>

ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ በ1876 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ፊደል ወደ ኦሮሚፋ ያስተረጎሙት መጽሐፍ ቅዱስ!(አቻምየለህ ታምሩ)

ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ በ1876 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ፊደል ወደ ኦሮሚፋ ያስተረጎሙት መጽሐፍ ቅዱስ! 

አቻምየለህ ታምሩ

ዐቢይ አሕመድ ያቋቋመው የኦሮሞ ሲኖዶስ የኦሮሞ ሕዝብ የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነቱን  በኦሮሚፋ እንዲፈጽም ከማድረግ ጋር የሚያገናኘው አንዳች ነገር የለም። በዐቢይ አሕመድ የተቋቋመው የኦሮሞ ሲኖዶስ ዋና አላማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ማጥፋትና ኢትዮጵያን አፍርሰው በኦነግ የደነዘዘ አእምሮ የተፈጠረችውን ኦሮምያቸውን አገር አድርገው ለመፍጠር ነው።  

የኦሮሞ ሕዝብ የትኛውንም እምነቱን በኦሮሚፋ እንዳይፈጽም የተከለከለበት ዘመን ኖሮ አያውቅም። የኦሮሞ ሕዝብ ሃይማኖቱን በቋንቋው እንዲፈጽም ሲያደርጉ የኖሩት ከሁሉ በፊት የኢትዮጵያ ነገሥታት ናቸው።  መጽሐፍ ቅዱስ ወደ አማርኛ ሳይተረጎም ወደ ኦሮምኛ እንዲተረጎም ያደረጉት ኦነጋውያን ላለፉት ሃምሳ ዓመታት ሲዘምቱባቸው የኖሩት ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ናቸው። 

ከላይ የሚታየው የመጽሐፍ ቅዱስ ሽፋን ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ አለቃ ዘነብን ቀጥረው፣ ለትርጉም ስራው የሚያስፈልገውን ማናቸውንም ወጪ መድበው በኢትዮጵያ ፊደል ወደ ኦሮሚፋ እንዲተረጎም ያደረጉት የመጀመሪያው የኦሮሚፋ ቋንቋ የአዲስ ኪዳን መጽሐፍ ቅዱስ ነው። 

ልብ በሉ! ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ይህንን ያደረጉት መጽሐፍ ቅዱስ ወደ አማርኛ ከመተርጎሙ ከኀምሳ ዓመታት በፊት ነው። ኦነጋውያን ሲዘምቱባቸው የሚውሉት ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ የኦሮሞ ሕዝብ ክርስትናን በኦሮሚፋ ቋንቋ እንዲማር መጽሐፍ ቅዱስን ወደ አማርኛ ቋንቋ ሳያስተረጉሙ ወደ ኦሮሚፋ እንዲተረጎም ያደረጉትን ንጉሠ ነገሥት ነው።

Filed in: Amharic