ተገንጣዩ ሲኖዶስ አስተዳደራዊ እርምጃ ተወሰደበት….!
ሮሀ ሚድያ
*… በጠቅላይ ቤተክህነት ጊቢ ያላቸው መኖሪያ ቤት ታሸገ
የአስተዳደር ጉባኤ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አስተዳደራዊ ውሳኔዎ ችን ወስኗል።
የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጠቅ ላይ ቤተ ክህነት የአስተዳደር ጉባኤ ዛሬ ማለዳ ላይ ባደረገው ስብስባ ትናንት ጥር 14 በወሊሶ ከተማ በተደረገው ሕገ ወጥ ሢመት:-
ራሳቸውን ኤጴስ ቆጶሳት ብለው በገለጡ ከተለያዩ አድባራት እና ገዳማት በተውጣጡ ፳፮ መኖኮሳት ላይ አስተዳደራዊ ውሳኔ አስተላልፏል።
በዚህ መሠረት:-
፩ኛ .ሁሉም መነኮሳት ከደመ ወዝ ታግደው እንዲቆዩ
፪ኛ. የሚያንቀሳቅሱት የገዳማት እና አድባራት ሂሳብ ካለ እንዲታገዱ
፫ኛ. ከዚህ በፊት ወደሚያገለግሉት የአገልግሎት መዋቅር እንዳይመለሱ
፬ኛ.በየትኛውም የኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አድባራት እና ገዳማት እንዳይገኙ ውሳኔ አስተላልፏል።
ፍትሕ መንፈሳዊ ውሳኔዎችን በተመለከተ ደግሞ ቅዱስ ሲኖዶስ ቀጣይ በሚያደርገው ስብሰባ ይወስናል ተብሎ ይጠብቃል።
ታሽጓል:-
“26 ጳጳሳትን ከወሊሶ ሾመናል ሲኖዶስም መስርተናል” ያሉት 3 ሊቃነ ጳጳሳት ጉዳያቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ታይቶ እስኪወሰን ድረስ ማረፍያ ቤታቸው ታሽጓል።
ስንዴው ከእንክርዳዱ የሚለይበት ዘመን መጥቷል። ተዋህዶ ይበልጥ ጠንክራ ለጠላቶቿ እሳት የምትሆንበት ጊዜ ደርሷል። ልጆቿም ጠንካራና ለክብሯ የሚዋደቁ ይሆናሉ። እመነኝ አንተ ትጠፋ ይሆናል እንጂ ተዋህዶ አትፈርስም!