>

የኢትዮጵያ ትንሳኤዋም አፍንጫችን ስር ነው። ይብላኝ ለእናንተ ድንጋይ አቀባዮች። (መምህር ዘመድኩን በቀለ)

የኢትዮጵያ ትንሳኤዋም አፍንጫችን ስር ነው። ይብላኝ ለእናንተ ድንጋይ አቀባዮች።

መምህር ዘመድኩን በቀለ

ዳይ ያዝ እንግዲህ…!

“…በነገራችን ላይ አክራሪ የኦሮሞ እስላሞቹና አክራሪ ፅንፈኛ የኦሮሞም፣ የደቡብም የዐማራም ጴንጤዎቹ በኦሮሚያ በይፋ በኦሮሚያ ፖሊስ እና በመከላከያ ሠራዊት በመታገዝ ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን የኢትዮጵያ ባንዲራ በይፋ ማውረድ ጀምረዋል።

“…ኢዜማዎች (ግንቦት ሰባቶች) ተቃዋሚ ተደማሪ ተደጋፊ ፓርቲዎች፣ የዐቢይ አሕመድ ደጋፊ ሳይሆን አምላኪዎች፣ አሸርጋጅ፣ ጫማ ላይ ተደፊ ገረዶች። የአዳነች አቤቤ አሽከሮች፣ ኢሳት፣ ኢኤምኤሶች፣ እነ ደረጀ ሀብተወልድ፣ ሲሳይ አጌና፣ ፋሲል የእኔዓለም፣ አቶ ግዛው፣ ጴጥሮስ፣ መሳይ መኮንን፣ አበበ ገላው፣ ታማኝ በየነ የአቢይ ፕሮፓጋንዲስቶች እንኳን ደስ አላችሁ። ከዐቢይ ጎን ቆማችሁ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ድጅኖ ያቀበላችሁ በሙሉ እንኳን ደስ ያላችሁ።

“…ብአዴኖች በተለየ ሁናቴ እንኳን ደስስ ያላችሁ። የህወሓትማ ምን ይነገራል? ለማንኛውም እንኳን ደስስ ያላችሁ። በዐቢይ ምክንያት በፍቅሩ ወድቃችሁ እሱን አትንካብን ብላችሁ የእርግማን መዓት ስታወርዱብኝ የከረማችሁ በሙሉ እንኳን ደስ ያላችሁ። ከገዳዮች እኩል፣ ሃገር ከሚያፈርስ እኩል ብድራታችሁን ፈጣሪ ይስጣችሁ።

“…ሃዘን በቤታችሁ ይግባ፣ እሳት ይልቀቅባችሁ። እርፈት ያሳጣችሁ። የሃዘን ድንኳን ከቤታችሁ አይነቀል። ባላችሁበት ያባክናችሁ። ሃሳብ ጭንቀት፣ ትካዜን እንደ ሸማ ያጎናጽፋችሁ። ፀፀት ያመንምናችሁ። የኢትዮጵያ አምላክ ሃገር ያሳጣችሁ። ተንከራተቱ፣ ዘራችሁ እህል ይለምን። አሜን ነው? አሜን በሉ።

“…ለኢትዮጵያ ግን መድኅኗ ከሆነ ቦታ ይመጣል። ይነሣልም። የኢትዮጵያ ትንሳኤዋም አፍንጫችን ስር ነው። ይብላኝ ለእናንተ ድንጋይ አቀባዮች። ለማንኛውም እንኳን ደስ አላችሁ

አንድ ለኢትዮጵያ ሺ ለጠላቱን ተከተሉት


https://t.me/ZemedkunBekeleZ
https://t.me/ZemedkunBekeleZ

Filed in: Amharic