>

ከኦሮሚያ ሰንደቅ አላማ ይስቀላል አይሰቀልም ግጭት የአንድ ተማሪ ህይወት አለፈ...!

ከኦሮሚያ ሰንደቅ አላማ ይስቀላል አይሰቀልም ግጭት የአንድ ተማሪ ህይወት አለፈ…!

በአዲስ አበባ ፈረንሳይ አካባቢ ልዩ ስሙ ጉራራ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በሚገኘው፣ ከፍተኛ 12 ትምህርት ቤት ከኦሮሚያ ሰንደቅ አላማ ጋር በተያያዘ በተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት የአንድ ተማሪ ህይወት ማለፉን አዲስ ማለዳ በወቅቱ በቦታው ከነበሩ ተማሪዎች ሰምታለች፡፡

ከትናንት በስተያ ኀዳር 27/2015 በኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ አላማ ምክንያት በተማሪዎቸ መካከል በተከሰተው ግጭት፣ ከ10 በላይ የትምህርት ቤቱ ተማሪ የመቁሰል አደጋ ጋጥሟቸዋል ተብሏል፡፡ ከተማሪዎች በተጨማሪ አንድ የትምህርት ቤቱ መምህር መጎዳቱን አዲስ ማለዳ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

የግጭቱ መነሻ የኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ አላማ በትምህርት ቤቱ በመሰቀሉ ቅሬታ ባደረባቸው ተማሪዎች፣ የሰንደቅ አላማውን መሰቀል በሚደግፉ ተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ልዩነት ነው ተብሏል፡፡ በዚህም የሰንደቅ አላማውን መሰቀል የማይደግፉ ተማሪዎች እንዲወርድ ፍላጎት ሲያሳዩ፣ በአንጻሩ መሰቀሉን የሚደግፉት ደግሞ ሰንደቅ አላማው አይወርድም የሚል ውዝግ ውስጥ ገብተው እንደነበር ታውቋል፡፡

በግጭቱ ተሳታፊ ያልሆኑ ተማሪች ጭምር ከኹለቱም ወገን በሚወረወር ድንጋይ ቆስለዋል፡፡ በሰንደቅ አላማው ይሰቀላል አይሰቀልም ውዝግ በተነሳው ግጭት፣ ጉዳት ያስተናገዱ ተማሪችን ወደ ህክምና ተቋም ለመውስድ ኹለት አንቡላንሶች በትምህርት ቤቱ ተገኝተው ነበር፡፡

የኦሮሚ ክል ሰንደቅ አላማውን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ት ቤቶች እንዲሰቀል መንግሥት ከወሰነ በኋላ፣ የተለያዩ አካላት ውሳውን ሲቃወሙ ነበር፡፡ ከመቃወምም አልፈው ወደፊት ችግር ሊፈጥር ይችላል በማለት ስጋታቸውን ሲገልጹ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እስከ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ አላማውን በት/ት ቤቶች መሰቀሉን ይቀጥላል ከማለት ውጪ ያሉት ነገር የለም፡፡

Filed in: Amharic