>
5:21 pm - Thursday July 20, 7369

አብይ ሸወደን አልሸወደን ልዩነት የለውም! (በፍቃዱ አላምረው)

አብይ ሸወደን አልሸወደን ልዩነት የለውም !

በፍቃዱ አላምረው

– ስምምነት ማድርጋቸውንስ ለምን  መደበቅ ፈለጉ? ይሄ ነገርስ. ምን ያመለክታል

እስከ እሁን ድረስ ቤተ ክርስቲያንን በተመለክት:  የነ አብይንና ሺመልስ አብዲሳን ድንፋታዎችን: የፌዴራል  መንግስት ኮሚኒኬሽን በጉዳዩ ላይ የሚያወጣን እንቱፈንቶ  የማስፈራራት መግለጫዎች በስፋት የዘገቡት የመንግስት ሜዲያዎች ለሲኖዶሱ ምንም እይነት ሽፋን አልሰጡም:: አሚኮንም ጨምሮ:: ያ በራሱ  ያስመዘገበው ትልቅ ድል   አለ:: የበለጠ ማንነታቸውና ድንቂርናቸው: አምባገነናዊነታቸው እንዲታወቅ አድርጏል::

አብይ እህመድ የሲኖዶሱን ጥያቄዎች በሙሉ መቀበሉን: ያንን ተከትሎ ሲኖዶሱ የሰጠውንም  መግለጫ  አነበቡክ:: ከመንግስት  ሜዲያዎች  አሚኮ ዘግቦታል:: ሌሎቹ ዝም እንዳሉ ነው::

በጉዳዩ ላይ እነ አብይ  አህመድ   : የኮሚኒኬሽን ሚኒስትሩ  ይሄ ጦማር እስከተፃፈበት ጊዜ ጀምሮ  ያሉት ነገር የለም:: ለምን ስምምነቱን ከህዝብ  መደበቅ ፈለጉ??? እስከ አሁን አንድም የመንግስት አካል ምንም ያለው ነገር የለም::  ከአማራ ክልል  መንግስት  በስተቀር:: 

የፌዴራል  መንግስቱ   እነ አብይ አህመድ ይሄን አልተስማማንም  ብለው  ቢክዱ: የአማራ ክልል መንግስት በጉዳዩ ላይ የሰጠውን መግለጫ  ማቅረብ ይቻላል::

ያም ሆነ ይህ በዋናነት የቤተክርስቲያንን ጥያቄ ያቀረብነው ለመንግስት ነው። በእኛ በልጆቿና  በቤተክርስቲያን አስተሳሰብ መንግሰት ማለት  የሀገሩ ገዥ ማለት ነው።

የሀገሩ ገዥ ደግሞ ህግና ስርዓት ነው። ህግና ስርዓቱን አምነን በሁለት ቀናት ውስጥ ህግና ስርዓቱን  ለመተግበር ምለው ተገዝተው  ስልጣን ወደ ያዙ ቄሳሮች ጥያቂያችን እንዲመለስ በግልፅ  አቅርበናል። አባቶቻችን በግልፅ የነበረውን ሸፍጥ ገላልጠው ያዩትን አንድናይ አድርገው ያየነውን አይተው ፤ የሰሙትን አሰምተውን የሰማነው ሰምተው ከአንባገነን መንግስት ጋር አንገት ለአንገት ተያይዘዋል። በምን?  በፆለት በህግና በስርዓት

አብይ አህመድ አሊ የተኮፈሰውን እብሪቱ ተንፍሶ የምትሉኝ ሁሉ አደርጋለሁ ብሏል። (በነገራችን አባቶቻችንላይ እነ አካለ ወልድን ለመክዳት አብይ ደቂቃ አይወስድበትም። ምክንያቱም በእነሱ ሔዶ የሚያፀናውን ስልጣን ሊያጣ ጫፍ ደርሶ ስለነበረ አሁን እነ አቡነ አማትያስን አክብሮ ባይሆን እንኳን ተገዶ ስልጣኑን ለማቆየት የእነ ሳዊሮስ ቡድንን ከማሳደድ ወደ ኋላ አይልም።  አላማው ስልጣኑን ማቆየት ከሆነ )  ቅዱስ ሲኖዶስ  የምንልህን ለማድረግ ሁለት ቀን ሰጥተናል ብለውታል። ጊዜ እፈልጋለሁ ብሏል። ያ ። ጊዜ ከልዩ ጥንቃቄ ጋር ተሰጥቶታል።

ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ የተነሳው  የምንለው መንግስት ፕሮጀክቱን ከቀጠለበት ነገ የሚፈርሰው እሱ ነው። በምድር ያለውን ሁሉ ሴራና ውስብስብ መንገድ ቢጠቀም የነቃና የበቃው ትውልድ ከአባቶቹ ጋር ሆኖ የሚተወዉ አይደለም።  ጥያቄው ለመሆኑ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ነቅትናል ወይ ነው ? ተደራጅተንና ነቅተን ሀገር ርነጠብቃለን ወይ ?

ዶ/ር አብይና መንግስታቸው ለመሸውድ አስበው ከሆነ ችግርን ለነገ እነንዳሳደሩል ይወቁት። እስከዛው ንስሃ ገብተን እምነትን አፅንተን ፖለቲካችንን አርቀን ተደራጅተን እንጠብቃቸዋለሁ። 

ካልሸወዱንም እሳቸው አምላክ አይደሉምና በእሳቸው ቀጥተኛ ትዕዛዝም ሆነ በረከት የሚቃና አንዳች የቤተክርስቲያናችንን ምሰሶ የለምና እንደሌሉ ቆጥረን  ስራችንን እንሰራለን።

ዋናው ጥያቄ ይሔ መንግስት እያጃጂለ እያዘናጋ የሚፈልገውን ያደርጋልና አሁንም ተዘናጋንለት የሚለው አንደሆነ እረዳለሁ።

ከዚህ በኋላ እያዘናጋ እያጃጃለ የሚያፈርስን የሚበታትን መንግስስተ አለ ብየ አላምንም ።

ታዲያ ያለው ምንድን ነው ?

አሁን ያለው  በሀይማኖት ገብቶ እፈተፈተ ከህፃን አስከ መነኩሴ እንዲበተን ፆለት የያዘበት ብኩን መንግስት  ደቃቃ ፤ ከምሁር እስከ ባለሃብት ሊለየው ጫፍላይ የለቆመ መንግስት ፤ ደጋፊና አባላቱ በግልፅ እየወጣን ነው ብለው አንድ እግራቸውን ከፓርቲው ቢሮ የነቀሉበት መንግስት በአጠቃላይ  የተበታተነ አቅም አልባ የሆነ እና ከወንጀል ለማምለጥ የሚያዘናጋ የሚያጃጅል መንግስት ነው።  ይህ መንግስት ከውጭ የዲፕሎማሲ ክስረት ከውስጥ በፖለቲካ በማሕበራዊና በኢኮኖሚ ጉዳይ የከሰረና ኤጅግ ተቅበዝባዥ የሆነ ሀይል ነው።

በተለይ ደግሞ እናቶች አባቶችና ገበሬውን በንግግሩ በማታለል ይዞት የነበረውን ፖለቲካው ድጋፍ በቀጥታ ቀሀይማኖት ውስጥ በአደባባይ በመግባትና በመጉዳት ላይመለስ ከእጁ ወጥቷል።

ገበሬ ከዚህ በኋላ  ለብልፅግና መንግስት የሚሰጠው ልብና ጆሮ አንደለሌ ማወቅ አለባችሁ።  ገበሬ የያዘውን እስኪጥል ብዙ ጊዜ ቢወስድም በቀጥታ በእምነቱ ጉዳይ ገብቶ ዶ/ር አብይ አንቅቶታል።

ሌላው በእምነት ጉዳይ ከዚህ በኋላ በደወል የሚገናኝ ንቁ ትውልድ በአንድ ሳምንንተ ውስጥ ተፈጥሯል። የሌላ እምነት ተከታዩችም ከኦርቶዶክስየነተማሩ ይመስለኛል። 

ይህ ሁሉ ሆኖ ዶ/ር አብይ ሸወደን አልሸወደን  ዋጋ የለውም። ለእነሱ የተሰጠው ጊዜ ሌላ ተንኮል ለማሰብ የሚያስብበት ቢሆንም ለአባቶቻችንን መፅሐፍትን ለማገላበጫና ለማደራጃ ለእኛም ለአስተውሎትና ለንቃት የተሰጠ የጊዜ መሆኑን ማወቅ አለብን ።

የቤተክርስቲያንን ችግር ለመፍታት ሰፊ ስራ የሚጠይቅ ቢሆንም አሁን ግን የችገራቸንን መካኒኮች በማወቃችን የበለጠ ጊዜ አግኝተን ለሰልፉም ለነቀፋውም ለማውረዱም እንደርስበታለን።

በሌላ በኩል ምናልባት አባቶቻችን በጥርጣሬየሰጡትገጊዜ ካለ ከጨዋ ህዝብ ለጨዋ ሀገርና እርስት የተሰጠ የሰላም አስተዋፅኦ ተደርጎ ቢወሰድ ጥሩ ነው። የአፍሪካ ህብርት ጉባኤ አንዲካሔድ ማገዝም ሆነ መንግስት እንዲረጋጋ ማድረግ የቤተክርስቲያናችን ነባር ተግባር መሆኑን አንዘንጋ ።

Filed in: Amharic