>

ታዴዎስ ታንቱ ኦሮሞ ዳኞች ከችሎት እንዲነሱላቸው ጠየቁ (ጌጥዬ ያለው)

ታዴዎስ ታንቱ ኦሮሞ ዳኞች ከችሎት እንዲነሱላቸው ጠየቁ

 

ጌጥዬ ያለው


ሀቀኛው ጋዜጠኛ እና የታሪክ ፀሃፊ ጋሽ ታዴዎስ ታንቱ ከአንድ ወር በኋላ ዛሬ ታህሳስ 21 ቀን 2015 ዓ.ም. የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የፀረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ቀርበዋል። አዛውንቱ ጋዜጠኛ ኦሮሞ ዳኞች አድሏዊ መሆናቸውን ጠቅሰው ብሎም በእነርሱ መዳኘት እንማይፈልጉ አስረድረተው ከችሎት እንዲነሱላቸው ጠይቀዋል። በዚህም የዳኛ ቅያሪን በተመለከተ ብይን ለመስጠት ችሎቱ ለታህሳስ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ዳኛን ማስቀየር የተከሳሽ ሕገ መንግሥታዊ መብት መሆኑ ይታወቃል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ጋሽ ታዴዎስ በቀረቡባቸው አራት ሀሰተኛ የሽብር ክሶች ላይ የሰው እና የሰነድ መከላከያ ምስክሮችን እንዲያቀርቡ ችሎቱ አዝዟል። በዚህም መሰረት ፖሊስ እሳቸውን ሲያስር ከሳምሶናይት ቦርሳቸው ውስጥ የነበሩና ነጥቆ የወሰዳቸውን እንዲሁም በቤት ብርበራ ጊዜ የወሰደባቸውን የሰነድ ማስረጃዎች ታህሳስ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. ለችሎቱ እንዲያቀርብና ጋሽ ታዴዎስ ከክስ መከላከያነታቸው አንፃር ሰነዶቹን እንዲያብራሩ ታዝዟል። ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቤተ መፅሀፍትና ቤተ መዛግብት ኤጀንሲ (ወመዘክር) ከተለያዩ መፅሀፍተ ያጣቀሷቸውን የታሪክ ማስረጃዎች እንዲያቀርቡ ደግሞ ለጥር 6 ቀን 2015 ዓ.ም. ተቀጥሯል። ለዚህም ቂሊንጦ ወህኒ ቤት በፖሊሶች አጅቦ ከእስር ቤት ወመዘክር እንዲያመላልሳቸው ታዝዟል።
በቀጣዮቹ ቀናት ደግሞ ከኢትዮጵያ ውጭ የሚኖሩ የሰው ምስክሮች በድምፅና ምስል አቀራረብ ቴክኖሎጂዎች ታግዘው የታሪክ እውነታዎችን ለችሎቱ ያስረዳሉ።
አዛዎንቱ ጋዜጠኛና የታሪክ ፀሃፊ ጋሽ ታዴዎስ ታንቱ ከግንቦት 10 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ በግፍ እስር ላይ ይገኛሉ።
Filed in: Amharic