ከፍተኛ ውለታ የዋለች ቤተክርስቲያንን በማሳዘን ምን ታገኛለህ?!
ሙክታሮቪች ኡስማን…!
“…የምድሩን አድሎ ተወልህ፣ ሁለተኛ ዜጋ ነህ ስትለው ተቀበለህ። ሀገር አደጋ ላይ ስትወድቅ ና ስትለው መጣልህ። የባለስልጣኖችን ሌብነት ቻለልህ። የኑሮ ውድነቱን ተሸከመልህ። ቆሎ ቆረጠመ። ምን እድርግ ነው የምትለው? የምድሩ ኑሮ ሰቆቃ ሆነ።
” ማልቀሻውን፣ መለመኛውን፣ የሰማዩን፣ የነፍሱን ማረፊያ እንዴት ልትነሳው ትደፍራለህ? ፍትሀት እንዴት ትነሳዋለህ? መቀበሪያውን እንዴት ትነሳዋለህ? ጭካኔ አይደለምን? ምንድነው የምትፈልገው? የኢትዮጵያ ህዝብ የጠየከውን ሁሉ ሰጠህ። የቀረ ምን አለ? ምን እንስጥህ? ምን ቀረን? ምንድነው ፍላጎትህ? የኢትዮጵያ መሰረት የሆነች፣ ታሪክ ከትባ ያኖረች፣ ሀገርን ከነክብሯ፣ ፊደልን ከነቁጥሯ ለትውልድ የሰጠች፣ የብዙ ሚስጢራት ዋሻ የሆነች፣ ለእስልምና የዛሬ ቁመና ከፍተኛ ውለታ የዋለች ቤተክርስቲያንን በማሳዘን ምን ታገኛለህ?
መጥኔ‼