>

ማን ገደለው?  (ዘመድኩን በቀለ)

ማን ገደለው?

ዘመድኩን በቀለ

“…ይሄን የነፃው ፕሬስ መሥራች ቀንዲል፣ አማኝ ጿሚ ጸሎተኛ፣ ጥብቅ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን፣ ባለ ብዙ ዲግሪ ባለቤት፣ የሸዋ ኦሮሞ እንደሆነም የሚነገርለትን የማይክሮ ሊንክ ኮሌጅ ባለቤት አቶ ዳኛቸው ይልማ ነው። አቶ ዳኛቸው ይልማን ማን ገደለው? እንዴትስ ሞተ?

“…ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌናስ የሟቹ ጓደኞች የነበሩትን የነጻው ፕሬስ ፕሬዚዳንት ጋዜጠኛ ክፍሌ ሙላትን እና የነጻው ፕሬስ አባል የነበረው የሟች አቶ ዳኛቸው ይልማ የቅርብ ጓደኛ የነበረውን አቶ ብሩክ ዶሜኒክን ኢንተርቪው ካደረጋቸው በኋላ እና አቶ ብሩክን ዳኛቸው ታሞ ነው የሞተው እንዲል ገፊ ጥያቄዎ

ችን ሲያቀርብለት የሚያሳየውን ቃለ መጠይቅ ለምን ከኢሳት የዩቲዩብ ቻናል ላይ እንዲወርድ አስደረገ?

“…ሁለት ልጆቹንና ባለቤቱን በጥሩ ሁኔታ በሚያኖርበት አሜሪካ ቨርጅኒያ አስቀምጦ የዐቢይን ና ና የሚል ቃል አምኖ ከግማሽ ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጣ ሰርቨር ይዞ በሚዲያ ሙያ ላይ ለመሠማራት ወደ ሃገር ቤት የገባውን ጋዜጠኛና ምሁር ማን በላው?

“…የማይክሮ ሊንክ ኮሌጅ መስራች የነበረው አቶ ዳኛቸው ይልማ ብቸኛው የዐቢይ አህመድ የማይክሮ ሊንክ ሰርተፍኬት ጉዳይ ዐዋቂም ነበር ይባላል። ጀምሬአለሁ እጨርሰዋለሁ። በዝርዝር ከተፈለገም ጥያቄዬን ቦርቀቅ አድርጌ ማቅረብ እችላለሁ።

“…ና ና ግባ ግባ ብሎ አጣድፎ ካስመጣው በኋላ ዳኛቸውን ማን በላው? በዘመነ ወያኔ ጊዜ የወያኔ ተቃዋሚ የነበሩት በሙሉ ለውጥ መጥቷል ብለው የዐቢይ አሕመድን ምላስ አምነው ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በመርዝ፣ በመኪና አደጋ፣ ልቤን ብለው፣ ደም ተፍተው የሞቱትን በሙሉ ማነው የሚፈጃቸው።

“…ወያኔ፣ ሻአቢያ፣ ግንቦት ሰባት፣ ኦነግና ኦህዴድ ብአዴን ድምጽ አጥፍተው ያለ ተቃውሞ እየፈጁት ነው የሚሉ መተርጉማንም አሉ።

Filed in: Amharic