>
5:18 pm - Thursday June 16, 1774

ግርማ የጅብጥላ፤ ስምን ከሲመት መለየት የማይችል ብአዴናዊ እንኩቶ (መስፍን አረጋ)

ግርማ የጅብጥላ፤ ስምን ከሲመት መለየት የማይችል ብአዴናዊ እንኩቶ  

ጉድ ሳይሰማ መስከርም አይጠባም እንዲሉ፣ የጭራቅ አሕመድ ቀንደኛ ሎሌ ግርማ የሺጥላ፣ ስልጣን እያለኝ ስልጣን እንደሌለኝ ይስማኛል ብሎ አማረረ አሉ፡፡  እንክትካች በሉት፡፡  በኔ በኩል ደግሞ ደደብ በማለት አንባቢን ላለማስቀየም ስል ብቻ እንኩቶ ብየዋለሁ፡፡  ይሄን እንኩቶ የምጠራው ደግሞ ግርማ የሺጥላ ብየ ሳይሆን ግርማ የጅብጥላ ብየ ነው፣ ጥላነቱ ለሺወች ሳይሆን፣ ለኦነጋዊው ጅብ ለጭራቅ አሕመድ ነውና፡፡

እንኩቶው ግርማ የጅብጥላ ሆይ፣ ስልጣን ያለህ እየመሰለህ ስልጣን እንደሌለህ የሚስማህ እውነትም ስልጣን ስለሌለህ ነው፡፡  ጌታህ ጭራቅ አሕመድ የሰጠህ ስም እንጅ ስልጣን አይደለም፡፡  አንድ ልጅ ወላጆቹ ሺፈራው ብለው ስለሰየሙት ብቻ ሺወች ይፈሩታል ማለት አይደለም፡፡  አንተ ደግሞ፣ ጌታህ ጭራቅ አሕመድ ያማራ ክልል የብልጽግና ጽፈትቤት ኃላፊ ብሎ ስለሰየመህ ብቻ የጽፈትቤቱ ኃላፊ ነህ ማለት አይደለም፡፡

ስልጣን የስም ሳይሆን የግብር የሚሆነው፣ ስልጣኑን የሚደግፍ፣ ከስልጣኑ ጀርባ የቆመ ጠንካራ ደጀን ኃይል ሲኖር ብቻ ነው፡፡  አንተ ግርማ የጅብጥላ ግን ለስልጣንህ ደጀን በመሆን ስልጣንህን እውነተኛ ስልጣን የሚያደርግልህን ፋኖን አዋርደሃል፣ ገድለሃል፣ አስረሃል፡፡  እወክለዋለሁ የምትለው ያማራ ሕዝብ ደግሞ የስልጣንህ ደጀን መሆን ይቅርና ቢያገኝህ፣ መሣርያ ቢያጣ በጥርሱ ይዘለዝልሃል፡፡ 

ስለዚህም ያንተ ስልጣን ምንም መሠረት የሌለው፣ በጭራቅ አሕመድ በጎ ፈቃድ ላይ ብቻ የተንጠለጠለ፣ የስም ማለትም የይስሙላ ስልጣን ነው፡፡  ስልጣንህ በጭራቅ አሕመድ በጎ ፈቃድ ላይ ብቻ ስለተንጠለጠለ ደግሞ በስልጣንህ ማድረግ የምትችለው ጭራቁ የፈቀደልህን ብቻና ብቻ ነው፡፡  ከጭራቁ ፈቃድ ውጭ አንዲት ጋት ለመራመድ ብትሞክር ደግሞ፣ እድለኛ ከሆንክ እንደነ ገዱ አንዳርጋቸው በብጣሽ ወረቀት ያባርርሃል፣ እድለኛ ካልሆንክ ደግሞ እንደነ ዶክተር አምባቸው ይረሽንሃል፣ ወይም እንድነ አበረ አዳሙ በመርዝ ይገልሃል፡፡  ስለዚህም አንተ በስም የያዝከውን ስልጣን፣ በግብር የያዘው ጭራቅ አሕመድ ነው፡፡  ስልጣን እያለህ ስልጣን እንደሌለህ የሚስማህ በዚህ ምክኒያት ነው፡፡  ገባህ፣ የኔ እንኩቶ፡፡ 

እንኩቶየ፣ ስልጣን እያለህ ስልጣን እንደሌለህ እንዳይሰማህ ከፈለክ፣ ማለትም ስልጣንህ የስም ሳይሆን የግብር እንዲሆን የምትፈልግ ከሆነ፣ ይችን አጭር ምክሬን ስማኝ፡፡  ፋኖን ማዋረድህን፣ ማሰርህንና መግደልህን አቁመህ ውስጥ ለውስጥ አጠናክረው፡፡  የጭራቅ አሕመድ ሸኔ መቶ አማራ ሲጨፈጭፍ፣ ፋኖ ደግሞ ባጸፋው ሺ ሸኔ እንዲረፈርፍ በሕቡዕ አመቻችለት፡፡  የጭራቅ አሕመድ ሸኔ አንድ ያማራ ጀግና ሲገድል፣ ደመላሽ ፋኖ ደግሞ አንዱን ቀንደኛ ኦነግ መርጦ ባደባባይ ላይ እንዲዘርረው በመረጃና በመሳስሉት እርዳው፡፡  የጭራቅ አሕመድ ፓሊስ አንድን ያማራ ካህን በጥፊ ሲማታ፣ ፋኖ ደግሞ ያንን ፓሊስ /እገዛ/ በሩ ላይ በክላሽ እንዲያዳፍነው አስፈላጊውን \እገዛ\ በስውር አድርግለት፡፡

እኒህንና እኒህን የመሳስሉትን ስታደርግ፣ ታላቁ ያማራ ሕዝብ ደጀን ስለሚሆንህ፣ ስልጣንህ የስም ሳይሆን የግብር ይሆናል፡፡  ጭራቅ አሕመድ ደግሞ ፊትህን ለማየት ይፈራል፡፡  የተዋሕዶን ኃይል አይቶ በመፍራት በተዋሕዶ አባቶች እግር ሥር እንደወደቅው ሁሉ፣ ያማራን ኃይል አይቶ በመፍራት እግርህ ሥር ይወድቃል፡፡  እግርህ ሥር ሲወድቅ ግን፣ በወደቀበት አናቱን በርቅሰህ ለዘላለሙ ሸኘው እንጅ፣ እንደ ተዋሕዶ አባቶች ተነስ ብለህ እጆችህን አትስጠው፣ የሰጠኸውን እጆች አስሮ አንተኑ ራስህን እግሩ ሥር ይጥልሃልና፡፡   ጭራቅ አሕመድ ማለት፣ ሲያቃጡብት የሚጥመለመል፣ ሲዞሩለት የሚናደፍ፣ የነደፈውን ሁሉ የሚገድል፣ አሲል እባብ መሆኑን መቸም ቢሆን አትዘንጋ፡፡  እባብ ግደል፣ ከነብትሩ ገደል፡፡   

በመጨረሻም እንኩቶየ፣ ይችን አጭር ምክሬን ላንተ ቢጤ ብአዴናዊ እንኩቶወች፣ በተለይም ደግሞ ለተመስገን ጡሩነህ  እና ሰማ ጡሩነህ አስተላልፍልኝ፡፡  እሽ የኔ እንኩቶ፡፡        

መስፍን አረጋ 

mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic