>

የ2014ቱ ብሄራዊ ፈተና ይመርመር!!

የ2014ቱ ብሄራዊ ፈተና ይመርመር!!

ጌጥዬ ያለው

—-ከመምህራን እና ተማሪዎች ስብስብ

—-በ2014 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን የተፈተኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤት ይፋ ተደርጓል። 


ሆኖም፣ ሁሉም ተማሪዎች ለማለት በሚጠጋ ደረጃ፣ ከግማሽ ያነሰ ውጤት አስመዝግበዋል። እንደ ሪፖርቱ ከሆነ፣ በኢትዮጵያ አቀፍ ደረጃ ከተፈተኑት 896, 520 ተማሪዎች መካከል ግማሽና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡት 29, 909 ተማሪዎች በቻ ናቸው። 
ይህም በመቶኛ ሲሰላ፣ 96.7 ከመቶ ያህሉ ከግማሽ ያነሰ ውጤት አስመዝግበዋል ማለት ነው። 96.7 ለ100 ቅርብ ነውና፤ በሒሳብ የአቅራብ ስሌት መሰረት ሙሉ በሙሉ ለማለት በሚያዳዳ ደረጃ ተማሪዎች አነስተኛ ውጤት አስመዝግበዋል። 
እውን ተማሪዎች በዚህ ደረጃ ወድቀዋል? ወይስ ፈተናው ችግር ነበረበት? 

ምንም እንኳን የትምህርት ስርዓቱ  ድክመት የገዘፈ መሆኑ እሙን ቢሆንም፣ የተጋነነ ከሚመስለው አነስተኛ ውጤት አኳያ ቁርጥ ያለ ብያኔ ለመስጠት እንዲያስችል፣ ፈተናው ፍታዊ ነበር? ወይስ ያለ አግባብ የከበደ ነበር? የሚለው ጥያቄ በገለልተኛ አካል በአፋጣኝ ሊመረመር ይገባዋል። 
አዳዲሶቹ የትምህርት ሚኒስትር ባለስልጣናት የትምህርት ስርዓቱ የተበላሸ ነው የሚል ጥብቅ አቋም አላቸው። ትክክልም ናቸው። 
ሆኖም፣ አቋማቸው አካዳማዊ ብቻ ሳይሆን ፖለቲካዊ ይዘትም አለው። ሀገራዊ አቅጣጫ ከማስቀመጥ አኳያ፣ የትምህርት ፖሊሲ ፖለቲካዊ ይዘትም አለውና፣ ይህ በራሱ ችግር የለውም። 
ሆኖም፣ ችግሩን በአግባቡ ማወቁ የመፍትሄው ግማሽ አካል ነውና፣ ባለስልጣናቱ ፖለቲካዊ አቋማቸውን የሚያረጋግጥላቸው ከበድ ያለ ፈተና አውጥተው ቢሆንስ? ተብሎ መጠየቁ እና መመርመሩ ፣ የተሻለ የትምህርት ፖሊሲ ለመቅረፅ በሚሰራው ላይ ወሳኝ እንደምታ አለው። የተማሪዎቹ ቁመና በትክክል ሲታወቅ ብቻ ነው ለችግሩ መፍትሄ የሚሆን አዲስ የትምህርት ካሪኩለም መቅረፅ የሚቻለው።
በየትኛውም የተበላሸ የትምህርት ስርዓት ባለባቸው ሀገራት እንዲህ ዓይነት ዝቅተኛ ውጤት ተመዝግቦ አያውቅም። በየትኛውም ቦታ ቢያንስ 10 ከመቶዎቹ በራሳቸው ጥረት ማንኛቸውንም ሚዛናዊ ፈተና ማለፍ እንደሚችሉ ከዓለም አቀፋዊው ልምድ ይታወቃል። የ2014ቱ ውጤት ይህን እውነታ በሰፊ ልዩነት ይፃረራል። ይህ ቆም ብለን እንድናስብ ሊያደርገን ይገባል። 
ስለዚህም፣ የ2014ቱ ፈተና አስቀድሞ ሙያዊ ፍተሻ ይደረግበት። አሁን ተገኘ የተባለውን ውጤት እንደወረደ መቀበል አይቻልም። 
በመጨረሻም፣ በሌሎች ሀገራት እንዲህ ዓይነቱ ችግር እንደሚከሰት ታች ያለው የቪኦኤ ዜና ያሳየናል። ችግሩ ሲከሰት እነሱ ያስተካክሉታል። ችግሩ ካለ፣ እኛም ከእነሱ ተምረን እናስተካክለው።—-VOA News—-May 06 2018 —-German Students Protest ‘Unfair’ English Exam—-Thousands of German students are accusing school officials of creating an English exam that was “unfairly” difficult.
The exam is important because it is part of Germany’s Abitur system. The Abitur test is given to students who are completing high school and preparing to enter college.
More than 35,000 people have signed a petition to voice their concerns about the test which was recently held in the state of Baden-Württemberg.
The students say the English part of the 2018 Abitur was clearly more difficult than tests given in recent years. They are calling on school officials to consider their criticisms while judging student performance and giving test results. School officials have defended the test. The said the questions were “appropriate” for the students.

Filed in: Amharic