዚህም ሻቢያ የአማራ ሕዝብ የሕልውና ጠላት አይደለም፡፡  እርግጥ ነው የአማራ ሕዝብ የሕልውና ጠላት የሆኑት ወያኔና ኦነግ ሻቢያ ያሳደጋቸው ውሾች ናቸው፡፡  ሻቢያ እነዚህን ውሾች ያሳደጋቸው ግን የጦቢያን መንግስትና አስተዳደር እንዲያፈራርሱለት እንጅ የአማራን ሕልውና እንዲያጠፉለት አልነበረም፡፡  ለዚህ ደግሞ ወያኔ የአማራን ሕልውና ለማጥፋት ይበጀው ዘንድ በጦቢያ ላይ ያሰፈነውን ጦቢያን በክልል የመበጣጠስ ጎጠኛ ፖሊሲ፣ ሻቢያ በጽኑ መቃወሙን መጥቀስ ብቻ በቂ ነው፡፡

ወያኔና ኦነግ ሻቢያ ያሳደጋቸው የሻቢያ ውሾች ቢሆኑም፣ አሁን ላይ ግን አሳዳጊያቸውን ሻቢያን ለመንከስ ተደራድረው ተመሳጥረዋል፡፡  በሌላ አባባል ወያኔና ኦነግ የፈጠራቸውን ሻቢያን ሊበሉ የተነሱ የሻቢያ ፍራንከንስቲኖች (frankenstein) ሁነዋል፡፡  በመሆናቸውም ወያኔና ኦነግ የአማራ ሕዝብ ብቻ ሳይሆኑ የሻቢያም የሕልውና ጠላቶች ሁነዋል፡፡  ስለዚህም ወያኔና ኦነግ የአማራንና የሻቢያን ሕልውና ተባብረው ለማጥፋት እንደተደራደሩ፣ ፋኖ እና ሻቢያም የወያኔንና የአነግን ሕልውና ተባብረው ለማጥፋት መደራደር አለባቸው፡፡  

ፋኖና ሻቢያ በሕልውና የሚፈላለጉ የሕልውና ጠላቶች ስላልሆኑ፣ ሰጥቶ በመቀበል መርሕ ላይ የተመሠረተ በወያኔና በኦነግ አንጻር የሚቆም የተባበረ ግንባር መፍጠር ይችላሉ፣ መቻልም አለባቸው፡፡  ባሁኑ ጊዜ ደግሞ ይህ ትብብር ይበልጥ የሚጠቅመው በወያኔና በኦነግ አጣብቂኝ ውስጥ ለገባው ለፋኖ ነው፡፡  በመሆኑም፣ ሻቢያን የወጋ ፋኖን ወጋ ብሎ ፋኖ ለጠላትም ለወዳጅም በግልጽ ቋንቋ በይፋ ማወጅ አለበት፡፡  

ለማጠቃለል ያህል፣ የአማራ ሕዝብ ሕልውናውን ማስጠበቅ የሚችለው፣ የሕልውናው ጠላቶች የሆኑትን ወያኔንና ኦነግን በማጥፋት ብቻ ነው፡፡  በመሆኑም፣ ወያኔንና ኦነግን ለማጥፋት ሊያግዘው ከሚችል ከማናቸውም ድርጅት፣ ሕዝብ ወይም አገር ጋር ለመተባበር ቅንጣት ማቅማማት የለበትም፡፡  ይህ ድርጅት ለገዛ ራሱ ሕይወት ሲል ከወያኔና ከኦነግ ጋር የሞት ሽረት ትግል የሚያደርገው ሻቢያ ከሆነ ደግሞ እሰየው ነው፡፡  ከራስ በላይ ንፋስ እንዲሉ፣ ከሁሉም የሚቀድመው ራስን (ሕልውናን) ማዳን ነው፡፡  ወያኔንና አነግን ለመፍጨት እስካገለገለ ድረስ የወፍጮው ምንነት ትርፍ ጉዳይ ነው፣ የትም ፍጭው ዱቄቱን አምጭው ነውና፡፡          

 

መስፍን አረጋ 

mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic