>

ኦሮምኛ እንዲጠላ ያደረገው የኦህዴድ/ኦነግ የማታለል፣  አባገዳዊ የጭፍለቃ ፖሊሲ ....! (ግርማ ካሳ)

ኦሮምኛ እንዲጠላ ያደረገው የኦህዴድ/ኦነግ የማታለል፣  አባገዳዊ የጭፍለቃ ፖሊሲ ….!

ግርማ ካሳ 


ከአራት አመት በፊት አራት የኦሮምኛ ት/ቤት በአዲስ አበባ ተከፈቱ፡፡ ጀነራል ታደሰ ብሩ፣ ዋቆ ጉቱ በሚል ስም ነው ሁለቱ የተቋቋሙት፡፡ ሌሎች ሁለቱ ስማቸውን አላውቅም፡፡ ጀነራል ታደሰ አገርን ያገለገሉ ትልቅ ሰው ነበሩ፡፡ ትምህርት ቤት በርሳቸው ስም ይገባቸዋል፡፡  ዋቆ ጉቱ ግን ከሲያድባሬ ጋር ሲሰራ የነበረ ሽፍታ ነበር፡፡ የኦህዴድ/ኦነግ ፖለቲከኞች  እነ ጀነራል ጃጋማ ኬሎ፣ እነ ባልቻ አባን ነፈሱ፣ እነ ደጃች ገረሱ ዱኪ የመሳሰሉት እያሉ፣ በዚህ ጸረ ህዝብ በሆነ ሽፍታ ስም ትምህርት ቤት ማቋቋማቸው ፣ በራሱ ማንነታቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ አንድ በሉ፡፡

ኦህዴድ/ኦነጎች የኦሮምኛ ት/ቤት ሲከፍቱ፣  በአዲስ አበባ ምክር ቤት ውይይት ተደርጎበት አልነበረም፡፡ በማን አለብኝነት ነበር፡፡ ለምን ሲባሉ፣ “ምን አገባችሁ ? የአዲስ አበባ መስተዳደር መሬት ብቻ ነው የሰጠው፣ የኦሮሞ ክልል መንግስት ነው ለኦሮሞዎች ትምህርት ቤቱን የከፈተው፡፡ የትግራይ ፣ የሶማሌ ክልሎች ከፈለጉ መክፈት ይችላሉ” የሚል ምላሽ ሰጡ፡፡ ዋናው መሰረታዊ የመርህና የሕግ ጥያቄዎች ባለመመለስ ወደ ጎን በማድረግ፡፡ ሁለት በሉ፡፡

በአመቱ፣ እነዚህ ትምህርት ቤቶች ፣  የኦሮሞ ክልል ገንዘብ እንዳይከፍል፣ በአዲስ አበባ መስተዳደር ትምህርት ቢሮ ስር እንዲሆኑ ተደረገ፡፡ ይሄንን፣ ሲያደርጉ፣ በሚስጥር፣ ውስጥ ውስጡን፣ በማታለል፣ ከአዲስ አበባ ምክር ቤት እውቅና ውጭ ነበር፡፡ ከንቲባ ጽ/ቤቱን ፣ የአዲስ አበባ የትምህርት ቢሮ የያዙት ኦህዴዶች ስለነበሩ፡፡ አያችሁ ምን ያህል አታላዮች እንደሆኑ ? ሶስት በሉ፡፡

በአዲስ አበባ 10 ሚሊዮን ሕዝብ ይኖራል ብለን ብናስብ፣ ባለፈው የህዝብ ቆጠራ መሰረት ኦሮምኛ ተናጋሪው 10% ስለነበረ ወደ አንድ ሚሊዮን ኦሮምኛ የአፍ መፍቻው ቋንቋቸው የሆኑ ይደርሳሉ ማለት እንችላለን፡፡ ከዚህ ውስጥ ወደ ትምህርት ቤት የሚሄደው ግማሹ ወይም 500 ይደርሳል፡፡  የመቀሌ፣ የጎንደርን ህዝብ የሚያክል፡፡  ከዚህ ሁሉ ተማሪ በነዚህ ትምህርት ቤቶች ለመማር የሚመዘገብ ጠፋ፡፡ ሌላው ማህበረሰብ ተዉት፣ ከዚህ ሁሉ ኦሮሞ  ሰው በመጥፋቱ፣ ለፖለቲካቸው እንዲያመች፣  ከአዲስ አበባ ውጭ ከነ ቡራዩ ሰበታ ተማሪዎች በባስ ማመላስ ጀመሩ፡፡ ትምህርት ቤቶቹ ሙሉ ናቸው በሚል፡፡  አሁንም ተመልከቱ፣ ምን ያህል አታላዮች እንደሆኑ፡፡  አራት በሉ፡፡

ከነ ቡራዩ የሚመጡት የኦሮሞ ገብሬ ተማሪዎች በአቅራቢያቸው ቢማሩ ነበር የሚሻላቸው፡፡ በቶሎ ተምረው፣ ቤታችው ይገባሉ፡፡ ለማጥናት፣ ወለጆቻቸውን ለማገዝ፣ ለመጫወት ሰፊ ጊዜም ይኖራቸዋል፡፡ በመነገድ አይጉላሉ፡፡ ሆኖ ኦህዴድ/ኦነጎች፣ ለነርሱ ፖለቲካ ብለው የኦሮሞ ልጆች ከሩቅ ቦታ መጥተው እንዲማሩ ማድረጋቸው፣ ሰዎቹ በርግጥም ለድሃው ኦሮሞ ደንታ እንደሌላቸው የሚያሳይ ነው፡፡ አምስት በሉ፡፡

ከሰበታና ከቡራዩ ተማሪዎች በባስ ሲያስመጡ፣ ወጭውን የኦሮሞ ክልል መንግስት አልነበረም የሚሸፍነው፡፡ የአዲስ አባባ የትምህርት ቢሮ እንዲሸፍን ነበር የተደርገው፡፡ ይሁእ ሁሉ ሲሆን፣ ህጉን ተከትሎ፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለው መልኩ ሳይሆን፣ ከህግ ውጭ በማታለልና በማጭበርበር፡፡ ስድስት በሉ፡፡

አሁን በነዚህ ትምህርት ቤቶች ተመዝጋቢ ሲጠፋ፣ ከነ ቡራዩ ብቻ እያመጡ  አዲስ አበባ ኦሮማይዝድ የማድረግ አጀንዳቸውን አምስፈጸም ስለማይችሉ፣ በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች በግዳጅ ኦሮምኛ እናስተምራለን ብለው ተነሱ፡፡ በሺሆች የሚቆጠሩ፣ አማርኛና ሂሳብ ከሚያስተምሩ መምህራን የበለጠ ደሞዝ የሚከፈላቸው የኦሮምኛ አስተማሪዎችን፣  ከነወለጋና አርሲ አስመጡ፡፡ በነጻ ኮንዶሚኒየሞች፣ አዋጦ እጣ ከሚጠብቀው አዲስ አበቤ ነጥቀው ሰጡ፡፡ ይሄንን ሲያደረጉ በማን አለብኝነት፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ሳያውቅ፣ የአዲስ አበባ ህዝብ ሳይጠየቅ የተደረገ ነበር፡፡ በማታለል፡፡ ሰባት በሉ፡፡

ሲጀመር በመቶ ገዳ ትምህርት ቤቶች ነበር ኦሮምኛ ማስተማር የጀመሩት፡፡ አሁን ወደ 4 መቶ አሳድገዉታል፡፡ ነገር ግን ኦሮምኛ ለመማር የሚመዘገው ተማሪ በጣም ትንሽ ነው፤፡ ብዙ የትምህርት ክፍለ ጊዜው፣ 2፣ 3፣ ወይም 4 ተማሪዎች ብቻ ነው ያሉት፡፡ በሺሆች የሚቆጠሩ፣ ከሌሎች ምሁራን የበለጠ ደሞዝ የሚከፈላቸው የኦሮምኛ አስተማሪዎች የሚያስተምሩት 3፣ 4 የሚሆኑትን ነው፡፡ ስምንት በሉ፡፡

ኦሮምኛ የሚያስተምሩ አሉ በሚል ከ4 መቶ በላይ በሆኑ ትምህርት ቤቶች፣ የትምህርት ቤቱ ዋናው ወይንም ምክቱ ኦሮሞ መሆን አለበት ብለው፣ በሁሉም ቦታ ኦሮሞነት ለዳሬክተርነት እንደ መስፈርት ተቀምጦ፣ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፣ ብቃት ያላቸው እያሉ፣ ከወለጋና ከአርሲ የመጡ በአዲስ አበበ ትምህርት ቤቶች ዳይክተሮች ሆነው ተቀመጡ፡፡ ዘጠኝ በሉ፡፡

አዲስ አበባ የኦሮሞ ክልል ናት በሚል፣ የአዲስ አበባ አስተዳደር ነን ብለው፣ መመሪያ ግ ን ከኦሮሞ ክልል ጨፌ ፣ ከአባ ገዳዎች እየተቀበሉ፣ በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የግብጽ የሚመስለውን የአባ ገዳ ባንዲራ ካልተሰቀለ፣  የኦሮሞ ክልል የጥላቸው መዝሙር ካልተዘመረ ብለው የአዲስ አበባ ወጣት እያሸበሩት ነው፡፡ አስር በሉ፡፡

Filed in: Amharic