>

ድምፃዊ ቴዲዮ ገርጅ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ተይዞ በፌድራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰማ! (አሻራ. ሚድያ)

ድምፃዊ ቴዲዮ ገርጅ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ተይዞ በፌድራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰማ!

አሻራ. ሚድያ


ድምፃዊ ቴዲዮ ዛሬ ታህሳስ 21 ቀን 2015 ዓ.ም ገርጂ የሚገኘው መኖሪያ ቤቱን ፌድራል ፖሊስ በመክበብ ወደ 3ኛ ፖሊስ እየተወሰደ እንደሆነ ከቦታው የሚገኙ ምንጮች ለአሻራ ሚዲያ ገልፀዋል።«የወንዜ የወንዜ» የሚለውን አዲስ ዘፈን  በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ ያተኮረ በመሆኑ ለእስሩ ምክንያት እንደዳረገው ምንጮች ተናገሩ።

ወቅቱን የዋጀ የህዝቡን መገፋታት፣ መጨቆን፣ አንገት መድፋት፣ መዘረፍ፣ መበዝበዝን በሙዚቃው በመቃኘት በተለይም አራት ኪሎ ላይ ያለውን ስልጣን ያለአግባቡ በመጠቀም አሁን ያለውን የኢትዮጵያ መንግስት ቁመት ቁልጭ አድርጎለመላው አለም አሰምቷል።

ስለ አዲስ አበቤ ስቃይ ማን ዘፍኖ  ድምፁን አሰምቶ ታሰረልን። ስለ እኛ ስቃይ ጮኸልን ብለዋል የመረጃ ምንጫችን።

ወንበርሽ በሚለው የቴዲዮ ሙዚቃ ውስጥ የሚከተሉት ስንኞች «የወንዜ የወንዜ የወንዜ አራት ኪሎ… ወንበርሽ ይፋጃል ጠፋ ሁሉን ችሎ ብሎ በዘፈነው ዘፈን ለእስር እንዳበቃው ተገልጿል።

https://youtu.be/bysBhXz4XaM

Filed in: Amharic