>

አማራ የመቀሌው ሽርሽር እንዴት ማየት አለበት? (አሸናፊ)

አማራ የመቀሌው ሽርሽር እንዴት ማየት አለበት?

አሸናፊ


ባለፉት ሁለት አመታት በተካሔደው ጦርነት ዋና ተጠቂ የነበሩት ክልል አፋር እና አማራ ክልል ናቸው። እነኝ ክልሎች ቀድም በነበረው የህወሀት መራሹ ኢህአዴግ ዘመን ከፍተኛ በደል የደረሰባቸው ናቸው። በተለይ አማራ ክልል እድሜ ለነበረከት ስምን የአይምሮ ዘገምተኛ የሆኑ በገዛ ህዝባቸው ላይ መከራን ሲያወርድ የነበሩ የብኣዴን አባሎች ስብስብ ናቸው። በሎሌነት ማስተርስ የጫኑ የሰው ከንቱ ስብስብ ናቸው። መቼም የማይማሩ የህዝብ ጥቅም የሚባል የማይገባቸው ገረዶች ናቸው።
የማዝነው ዛሪም ገሚሶቹ በአብን ስም የተኮለኮሉትን እነሱ መሆናቸው ነው። አንድም ቀን እረ ግፍ በቃ ብለው የማያውቁ ትህነግ  የተጋጠ አጥንት  ሲወድቅ ጠብቀው ሲግጡ የከረሙ ናቸው። ክርስቲያን በለው በቀለ  በለው ጣሂር በለው ሁሉም ልቅምቃሚ እንክርዳድ አማሮች ናቸው። እነኝ እና ብአዴን ሙታኖችን ጀግና ጀግና ሲያጫውታቸው ሳይ በእውነት እንደህዝብ ምን ነክቶት እንደሆነ ግራ ያጋባል። ሲለው 55 ሚሊዮን ነኝ የሚል ህዝብ አንድ እንኳን የትህነግን ሾርባ ያልጠጣ ለመብቱ የሚከራከርለት መሪ ያጣል?
ወደ ጹሑፌ አላማ ልመለስና አሁን እየተካሔደ ያለው ድርድርን የመቀሌውን ሽርሽር አማራው በምን መነጽር ነው ማየት ያለበት ነው?
ማንኛውም ጦርነት ማክተሚያው ድርድር መሆኑ እሙን ነው። ዶር አብይና ካቢነው መቀሌ ሄድ ብሎ መናደድ ወይም ተጣሉ ብሎ መደሰት ለአማራ ምንም አይጠቅመውም ጉዳዬን ከዶ.ር አብይ ባሻገር ማየት ካልተቻለ ትርጉም የለውም። መጀመሪያ ይህን ጦርነት ለምን በሙሉ አቅሙ ተሳተፈበት? ለአብይ ብሎ ወይስ ትህነግ በሀገሩ በነጻነቱ ህልውና ስለመጣ? የዚህ መልሱ የአብይን መንግስት ለማቆም ከሆነ እንግዲ ለራሱ ማርክ ይስጥ። ነገር ግን ለነጻነቱ ለሀገሩ ብሎ ከሞተ ከቆሰለ ከዘመተ ውጤቱ እጅግ በጣም ጥሩ ባይባልም በጣም ጥሩ የሚባል ነው። ምክንያቱም ሀገሩን አትርፏል ዳግም ባርነትን ገለል አድርጓል። እራሱን የአለማችን አንበሳ አድርጎ የሚቆጥረውን ትህነግን የራበው ብችላ እንደሆነ አሳይቶታል ወልቃይት በእጅ አስገብቷል። በነዚህ ሁላ መስፈርት አማራው አሸናፊ ነው። ስነ ልቦናው በዚህ በኩል ነው መቃኝት ያለበት።
ዶ.ር አብይ መንግስት  በህገመንግስቱ ቢልም በየሜዳው እየወጣችሁ ከመለፍለፍ መሪት ላይ ወርዶ ተጨባጭ የሆነ ነገር መስራት ነው። ለህዝበ ውሳኔ መዘጋጀት ለዚህም  ከሲዳማ ትምህርት መውሰድ ይቻላል። ዶር አብይ ሊያግዝህ የሚችለው አንተ ጠንክረህ ስትሰራ የትህነግን ተንኮል ቀድመህ ተንትነህ ስትመክት ብቻ ነው።
በህግ ከተባለ ህጉ የሚፈልገውን አዘጋጅቶ በጦርም ከተባለ እራስን አዘጋጅቶ መጠበቅ ነው። ከዚያ ውጭ ታደሰ ጫፎ ተቃቀፈ ዳግማዊት ተሳሳመች እያልክ እየዞርክ እንደመንደር ሴት አትብከንከን።  ጠንከር ማለት ነገን አሻግሮ ማየት የህወሀት ተላላኪዎች መለየት በአይነ ቁራኛ መጠበቅ። የመለያየት አደጀንዳ የሚያወሩትን ማግለል።
ለህወሀት ምቹ ያልሆነ ሜዳ መፍጠር ይገባል። ምክንያቱም ወያኔ ወደ ቀድም ስራዋ መመለሷ ስለማይቀር። አንተ ስትጠነክር ያኔ ዶር አብይ ከጎንህ ታገኝዋለህ።  ምክንያቱም የትህነግን ባህሪ ጠንቅቆ ያቀዋል ትህነግ ቂመኛ ነች እንኳን ገደል ለገደል አሯሩጧት ደም በደም አድርጓት በሰላም የተቃወማትን ምን እንደምታደርግ ጠንቅቆ ያውቃል። እመነኝ ጦርነቱ እንደተጀመረ የአብይ አንገት ቆርጠን እናመጣለን ሲሉ ለማለት እንዳላሉ ጠንቅቆ ያቃል። ምክንያቱም የሀጢያታቸውን ጥግ በቦታ ሆኖ ያየ ሰው ነው። መቼም እንደማይተኙለት ያውቃል። እንኳን ወልቃይት አዲስ አበባን ቢሰጣቸው እንደማይለወጡ ያውቃል። ከንተ ከጀገንክ እሱ አንተ ጎን ታገኝዋለህ። የቤት ስራህን ስራ።
Filed in: Amharic