>
5:26 pm - Sunday September 15, 0926

ለመላው ኢትዮጵያውያን ለአማራ ክልል መንግስት...! (ሰርካለም ፉሲል)

ለመላው ኢትዮጵያውያን

ለአማራ ክልል መንግስት…!

ሰርካለም ፉሲል

እስክንድር ዘመኑን ሙሉ አንድ ቀን እንኳ እፎይ ሳይል ቤቱንና ልጁን ከሃገርና ሕዝብ አይበልጥብኝም ብሎ ሲከፍል ስለኖረው መስዋዕትነት ሁሉም የሚያውቀው ጉዳይ ነው:: 

እስክንድር በሃገሪቱ ለመጣው ለውጥ የእራሱን አሻራ ያኖረ ቢሆንም በግርግር ስልጣን የያዘው ተረኛውና ዘረኛው የኦሮሙማ መንግስት ሰላማዊና ሕጋዊ በሆነ መልኩ እስክንድር የሚያደርገውን ትግል እንዲያካሂድ እድል ነፍጎታል:: በሕይወትም እንዳይቆይ ለማጥፉት የነበረውን እቅድ እስክንድር አስቀድሞ በማወቁ ከከተማ ተሰዶ በገጠር እንዲቀመጥ አስገድዶት ቆይቷል::

በዛሬው እለት በአማራ ክልል ልዩ ሃይል እስክንድር መታሰሩን ተረጋግጧል:: መታሰር ለእስክንድር አዲስ ባይሆንም የአማራ ክልል መንግስት  ለዘረኛውና ለተረኛው የኦሮሙማ የፌዴሬራል መንግስት አሳልፎ እንዳይሰጠው በጥብቅ አደራ ማለት እፈልጋለሁ::

 የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይም መላው የአማራ ሕዝብ ፣ ዋጋ የከፈለለት የአዲስ አበባ ህዝብ እስክንድር ለገዳዮች ተላልፎ እንዳይሰጥ ያለቅድመ ሁኔታም በነጻ እንዲለቀቅ በሚቻለውና ባለህ አቅም እንድትረባረብ እንጠይቃለን::

Filed in: Amharic