ለሁለተኛ ጊዜ የታገቱ የደንቢደሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች…!
ሮሀ ሚድያ
በኦሮሚያ ክልል ስር በሚገኘው የደንቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ 9 የአማራ ተወላጅ ተማሪዎች መታገታቸው ተነግሯል።
ተማሪዎቹ የታገቱት ባለፈው ሃሙስ ህዳር 29/2015 ከደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ወደ አዲስ አበባ በኦዳ ባስ በሚጓዙበት ወቅት በምእራብ ወለጋዋ የጊምቢ ወረዳ ጉሊሶ ቀበሌ ውስጥ ነው ተብሏል።
ታጋች ተማሪዎችም:_
1) ቤዛ ተሾመ 5ኛ አመት የአርክቴክቸር ተማሪ ከአዲስአበባ
2) ሰይዳ 5ኛ አመት የመካኒካል ተማሪ ከደባርቅ
3) ማህሌት 4ኛ አመት የማኔጅመንት ተማሪ ከደብረ ማርቆስ
4) ሲሳይ 4ኛ አመት ሳይኮሎጂ ከደብረ ማርቆስ ፣
5) ደጀን 4ኛ አመት ኮምፒቱሽናል ሳይንስ ከ ደቡብ ጎንደር ፣
6) ኪሮስ 5ኛ አመት ሲቪል ኢንጂነር ከባህርዳር ፣
7) ቀኑ መለስ 4ኛ አመት ባዮ ቴክኖሎጂ ከጎንደር ፣
8) ቡዛዬሁ 4ኛ አመት ኮምፒቱሽናል ሳይንስ አከባቢው ያልታወቀ እና
9)ብርሀኑ 5ኛ አመት ሲቪል ኢንጂነሪንግ ከባህርዳር መሆናቸው ታውቋል።
ከሶስት ዓመት በፊት ህዳር 25/2012 ዓ. ም 17 የአማራ ብሄር ተወላጅ ተማሪዎች በኦነግ ሸኔ ታጣቂ ቡድን ታግተው ይኑሩ ይሙቱ ሳይለይ መረሳታቸው ይታወቃል።
ታዲያ ከአመታት በኋላ የአጋች ታጋች ድራማ በማይጠፋበት የኦሮሚያ ክልል በተለይ ደግሞ ተማሪዎች ከዚህ ቀደም የታገቱበት የወለጋው ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዳግም መታገታቸው አነጋጋሪ ሆኗል።