>

አዲስ አበባ ሆይ. . . ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ! (አቻምየለህ ታምሩ)

አዲስ አበባ ሆይ. . . ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ!

አቻምየለህ ታምሩ


የአዲስ አበባ ሕዝብ የእስክንድ ነጋ ጡር አለበት። አዲስ አበባን ከኦሮሙማ ስልቀጣ ለመታደግ ቀድሞ የተነሳው እስክንድር ነጋ በአዲስ አበባ ጉዳይ በኦሮሙማ በግፍ ታስሮ በሚሰቃይበት ወቅት በአንጻራዊነት ይሻለል በሚባለው የአዲስ አበባ ምርጫ ተብዮ ተውኔት ድምጹን ለእስክንድር ነጋ እንዲሰጥ የተጠየቀው የአዲስ አበባ ሕዝብ ድምጹን የሰጠው ስለ አዲስ አበባ በግፍ ለታሰረው ለእስክንድር ነጋ ሳይሆን ዛሬ በግድ ኦሮምኛ እንዲዘምርና የኦሮሙማን አርማ እንዲያውለበልብ ለሚያደርገው ለአፓርታይዳዊው ኦሮሙማ ነበር።

ዛሬ በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በአዲስ አበባ ልጆች ላይ እየተጫነ ያለው የኦሮሙማ መዝሙርና የኦሮሙማ አርማ የአዲስ አበባ ሕዝብ በምርጫው ያገኘው የፍላጎቱ ውጤት ነው። ፈረንጅ ‘Elections have consequences’ እንዲል እነሆ ዛሬ አዲስ አበቤ ከእስክንድር ነጋ ይሻለኛል ብሎ “የመረጠው” አፓርታይዳዊው ኦሮሙማ እያንዳንዱ አዲስ አበቤ ልጆቹን  በኦሮምኛ በግድ እንዲስዘምርና የኦፓርታይዳዊውን ኦሮሙማ የገዳ አርማ ከፍ አድርገው እንዲያውለበልቡ ግዳጅ ተጥሎበታል።

ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ እንዲሉ ዛሬ በየትምሕርት ቤቱ የአዲስ  አበባ ልጆች ኦሮምኛ እንዲዘምሩና የኦሮሙማ አርማ እንዲያውለበልቡ ቢገደዱ የአዲስ አበባ ሕዝብ በእስክንድር ነጋ ላይ ክህደት በመፈጸመ በምርጫ ተብዮው ተውኔት ከነእስክንድር ነጋ ይልቅ አፓርታይዳዊው ኦሮሙማ ይሻለኛል በማለት ያመጣው ስለሆነ በምርጫው ባገኘው ውጤት ጣቱን ወደሌላ አካል ሊጠቁም አይችልም። የኦሮሙማው የአፓርታይድ አገዛዝ የአዲስ አበባ ልጆች ኦሮምኛ እንዲዘምሩና የኦሮሙማን አርማ እንዲያውለበልቡ እያደረገ ያለው የአዲስ አበባ ሕዝብ የመረጠበትን አላማ እያስፈጸመ ነው።

የአዲስ አበባ ሕዝብ ከአጨብጫቢነት በመውጣት አዲስ አበባን ፊንፊኔያቸው ለማድረግ በኦሮምኛ በግድ እንዲዘምር፣ የኦሮሙማን አርማ እንዲያውለበልብና ኦሮሞ እንዲሆን ከሚያስገድዱት ኦነጋውያን መላቀቅ ከፈለገ የኦሮሙማ ናዚዝም ቀድሞ የገባቸውን የነእስክንድር ነጋን መንገድ በመከተል መደራጀትና መታገገል አለበት።

ኦሮሙማ በአዲስ አበባ ላይ እየደገሰ ያለው መከራ እያንዳንዱ አዲስ አበቤ ኦሮምኛ እንዲዘምርና የገዳ አርማቸውን እንዲያውለበልብ ግዴታ በማድረግ ብቻ የሚያበቃ አይደለም። ኦሮሞ አይደለም፤ ወይም ኦሮሞ አይመስልም እያሉ ከአርሲ፣ ከሐረርጌ፣ ከጅማ፣ ከኢሉባቦር፣ ከወለጋ፣ ወዘተ በግፍ እንሚያፈናቅሏቸው ድኆች ሁሉ ኦሮሞ አይደለም ወይም ኦሮሞ አይመስልም የሚሉትን አዲስ አበቤ ሁሉ ነገ በየቤቱ እየዞሩ ከቤቱ አፈናቅለው፤ እድሜ ልኩን ያፈራኸውን ጥሪት ቀምተው ሜዳ ላይ ይጥሉታል።

ይኽንን የሚጠራጠርና በዐቢይ አሕመድ የሚመራው የኦሮሙማ አፓርታይዳዊ አገዛዝ አዲስ አበባ ውስጥ ለማድረግ ስላቀደው አስቀድሞ ይጮኽ የነበረውን እስክንድር ነጋን እንዳበደ ሲቆጠር የነበረ ቢኖር የራሱን ጤነኛነት ይመርመር።

Filed in: Amharic