>
5:33 pm - Saturday December 5, 9237

የጠቅላዩ መሪነት ለዛሬዋ ኢትዮጵያ ወይስ ለነገዋ ኦሮምያ...! (አቻምየለህ ታምሩ)

የጠቅላዩ መሪነት ለዛሬዋ ኢትዮጵያ ወይስ ለነገዋ ኦሮምያ…!

አቻምየለህ ታምሩ

* …. ዐቢይ አሕመድ ጠቅላይ ሚኒስትርነቱ በኢትዮጵያ ፍርስራሽ ላይ እየገነባት ላለችው በኦነጋውያን የደነዘዘ አእምሮ ለተፈጠረችው ኦሮምያቸው እንጂ እያፈረሳት ላለችው ኢትዮጵያ አይደለም!

ኢትዮጵያን እያፈረሰ በፍርስራሻ በኦነጋውያን የደነዘዘ አእምሮ የተፈጠረችውን ኦሮምያቸውን መገንባትን የሙሉ ጊዜ ስራው ያደረገውን ዐቢይ አሕመድን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር እያሉ የሚጠሩ ግብዞች ኢትዮጵያን በማፍረስ የሚተባበሩ የአገርና የሕዝብ ጠላቶች ናቸው። እነዚህ ዐቢይ አሕመድን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር እያሉ የሚጠሩ ሰዎች ባለፊት አራት ዓመታት ውስጥ የቀሩትን የኢትዮጵያ መሰረቶች እያፈረሰ በፍራሹ ላይ በኦነጋውያን የደነዘዘ አእምሮ የተፈጠረችውን ኦሮምያቸውን ከመገንባት በስተቀር ለኢትዮጵያ ምን ሲሰራ አይተውት ነው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር እያሉ የሚጠሩት?

ዐቢይ አሕመድ ባለፉት አራት ዓመታት “የኢትዮጵያ ብልፅግና”፤ “ኢትዮጵያ ታሸነፋለች”፤ “ኢትዮጵያ ትሻገራለች”፤ “ኢትዮጵያ ትበለፅጋለች”፤ “ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር” ፤ “ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ” ወዘተ. . . እያለ  ባፉ እየደለለ በተግባር ግን ሲገነባ የባጀው  በልቡ የተጻፈችውን ኢትዮጵያን የምታክለውን ኦሮምያቸውን  እንጂ በልቡ የሌለችውን የሁሉ እኩል አገር የሆነችውን ኢትዮጵያ አይደለም።

ዐቢይ አሕመድ “የኢትዮጵያ ብልፅግና”፤ “ኢትዮጵያ ታሸነፋለች”፤ “ኢትዮጵያ ትሻገራለች”፤ “ኢትዮጵያ ትበለፅጋለች”፤ “ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር” ፤ “ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ” ወዘተ ሲል በልሳን “የኦሮምያ ብልፅግና”፤ “ኦሮምያ ታሸነፋለች”፤ “ኦሮምያ ትሻገራለች”፤ “ኦሮምያ ትበለፅጋለች”፤ “ኦሮምያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር” ፤ “ፈጣሪ ኦሮምያና ሕዝቦቿን ይባርክ” ወዘተ እያለ ነው።

አንድ ሰው እየገነባው ላለው ቤት እንጂ እያፈረሰው ላለው ቤት አስተዳዳሪ እሆኑም። ዐቢይ አሕመድም ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆነ ጠቅላይ ሚኒስትርነቱ በኢትዮጵያ ፍርስራሽ ላይ እየገነባት ላለችው በኦነጋውያን የደነዘዘ አእምሮ ለተፈጠረችው ለኦሮምያቸው እንጂ እያፈረሳት ላለችው ኢትዮጵያ ሊሆን አይችልም።

Filed in: Amharic